Get Mystery Box with random crypto!

የተንዚህ መከታ ተጨባጭ መረጃ መሰረታዊ ግንዛቤ እና እውነታ፣ ክፍል 3 = | የ ኡስታዝ ሀቢብ ኑሩ የድምፅ ፋይሎች

የተንዚህ መከታ ተጨባጭ መረጃ
መሰረታዊ ግንዛቤ እና እውነታ፣
ክፍል 3
=================__
"_አር _ ረህማኑ አለል _ዐርሺ ኢስተዋ
ጤነኞች ብቻ የሚረዱት የአሏህ ተዓምራዊ ቃል "
"የሰው ልጅ አእምሮ ማለት ባዶ ብርጭቆ ነው የተሞላበትን ይቀበላል " ሀጂ ሸይኽ ኡመር ኢማም ሀፊዞሁሏህ
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
አሰላሙ አለይኩም ወረህመቱላሂ ወበረካቱሁ የ አኼራ ወንድሜ እንደምን ነህልኝ? የ አላህ መሺኣ ሆኖ ዛሬ ከበድ የሚል ወሬ ይዤብህ መጥቻለሁ እና ከ ልብህ ይቅር ብለህ አድምጠኝ… ከ አላህ አገኝበታለሁ ብለህ ጆሮህን ስጠኝ ስራችን ሊላህ እስካልሆነ ትርፉ ወንጀል ብቻ ነው ።ሞት እና ቀብር እንዳለ አትርሳ …አሁን የፃፍኩልህን ሳላነብልህ አጀሌ ደርሶ ብለይህ አደራ ፋቲሃ ቅራልኝ,አኼራን እያሰብክ, የሲሯጡን መንገድ, ጣረ ሞት ላይ ያለውን የውሀ ጥም አትዘንጋው ኺታሜን እና ኺታምህን አላህ ያሳምርልን ።ዛሬ በጣም ፈልጌሃለሁ በጤናማ አስተሳሰብ ስማኝ,ካንተ ማገናዘብ እና ማመዛዘንን እሻለሁ የማወራህ ለቀብሩ ቤትህ የሚጠቅም ወሳኝ ጉዳይ ነው አደራ ወንድም ጋሼ ትህትናህ አይለየኝ ።

