Get Mystery Box with random crypto!

የተንዚህ መከታ ተጨባጭ መረጃ መሰረታዊ ግንዛቤ እና እውነታ፣ ክፍል 2 | የ ኡስታዝ ሀቢብ ኑሩ የድምፅ ፋይሎች

የተንዚህ መከታ ተጨባጭ መረጃ
መሰረታዊ ግንዛቤ እና እውነታ፣
ክፍል 2
==========

የኢማም ማሊክ አቋም የመዲና ዓሊም እና ኢማም፤ እንደሌሎቹ የሀቅ ኢማሞች አሏህ ከቦታና አቅጣጫ ያጠሩ ነበር። . እማም አል ሙፈሲር ናሲሩዲን ኢብን አልሙኒር (አል ሙቅተፋ ፊሸረፊል ሙስጠፋ) ስለ አቅጣጫ ተናገሩና ለአሏህ ማስጠጋቱ ተገቢ አለመሆኑን ካረጋገጡ በኋላ አሉ፦ ለዚህም ትርጉም ነው ኢማም ማሊክ ያመላከቱት በዚህ የነቢዩ (ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) ንግግር እሱም {ከዩኑስ ኢብኑ መታ አታስበልጡኝ} \ቡኻሪይ ዘግበውታል\ ኢማም ማሊክ እንዲህ ብለዋል “ከዩኑስ ልዩ አድርጋቹ (አታስበልጡኝ) ያሉት ተንዚህን ለማመላከት ነው ምክኒያቱም ነቢዩ (ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) ወደ ዐርሽ ከፍ ብለዋል፤ ዩኑስ ደግሞ በህር ውስጥ ወደ ታች ጠልቀዋል፤ ነገር ግን ይህ ቢሆንም በአቅጣጫ በኩል ሁለቱም አሏህ ዘንድ እኩል ናቸው፤ ብልጫ በቦታ ቢሆን ኖሮ ነቢዩ (ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) ከዩኑስ ቅርብ እና በላጭ ቦታ ላይ የሆኑ በሆነ ነበር (አታስበልጡኝ) ብለውም ባልከለከሉ ነበር።” ይህን ንግግር ከኢማም ማሊክ ኢማም ተቂዩዲን አሱብኪይም አስተላልፈዋል በመጽሃፋቸው (አሰይፉ አሰሰቂል/137) . እንዲሁም አልሓፊዝ ሙርተዳ ዘቢዲይ በ(ኢትሓፉ-ሳደቲል ሙተቂን/105/2)ብለዋል፦ ነገር ግን ሰሪጅ ኢብኑ-ኑእማን የዘገበው ከ አብዱላህ ኢብኑ ናፊእ ከ ኢማም ማሊክ እንዲህ ብለዋል በማለት “አሏህ በሰማይ ነው እውቀቱ በሁሉም ቦታ ነው” የሚለው ንግግር ከሳቸው ያልተረጋገጠ ነው። ይህን ንግግር ያስተላለፈ ሰው ኢማም አሕመድ ስለሱ እንዲህ ይላሉ “አብዱሏህ ኢብኑ ናፊእ አሳኢግ የሐዲስ ሰው አልነበረም በዛም ደካማ ነበር” ኢብኑ ፈርሑን ደግሞ እንዲህ አሉ “መጽሃፍም መስማትም አይችልም ነበር” ኢብኑ ዐዲይም እንዲህ አሉ “ወደ ማሊክ 'ጔራኢቦችን' ያስጠጋ ነበር” በተጫማሪም ስለ ሰሪጅ አል ኑዕማን እን ኢብኑ ናፊእ በሐዲሥ ደዒፍ የሆኑና ዘገባቸው አስተማማኝ ያልሆኑት የሚገልፅ መፅሃፎች ላይ ተቀምጧል። . ስለዚህ በንዲህ አይነት ሰነድ (ዘጋቢዎች) ይህ አይነት ንግግርን ወደሳቸው አናስጠጋም፤ ስለዚህ የኢማም ማሊክ አቋም ከላይ ከተጠቀሰልን በኋላ ሙሸቢሃዎች ወደ እሳቸው የሚያስጠጉት እሳቸው ያላሉት እንደሆነ ይረጋገጥልናል ማለት ነው። 〉
