Get Mystery Box with random crypto!

የተንዚህ መከታ ተጨባጭ መረጃ መሰረታዊ ግንዛቤ እና እውነታ፣ ክፍል 1 | የ ኡስታዝ ሀቢብ ኑሩ የድምፅ ፋይሎች

የተንዚህ መከታ ተጨባጭ መረጃ
መሰረታዊ ግንዛቤ እና እውነታ፣
ክፍል 1
==========
አዛኝ እና ሩህሩህ በሆነው ጌታዬሥም እጀምራለሁ፣

ከአባታችን አደም እስከ መጨረሻው ነብይ የሆኑት ረሱል አለይሂ ሶላቱ ወሰላም ድረስ ያሉት ሁሉም አንብያዎች አሏሁ ተዐላ ፍጡራንን እንደማይመስል እና ከቦታ እና በአቅጣጫ የተጥራራ ነው ብለው ነው የሚያምኑት።

ሁሉም ፍጡር የሆነ ነገር ቦታ እና አቅጣጫ ይይዛል።ፍጡር ደግሞ ከሁለት ነገር አያልፍም
[ ، ﺇِﻣَّﺎ ﺟِﺴْﻢٌ ﻟَﻄِﻴﻒٌ ﺃَﻭْ ﺟِﺴْﻢٌ ﻛَﺜِﻴﻒٌ .
1ኛው የማይዳሰስ አካል ወይም
2ኛው የሚዳሰስ አካል
ﭐﻟْﺠِﺴْﻢُ ﭐﻟﻠَّﻄِﻴﻒُ ﻛَﺎﻟﻨُّﻮﺭِ ﻭَﭐﻟﺮِّﻳﺢِ ﻭَﭐﻟﻈَّﻼﻡِ ،
1)የማይዳሰሱ አካል፦ ብርሃን፣ጨለማ፣ሩህ......
ﻭَﭐﻟْﺠِﺴْﻢُ ﭐﻟْﻜَﺜِﻴﻒُ ﻛَﺎﻟﻨَّﺠْﻢِ ﻭَﭐﻟﺸَّﻤْﺲِ ﻭَﭐﻟْﻘَﻤَﺮِ
2)የሚዳስሱ አካላት፦ከዋክብት፣ፀሀይ ፣ጨረቃ፣ሰው ፣ድንጋይ......
አሏሁ ተዐላ ደግሞ ከሚዳሰስ አካል እንዲሁም ከማይዳሰሱት አካል አይደለም(የተጥራራ) ነው።
በቦታ እንዲሁም በአቅጣጫዎች መካከል ክፍተት ወይም በዛ ክፍተት የሞላው ነገር ያስፈልገዋል።
ለምሳሌ፦በአንደኛው ሰማይ እና በምድር መካከል የ500 ዓመት ያክል ክፍተት አለው።
በዚህም በሚዳሰሱት አካል እና በማይዳሰሱት አካል የተሞላ ነው ማለትም በ2ቱ መካከል ብርሃን፣ጨለማ አሉ እንዲሁም ሰው፣ድንጋይ.... በተለያዩ ነገራቶች የተሞላ ነው።አሏህ ደግሞ በሚዳሰሱትም አካል ይሁን በማይዳሰሱት አካል አይገለፅም። የተጥራራው ጌታችን አሏሁ ተዐላ አምሳያ የለውም።ለዚህም አሏህ በቁርዓኑ እንዲህ ይለናል
قال الله تعالى"فلا تضربوا لله الأمثال"

ትርጉሙም፦ለአሏህ አምሳያ አታድርጉለት
አሏሁ ተዐላ በተለያየ የቁርዓን ዐያ ራሱን ያጥራራል።ከዚህ በተቃራኒ የሚያምን ማለትም ለአሏህ አምሳያ እንዲሁም በአቅጣጫ የሚገልፅ ሰው ከእስልምና የወጣ ነው።አሏህ ይጠብቀን

ለዚህም ሰለፍ የሆኑት ትልቅ አሊም የሆኑት ኢማም አቡ ጀዕፈር አጦሀውይ እንዲህ ብለዋል
" ﻭﻣﻦ ﻭﺻﻒ ﺍﻟﻠﻪ ﺑﻤﻌﻨﻰ ﻣﻦ ﻣﻌﺎﻧﻲ ﺍﻟﺒﺸﺮ ﻓﻘﺪ ﻛﻔﺮ"
ትርጉሙም፦አሏህን በፍጡር ባህሪ በአንዱ ባህሪ የገለፀ በርግጥ ከፍሯል ማለትም ከእስልምና ይወጣል። አሏህ ይጠብቀን