【NO MAN IS AN ISLAND】

።።።።።።።።።።
ዛሬ አንድ እኔንም አንተንም የሚያግባባ ሀሳብ ይዤልህ ቀርቤያለሁ ባለመስማማታችን ተስማምተን አብረን አንቀጥልም… ልብ ለልብ መገናኘታችን የግድ ነው ካሎነማ ወንድምነትህ ምኑ ላይ ነው? ??
አላህ ሱብሀነሁ ወተዓላ የፍጥረታቱ ጌታ ከማንም በላይ ሊከበር እና ሊፈራ, ሊወደድ የግድ ነው, ፀጋው ቢቆጠር አያልቅም ከሁሉ በላይ ግን ሙስሊም ስላደረገን አልሀምዱሊላህ… እና ይህ ጌታችን ለመኖሩ ጅማሬም ሆነ ፍፃሜ የለውም ሁሉ ሲጠፋ ብቻውን ቀሪ ነው… ሰው ፈጥሯል, ጅን ሰማይ,መለኢካ ሁሉንም አይመስልም, እንከን እና ጎዶሎ የሌለበት ባሪያዏቹን የማይበድል ፍትሃዊ ጌታ
።።።።።።።።።።።።።።።
አላህ በ ሱረቱ ሹራ ١١
ليس كمثله شيء
ይለናል, እኔን የሚመስል ማንም የለም, ነው ትርጉሙ አላህ እኛ በምንገለፅበት በ 1 ባህሪ እንኳን አይገለፅም እኛ ደካማ, ከጃይ ፍጡሮቹ ነን እሱ ደሞ ፈጣሪ ።
በሱረቱ ነህል ٦٠
ولله المثل الأعلى
እኔ የምገለፅባቸው ባህሪያቶች ከሁሉም ፍጡራን የተለዩ እና የተሟሉ ናቸው ይለናል
አሁንም እዛው ሱረቱ ነህል ٧٤ ላይ
فلا تضربوا لله الأمثال
ለኔ አንድም አምሳያ አታድርጉ… ማንኛችሁንም አልመስልም ይለናል…
በሱረቱል ኢኽላስ ٤
ولم يكن له كفوا أحد
ለኔ አንድም አቻ እና ወደር የለኝም ብሎ ራሱን አስተዋውቆናል… ስለዚህ አላህ በ አንድ እንኳን የፍጡር ባህሪ አይገለፅም ጌታችን እንጂ ጓደኛችን አይደለም… በመቀመጥ,ከላይ በመሆን ከታች በመሆን አይገለፅም ምክንያቱም ሁሌም እኛን አይመስልም
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ወንድሜዋ ጌታችን አላህ ምንም ነገር ሳይኖር ነበረ አርሽን ሳይፈጥር ያለ አርሽ ነበረ, አቅጣጫን ሳይፈጥር ያለ አቅጣጫ ነበረ… ከፍጥረታቱ ቅንጣት ታክል የማይፈልግ ከሁሉ የተብቃቃ ጌታ ነው ለዚህም በቁርአን ሱረቱል ኢምራን ٩٧
إن الله لغني عن العالمين
እኔ ከፈጠርኳቸው ፍጡሮች ሁሉ ምንም ነገር አልፈልግም ብሎናል አርሽም አልከው ሰማይ የርሱ ናቸው ከነሱ ትፈልጋለህ ብሎ መናገር የእናት ጡት ነካሽነት ይመስለኛል… ከማንም አልፈልግም እያለን…
።።።።።።።።።።።።።።።።
【ALLAH EXISTS WITH OUT A PLACE 】

።።።።።

ኢማሙል ቡኻሪይ በዘገቡት ሀዲስ ነብዪ ሶለሏሁ አለይሂ ወሰለም
كان الله ولم يكن شيء غيره
አላህ ምንም ነገር ሳይኖር ነበር ብለውናል… ይህ ማለት ቦታም አቅጣጫም ሳይኖር ጀሊሉ ያለ ቦታ ያለ አቅጣጫ ነበር እሱ ምን ይሳነዋል እኛንስ ሰው ይሆናል ተብሎ ከማይታሰብ ልብሳችንን ሊነካን ከማንፈልገው sperm መፍጠሩን ችሎበት የለ
…ኢማሙ ሙስሊም በዘገቡት ሀዲስ ነብዩ ሶለሏሁ አለይሂ ወሰለም
اللهم أنت الظاهر فليس فوقك شيء وأنت الباطن فليس دونك شيء
አንተ ጌታዬ አላህ ከ በላይህም ከ በታችህም ምንም ነገር የለም ብለውታል ታዳ ነቢን ነው የምትሰማው ወሀብይን? ??
እነሱ እንደሚሉት አላህ አርሽ ላይ ከሆነ በነቢ አባባል ሰማይም የለም, እኔ እና አንተም የለንም ማለት ነው ። ኧረ ወንድሜዋ ዘይንዬ ዋሽተው አያውቁም ጌታችን አላህ ከፈጠረው ነገር ሁሉ አይፈልግም ሳይፈጥራቸውም ያለነሱ የነበረ ነው ።
_አሁንም ኢማሙ ሙስሊም በዘገቡት ሀዲስ ነብዩ ሶለሏሁ አለይሂ ወሰለም
أقرب ما يكون العبد من ربه وهو ساجد، فأكثروا الدعاء
ከናንተ አንዳችሁ ለ ጌታው ቅርብ የሚሆነው ሱጁድ ሲያደርግ ነው እና ሱጁድ ላይ ዱኣ አብዙ ብለውናል እንደ ወሀብያ አስተሳሰብ አላህ አርሽ ላይ ቢሆን ቆመን ነው የሚቀርበን ወይንስ ግንባራችን መሬት ሲነካ? ??
ስለዚህ ጌታችንን አላህ በቦታም ሆነ በአቅጣጫ ነቢ ገልፀውት አያውቁም ።
።።።።።
【SHORT & PRECISE EXPLANATION ABOUT
AR_REHMANU ALEL _ARSHI ISTEWA】