አራቱ የመዝሀብ ዑለማኦች ስለ ኢስቲዋእ አንቀፅ ያነበራቸው አቋም፦ [ ክፍል - ሁለት - 2 ] -------------- -------- ----- --- 2- «ኢማም አቡ-ሐኒፈ» ፦ → ኢማም አቡሐኒፈ አሏህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና ሰለ ኢስቲዋእ ሲጠየቁ (አልፊቅህ አል-አብሰጥ/49) በሚል መጽሃፋቸው እንዲህ አሉ፦
« ﻣﻦ ﻗﺎﻝ ﻻ ﺃﻋﺮﻑ ﺭﺑﻰ ﺃﻓﻰ ﺍﻟﺴﻤﺎﺀ ﺃﻡ ﻓﻰ ﺍﻷﺭﺽ ﻓﻬﻮ ﻛﺎﻓﺮ ‏» ﻷﻧﻪ ﺃﺛﺒﺖ ﻟﻠﺤﻖ ﻣﻜﺎﻧﺎ
«ጌታዬ ሰማይ ላይ ይሁን ወስይ ምድር ላይ አላውቅም ያለ ካፊር ነው» ኢማም ዒዙዲን ኢብኑ ዐብዲሰላም (የኡለማኦች ልዑል) ተብለው ሚሰየሙት የአቡ ሐኒፋን ንግግር ጠቅሰው እንዲህ ኣሉ፦“ይህ ንግግር ለአሏህ ቦታ አለው ማለትን የሚያመላክት ስለሆነ፤ ለአሏህ ቦታ ኣለው ብሎ የሚያስብ ደግሞ ሙሸቢህ ነው (አሏህን ከፍጡር ጋር ያመሳሰለ ነው)። → ይህን ደግሞ የአቡሐኒፋ ንግግር እንደሆነ ብዙ ዓሊሞች አረጋግጠዋል። እንደ አሕመዱ ሪፋዒ፣ እንደ ተቂይ አል ሑስኒይ እና ሌሎችም። ከዚህ የተለየ ወደሳቸው ያሚያስጠጋ ካለ እንደሆነ ውሸት የተነገረ ይሆናል። ምክኒያቱም አቡ ሐኒፋ አሏህን ከተሽቢህ እና ከቦታ ያጠሩ እንደነበረ በመፅሃፎቻቸው፤ እንደ «አል-ፊቅሁል አክበር» ፣ «አል-ወሲያ» ፣ «አል-ፊቅሁል አብሰጥ» ላይ በግልፅ አስቀምጠዋል። ለምሳሌ ያህል ("አልወሲያ"/70) በሚል መጽሃፋቸው እንዲህ ይላሉ፦ “አሏህ በአርሹ ኢስቲዋእ ማድረጉን እናረጋግጣለን፤ በአርሽ ፈላጊ ሳይሆን እንዲሁም ሳይደላደልበት፤ እርሱ አርሽንም ከአርሽ ውጭ ላለውም ጠባቂ ነው፤ ከሌላው ፈላጊ ቢሆን ኖሮ እንደ ፍጡራን አለምን ማስገኘትና ማስተዳደር ባልቻለ ነበር፤ በመቀመጥና በመደላደል ከጃይ ቢሆን ኖሮ ዐርሽን ከመፍጠሩ በፊት ዬት የነበረ ሊሆን ነው?! አሏህ ከዚሁ የላቀና የጠራ ነው።» → የሚገርመው ነገር ወሃቢያዎች ይህ ንግግራቸውንም ለመበረዝ ሞክረዋል። ኢማም አቡሐኒፋ
