Get Mystery Box with random crypto!

አየር ላይ እንቅልፍ ጥሏቸው ነበር የተባሉ ሁለት የኢትዮጵያ አየር መንገድ አብራሪዎች ታገዱ ከሱዳ | Our World

አየር ላይ እንቅልፍ ጥሏቸው ነበር የተባሉ ሁለት የኢትዮጵያ አየር መንገድ አብራሪዎች ታገዱ

ከሱዳን ካርቱም ወደ አዲስ አበባ ሲበር የነበረ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ሁለት አብራሪዎች አየር ላይ እንቅልፍ ጥሏቸው አውሮፕላኑ መዳረሻውን አልፎ እንደነበር ተነግሯል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዛሬ እኩለ ቀን ባወጣው መግለጫ በእለቱ በአብራሪዎቹ እና በአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች መካከል ግንኙነት ተቋርጦ እንደነበር ያረጋገጠ ሲሆን፣ መንስኤው ምን እንደሆነ እየተጣራ ነው ብሏል።

አየር መንገዱ በአብራሪዎቹ እና በአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች መካከል ግንኙነት በምን ምክንያት እንደተቋረጠ ያለው ነገር ባይኖርም የተጀመረው ምርመራ እስኪጠናቀቅ ድረስ ሁለቱ አብራሪዎች ከሥራ ታግደዋል ነው ያለው።

የበረራ ቁጥር ኢቲ 343 ቦይንግ 737-800 አውሮፕላን ከካርቱም ወደ አዲስ አበባ በ37ሺህ ጫማ ከፍታ ላይ ሲበር ነበር።

ቢቢሲ ፍላይትራዳር24ን ጠቅሶ እንደዘገበው፣ ቢያንስ ባለፉት 7 ቀናት የኢትዮጵያ አየር መንገድ በየዕለቱ ከካርቱም ወደ አዲስ አበባ በረራ ያደረገ ሲሆን፣ በረራው የሚፈጀው ጊዜም ከ1 ሰዓት ከ25 ደቂቃ እስከ 1 ሰዓት ከ29 ደቂቃ ድረስ ነው።

ይሁን እንጂ ሰኞ ነሐሴ 9፣ 2014 ከካርቱም አዲስ አበባ የነበረው በረራ አውሮፕላኑ ያረፈው ከ1 ሰዓት ከ49 ደቂቃ በረራ በኋላ ነው።