Get Mystery Box with random crypto!

በጋና አንድ ግለሰብ በእንቅልፍ ላይ ሆኖ በአጋጣሚ ብልቱን ቆረጠ በጋና አንድ ግለሰብ በእንቅልፍ | Our World

በጋና አንድ ግለሰብ በእንቅልፍ ላይ ሆኖ በአጋጣሚ ብልቱን ቆረጠ

በጋና አንድ ግለሰብ በእንቅልፍ ላይ እያለ በአጋጣሚ የወንድ የዘር ፍሬውን በከፊል ቆርጦ ብልቱ ላይ ጉዳት ማድረሱ ተሰምቷል፡፡ኮፊ አታ የተባለዉ ግለሰብ በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ አደጋው ከተከሰተበት ጊዜ አንስቶ በሆስፒታል ውስጥ ይገኛል።

የ47 አመቱ ግለሰብ ከደረሰበት ጉዳት ለመታደግ ለቀዶ ህክምና ገንዘብ እየተሰበሰበ ይገኛል፡፡አታ ከሆስፒታል ሆኖ አደጋው እንዴት ተከሰተ ሲናገር ወንበሬ ላይ ተቀምጬ አሸለብኩኝ፤ በእንቅልፍ ልቤ ከፊቴ ሥጋ እየቆረጥኩ እንደሆነ አየሁ።"ቢላውን እንዴት እንዳነሳሁ አላስታውስም"ሲል አክሏል፡፡

በእንቅልፍ ልቡ ሆኖ ሲጮህ የደረሱለት ጎረቤቶቹ በክፍሉ ውስጥ ብቻውን ሆኖ ከፍተኛ ደም ሲፈሰዉ እንደደረሱለት ተናግረዋል::