ﻣﻦ ﻏﻴﺮ ﺃﻥ ﻳﻜﻮﻥ ﻟﻪ ﺣﺎﺟﺔ ﺇﻟﻴﻪ ﻭﺍﺳﺘﻘﺮﺍﺭ ﻋﻠﻴﻪ " «በአርሽ ፈላጊ ሳይሆን እንዲሁም ሳይደላደልበት» ያሉትን፦ ﻭﺍﺳﺘﻘﺮ ﻋﻠﻴﻪ በማለት፣ ሁለት ፊደል በማውጣት ተደላደለበት የሚለውን ትርጉም ወደሚሰጥ ቀይረውታል። ነገር ግን ንግግሩ ራሱ ያዋርዳቸዋል። እርስ በርስ የሚጋጭና የቀየሩት እንደሆነ ግልፅ ነው። ንግግሩስ እንዴት ይሄዳል? «በአርሽ ፈላጊ ሳይሆን» ብለው ተመልሰው "እንዲሁም ተደላደለበት" ማለታቸው፤ እንዲሁም የንግግራቸው መጨራሻን ካየነው አሏህ ከመደላደል ማጥራታቸውን ግልፅ ያደርግልናል «...ከሌላው ፈላጊ ቢሆን ኖሮ እንደ ፍጡራን አለምን ማስገኘትና ማስተዳደር ባልቻለ ነበር፤ በመቀመጥና በመደላደል ከጃይ ቢሆን ኖሮ አርሽን ሳይፈጥረው ዬት የነበረ ሊሆን ነው?! አሏህ ከዚሁ የላቀና የጠራ ነው» ። → እንዲሁም ("አልፊቅህ አል አብሰጥ"/57) እንዲህ ብለዋል፦ «አሏህ ቦታ ሳይኖር የነበረ ነው፤ ፍጡራንንም እንደዛው ሳይፈጥር ነበረ፤ እርሱ የነበረ ነው ዬት (ቦታ) በፊት ፍጡራንም እንዲሁም ምንም ነገር ሳይኖር በፊት የነበረ ነው እሱም ነው የሁሉም ነገር ፈጣሪ። »... → ኢማም አቡ ሐኒፋ አቋማቸው አሏህን ከቦታ እንዲሁም ከፍጡር በህሪ ማጥራት ቢሆንም ሙሸቢሃዎች ጥሜታቸውን ለማሰራጨት እሳቸው ያላሉትን በውሸት ወደሳቸው ሚያስጠጉት አይጠፋም። ከነዚህም አንዱ፦ «በአቡ ሙጢዕ አልበለኺይ የሚወራው! እሱም አቡ ሐኒፋ እንዲህ ብለዋል የሚለው ነው «ጌታዬ ሰማይ ላይ ይሁን ወስይ ምድር ላይ ይሁን አላውቅም ያለ ካፊር ነው» እስካሁን ያለው ትክክል ነው፤ ግን ከዚህ አስከትሎ እንዲህ ይላል “ምክኒያቱም 'አርረሕማኑ ዐለል ዐርሺስተዋ' ሰለሚል, ዐርሹ ደግሞ ከሰባት ሰማያት በላይ ነው” ይህ እሳቸው ያላሉት ንግግር ነው) አሁንም አስከትሎ ይላል፦ “እንዲህ ተብለው ሲጠየቁ ዐርሹ ላይ ነው ብሎ ዐርሹ ግን ሰማይ ይሁን ምድር አላውቅም የሚል ይከፍራል” [ምክኒያቱም አሏህ በቦታ ስለማይፈልግ ነው ዐርሽ ላይ ነው ማለቱ ቦታን ስለሚያመላክት ሰማይ ላይ ነው ማለት ክህደት እንደሆነ ምድር ላይ ነው ማለትም ክህደት ነው።] ዘጋቢው ግን ቀጥሎ እንዲህ ይላል “ምክኒያቱም አሏህ ሰማይ ላይ ስለሆነ...” አዑዙቢላህ አቡ-ሐኒፋ ከዚህ የፀዱ ናቸው። ሼኽ ሙላ ዐሊል ቃሪእ አልሐነፊይ አሉ፦ “ አቡ ሙጢዕ አልበለኺይ (የዚህ ንግግር ዘጋቢ) የሀዲስ ባልተቤቶች ዘንድ ወዳእ ነው (ሀዲስ ላይ ውሸትን የሚጨምር ነው)” እንዲሁም ሼኽ ሙስጠፋ አልሐማሚይ ዘገባው ተቀባይነት እንደሌለው እና “ወዳእ” መሆኑን ተናግረዋል። እንዲሁም ሙሸቢሃዎች ሚያወሩት አቡ ሐኒፋ "አሏህ ሰማይ ነው ብለዋል የሚሉት ትክክል አይደለም የራሣቸው ጭማሬ ነው።

••••••••••••••••••••••••••••••••••••
ዒልሙዲን ኢስላማዊ ስቱድዮ
ክፍል 3 ይቀጥላል……
https://t.me/elmudinIslamicstudio/13756