አሏህ ያለ ቦታ እና ያለ አቅጣጫ ያለ ጌታ ነው

ሁላችንም ማወቅና ትርጉማቸውን በሚገባ ማወቅ መሀፈዝ የሚገባን የቁርኣን አያ አሏህን ከቦታም ሆነ ከአቅጣጫ በአጠቃላይ ከፈጠረው ነገር የማይፈልግ ጌታ መሆኑን የሚገልጽ አያዎች(ءاية) ናቸው ለሁላችንም ይጠቅመናል አንድ ሙጀሲም አላህ ያለቦታ ያለ ለመሆኑ ማስረጃ ከቁርኣንና ከሀዲስ ጥቀሱልን ካለ ሁላችንም ይህንን መመለስ እንችላለን ከሀፈዝነው አሏህ ያግራልን
قال الله تعالى{ليس كمثله شىء وهو السميع البصير}سورة الشورى11] አሏህ በተከበረው ቁርኣን እንዲህ ይለናል እርሱን የሚመስል ምንም ነገር የለም እሱም ሰሚና ተመልካች የሆነ ጌታ ነው
قال الله تعالى{ولم يكن له كغوا أحد}سورة اﻹخﻻص4] አሏህ ሱብሀነ ወተአላ በቁርኣን እንዲህ ይለናል አሏህ አንድም ቢጤና አምሳያ የለውም
قال الله تعالى{فﻻ تضربوا لله اﻷمثال}سورة النحل74]
አሏህ ሱብሀነ ወተአላ በቁርኣን እንዲህ ይለናል ለአሏህ ምሳሌ አትጥቀሱለት አምሳያ የለውምና
قال الله تعالى{ولله المثل اﻷعلى}سورة النحل60
አሏህ ሱብሀነ ወተአላ እንዲህ ይለናል አሏህ ባህሪያቶች አሉት የሌሎችን የፍጡራን ባህሪይ የማይመስሉ

قال الله تعالى{هل تعلم له سميا} سورة مريم65]
አሏህ ሱብሀነ ወተአላ በቁርኣኑ።እንዲህ ይለናል አሏህን የሚመስል ምንም ነገር የለም
ከሀዲስ ማስረጃ ካሉን ደግሞ
قال رسول الله صلى الله عليه وسلم
كان الله ولم يكن شيء غيره {رواه البخاري وغيره}
የአሏህ መልእክተኝ እንዲ ብለዋል
አሏህ ከርሱ ሌላ ምንም ነገር ሳይኖር በፊት ነበረ ቡኻሪና ሌሎች ዘግበውታል