ወንድሜዋ አሁን ቁርአን ላይ ብዙ ቦታ ስለተጠቀሰው
الرحمن على العرش استوى
አር _ረህማኑ አለል አርሺ ኢስተዋ ላወራህ ወደድኩ… ከዚህ በፊት ቁርአን በቀጥታ እንደማይተረጎም በደንብ ያወራን ይመስለኛል… አዏ አማረኛ ራሱ ብዙ በቀጥታ የማይተረጎሙ ቃሎች አሉት አልጋ _ወራሽ, ሆደ ሰፊ, አይነ ደረቅ, እና ሌሎችም… ይህም ቁርአን ቀጥታ ተወስዶ አላህ አርሽ ላይ ተቀመጠ ወይንም ከፍ አለ አይባልም… በአጭሩ ወደ አረብኛው አለም ልውሰድህ እና እውነታውን ላስቃኝህ

ታላቁ ሰሀብይ ኢማሙ አሊይ ረዲየሏሁ አንሁ
إن الله خلق العرش إظهارا لقدرته ولم يتخذه مكانا لذاته
አላህ አርሽን የፈጠረው ችሎታውን ሊያሳይ እንጂ ቦታ አድርጎ ሊይዘው አይደለም ። ይሉናል አቡ መንሱሪል በግዳዲይ አል ፈርቁ በይነል ፊረቅ ላይ ዘግበውታል ነቢ ሶሀቦቻቸውን ያስተማሩት ይሄንን ነው እንግዲህ አላህ ከ አርሽ አለመፈለጉን ስለዚህ ይህ ቁርአን አላህ አርሽ ላይ ተቀመጠ ተብሎ በቀጥታ አይወሰድም አሏህ አይሁዶችን የረገማቸው በምን መሰለህ በ 6ቀን ሰማይ እና ምድርን ፈጥሮ በ 7ኛው ቀን ደክሞት#አርሽ ላይ ተኛ…ተቀመጠ ወይም ከፍ አለ የሚሉት ወሀብዬች ከ እርግማን እና ቁጣው ይተርፋሉ ትላለህ? ??
ሀፊዝ አቡ በክር ኢብኑል አረቢይ ኢስተዋ 15 ትርጉም አለው ብለውናል, መቀመጥ,ከፍ ማለት, መቆጣጠር, መብሰል,ማሰብ, እኩል መሆን ወ·ዘ,ተ ስለዚህ ከነዚህ ትርጉሞች ውስጥ ለ አላህ ተስማሚ የሆነውን መምረጡ የ ግድ ነው ከፍ አለ እንዳትል ጎደሎ ባህሪ ነው በፊት አላህ ዝቅ ያለ ነበር እንዴ??? መቀመጥም ለፈጣሪ ስድብ ነው ስለዚህ ተቆጣጣረ የሚለው ተስማሚ ነው…።
ታላቁ ሰሀብይ ኢብኑ አባስ ረዲየላሁ አንህ
إذا إشتبه عليكم شيء من القرآن فاطلوبه من الشعر فإنه ديوان العرب
አንድ ቁርአን አልገባችሁ ካለ ግጥም ውስጥ ፈልጉት… ግጥም የ አረቦች መዝገበ ቃላት ነው ይሉናል ስለዚህ ወደ ግጥም ሄደን የቁርአኑን ትርጉም እንይ
ገጣሚው
••••••••••••••••••••••••••••••••••••
ዒልሙዲን ኢስላማዊ ስቱድዮ
ክፍል 4 ይቀጥላል……
https://t.me/elmudinIslamicstudio/13758