اللهم أنت الظاهر فليس فوقك شىء وأنت الباطن فليس دونك شىء
የአሏህ መልእክተኛ እንዲህ ብለዋል አንተ ጌታዩ ሆይ አንተ ነህ አዝዛሂር ከአንተ በላይ ምንም ነገር የለም። አንተው ነህ አልባጢን ካንተ በታች ምንም ነገር የለም
قال اﻻمام علي بن أبى طالب رضي الله عنه كان الله وﻻ مكان وهو اﻻن على ما عليه كان}رواه ابو منصور البغدادي في كتابه الفرق بين الفرق ኢማሙ አሊይ እንዲህ አሉ አሏህ ነበረ ነገር ግን ቦታ አልነበረም ቦታ ሳይኖር ያለቦታ ነበር አሁንም ቦታን ከፈጠረ በኃላ ያለ ቦታ ያለ ጌታ ነው{ይህንን ንግግር አቡ መንሱር በግዳዲይ አልፈርቅ በይነ ፈርቅ በተሰኝው ኪታብ ላይ ገልጽውታል
አንብበው አዳምጠው ከተጠቃሚዋች ያርገን ሂፋዙንም አሏህ ያግራልን
የአራቱ መዝሀብ ዑለማኦች ስለ ኢስቲዋእ አንቀፅ ያላቸው አቋም - 1- «ኢማም ማሊክ» ----------- -------- ------ ---
ኢማም ማሊክ በተረጋገጠና ትክክል በሆነ ሰነድ አብዱሏህ ኢብኑ ወህብ ባስተላለፉት እንዲህ ብለዋል፡ ﺛﺒﺖ ﻋﻦ ﺍﻹﻣﺎﻡ ﻣﺎﻟﻚ ﻓﻲ ﻣﺎ ﺭﻭﺍﻩ ﺍﻟﺒﻴﻬﻘﻲ ﺑﺈﺳﻨﺎﺩ ﺟﻴﺪ ﻣﻦ ﻃﺮﻳﻖ ﻋﺒﺪ ﺍﻟﻠﻪ ﺑﻦ ﻭﻫﺐ ﻗﺎﻝ : ﻛﻨﺎ ﻋﻨﺪ ﻣﺎﻟﻚ ﺑﻦ ﺃﻧﺲ ﻓﺪﺧﻞ ﺭﺟﻞ ﻓﻘﺎﻝ : ﻳﺎ ﺃﺑﺎ ﻋﺒﺪ ﺍﻟﺮﺣﻤﻦ ﺍﻟﺮﺣﻤﻦ ﻋﻠﻰ ﺍﻟﻌﺮﺵ ﺍﺳﺘﻮﻯ ﻛﻴﻒ ﺍﺳﺘﻮﺍﺀﻩ ؟ ﻓﺄﻃﺮﻕ ﻣﺎﻟﻚ ﺭﺃﺳﻪ ﻓﺄﺻﺎﺑﺘﻪ ﺍﻟﺮﺣﻀﺎﺀ ﺛﻢ ﺭﻓﻊ ﺭﺃﺳﻪ ﻓﻘﺎﻝ : ﺍﻟﺮﺣﻤﻦ ﻋﻠﻰ ﺍﻟﻌﺮﺵ ﺍﺳﺘﻮﻯ ﻛﻤﺎ ﻭﺻﻒ ﻧﻔﺴﻪ ﻭﻻ ﻳﻘﺎﻝ ﻛﻴﻒ ﻭﻛﻴﻒ ﻋﻨﻪ ﻣﺮﻓﻮﻉ ﻭﺃﻧﺖ ﺭﺟﻞ ﺳﻮﺀ ﺻﺎﺣﺐ ﺑﺪﻋﺔ ﺃﺧﺮﺟﻮﻩ ﻗﺎﻝ : ﻓﺄﺧﺮﺝ ﺍﻟﺮﺟﻞ " ﺍﻩ

{ማሊክ ኢብኒ አነስ ዘንድ እያለን አንድ ሰውዬ
ገባና እንዲህ ኣለቸው፦ የአብዱላህ አባት ሆይ ﺍﻟﺮﺣﻤﻦ ﻋﻠﻰ ﺍﻟﻌﺮﺵ ﺍﺳﺘﻮﻯ ﻛﻴﻒ ﺍﺳﺘﻮﻯ
አሏህ በዐርሽ ኢስቲዋእ አደረገ ኢስቲዋኡ እንዴት ነው? በማለት ሲጠይቅ ኢማም ማሊክ ኣጎንብሰው (ከባድ በሆነ ላብ) ተውጠው ከዚያም ቀና ብለው እንዲህ ኣሉት «ረሕማን አርሽ ላይ ኢስቲዋእ ማድረጉ እሱ እንደ ገለፀው ነው ለርሱ እንዴት አይባልም እንዴታነት በሱ ላይ የተነሳ ነው (እንዴታ ለርሱ ተገቢ አይደለም) እንተ ደሞ መጥፎ እና የቢድዓ ሰው ነህ አስወጡት» ከዚያም ሰውዬውን አስወጡት። ኢማም ማሊክ እንዴታነት በሱ ላይ የተነሳ ነው (እንዴታ ለርሱ ተገቢ አይደለም) ማለታቸው፤ የአሏህ ኢስቲዋእ በእንዴታነት ሁናቴ አይደለም እንደፍጡራኑ እንደ መቀመጥና ከዛም በላይ ከፍ አለ በመሳሰሉት አይደለም
••••••••••••••••••••••••••••••••••••
ዒልሙዲን ኢስላማዊ ስቱድዮ
ክፍል 2 ይቀጥላል……
https://t.me/elmudinIslamicstudio/13755