Get Mystery Box with random crypto!

ዲያከብሩት የሚፈልግ፣ እያዋረዳቸው እንዲያልቁት የሚሻ፣ እየጠላቸው እንዲወዱት የሚመኝ ሰው በርግጥ | Our World

ዲያከብሩት የሚፈልግ፣ እያዋረዳቸው እንዲያልቁት
የሚሻ፣ እየጠላቸው እንዲወዱት የሚመኝ ሰው በርግጥም ቂል ነው።
24, ፍትህ ሃይማኖት፣ ዘር ወይም ብሔር የለውም። ለማንም አይወግንም፡፡ ለሁሉም _ የሰው ዘር እኩል ይቆማል።
እናም ከተበደሉት ሁሉ ጎን ቁም፤ ይህ የሰውነትህ ክብር ነው።
25. ደስታህ ታምቆ የሚገኘው ሌሎችን በማስደሰት ውስጥ ነው፤ ቁስል ላይ
እንደሚያርፍ ዝንብ ጉድለታቸውን ከማነፍነፍ ይልቅ ጠንካራ ጐናቸውን እንዲያጐለብቱ በማገዝ ይደሰቱ ዘንድ
እርዳቸው።
26. ለእያንዳንዷ በጎ ሥራችን በአንድ ወይም በሌላ መንገድ በጎ ይዋልልናል፤
በአንፃሩ ለእያንዳንዷ ክፉ ሥራችን በአንድ ወይም በሌላ መንገድ ክፉ
ይዋልብናል።
27. በሚደርስብህ ውጫዊ ተፅእኖና በምትመርጠው ምላሽ መሃከል ማገናዘቢያ ጊዜ ያስፈልግሓል።

ያ ምርጫሕን እንድታስተካክል የሚያስችልሕ ቁልፍ መሳሪያ ነው።
አለያ ግን ምላሽህ ግልብና በውሉ ያልተሰላ በመሆኑ በአብዛኛው ለባሰ ችግር ያጋልጥሃል። ከደረሰብን ችግር ይልቅ ለችግሩ የምንሰጠው ያልበሰለ ምላሽ
ይበልጥ ይጐዳናል።
28 በሕይወት ተስፋ ለቆረጡና ዙሪያቸው ገደል ለሆነባቸው ወገኖች ተስፋ ከመሆን .
የተሻለ የመንፈስ ምግብ ፈፅሞ አይገኝም።

29 “ከሰዎች ሁሉ በላጩ ለሰዎች የነፍስ ፈጣሪ የሆነው ነው....
ነቢዩ ሙሐመድ (ሰበ መ
ለጹ 30. ላንተም ሆነ ለሰው ዘር የማይጠቅም ብሎም የሚጐዳ ሃሳብ ለማውጠንጠን
የምታፈሰውን ኃይል ጠቃሚና አወንታዊ ሃሳቦች ለማፍለቅ ብታውለው ሰው _ የመሆንን ክብር ትረዳበታለህ። በአንፃሩ
ያልተገባ ጥቅም ለማግኘት የምታውለው
ኃይል የተገባ ጥቅም ማግኘት የሚያስችልህን አቅም ያመክናል።
31 የታላቅነት መንገድ ፈታኝ መሆኑን አትዘንጋ፤ ዳገታማ ነውና የምድር ስበትን
መቋቋም ይኖርብሃል። በአንፃሩ የውድቀት መንገድ ግን ቀላል ነው፤ ቁልቁለት ነውና ስበቱም ያግዝሃል። በፈጣሪህ
የተቸረህን የመምረጥ ነፃነት ተጠቅመህ ምርጫህን አስተካከል።
32. አዕምሮህን በዕውቀት ቀልበው፤ አካልህን በተመጣጠነ ምግብና በስፖርታዊ _እንቅስቃሴ ተንከባከበው። ልቦናህን
በፍቅር ሙላው፤ መንፈስህን በዘልዓለማዊ
ግብ አድሰው። ለምሉዕ ስብዕና የሚያበቃህ አካልህን፣ አዕምሮህን፣ ልብህንና መንፈስህን ሚዛናዊ በሆነ መልኩ

ማበልፀግህ ነውና።
33. ልብህን ከጥላቻ፣ ከምቀኝነትና ከጐሜ አፅዳ፣ ይህንን በማድረግህ ነፃነትህን
ትቀዳጃለህ፣ ክፉ ስሜት ተሸክመህ ከመኖር ትገላገላለህ።
34 ይቅር በል፤ ለራስህ ያልሰጠኸውን ፍፁምነት ከሌሎች አትጠብቅ።
35. ባለፈ ነገር እርር ድብን አትበል፤ እንዲያ መሆንህ አዎንታዊ ለውጥ አያመጣም"
ይልቁንስ፡- ዛሬን በትክክል ኑር፤ ይህ ትናንትን ማረሚያ፣ ነገን ማሳመሪያ መንገድ ነውና።
36. የምታደንቃቸውን ሰዎች ለመምሰል ከመጣር ይልቅ አድናቆቱ ውስጥህ ያለውን ያንተኑ አቅም እንድታወጣ ያድርግህ፤ ሁሉም ሰዎች የራሳቸው ተሰጥኦ አላቸውና ራስህን ሁን።

37. ተፈጥሯዊ ችሎታሕን ፣ ተገንዘብ፤ እሱም ላይ አተኩር፤ የሚስብህን የዕውቀት ዘርፍ በጥልቀት
» ተማር፤ የተመቸህ የሥራ ዓይነት ላይ ተጠመድ። እንዲያ ስታደርግ የስኬት መስመር ላይ መሆንህን እርግጠኛ ሁን።
38 ኪሳራን ወደ ትርፍ
፥ ውድቀትን ወደ ስኬት መለወጥ የምትችለው ከሁኔታዎች ጋር ራስህን በማጣጣም ብልህ ውሳኔ ላይ
መድረስ ስትችል ነው።
39. በፍጡራን ላይ ያለን ተስፋ ሲሟጠጥ በአላህ ላይ ብቻ ተስፋችንን እንጥላለን፤ ያኔ ያልተጠበቀ እርዳታው ይደርሳል።
40. ከአላህ እዝነት ተስፋ አትቁረጥ፤ የርሱን እርዳታ የምታገኘው በሻትከው ያክል
መሆኑን አትዘንጋ።
41. . በዚህች ዓለም ውስጥ አላፊ ያልሆነ ነገር እንደሌለ መገንዘብ በችግር ውስጥ
ብርታትን፣ በደስታ ውስጥ መረጋጋትን ይሰጣል።
42. ስቃያችን መዳኛችን ሊሆን ይችላል፤ ብዙም አምርረን አንጥላው። ለኛ በጎ የሆኑ
ነገሮች በአብዛኛው የሚገኙት በማንወዳቸው ነገሮች ውስጥ ነውና። .
43 ከአላህ ጋር ያለህን ግንኙነት ምንጊዜም መርምር፤ ከፈጣሪ ጋር ያለህ ግንኙነት - መበላሸት ከፍጡራን ጋር ያለህን
ግንኙነት ያበላሻል።
44. ኢማን የጭንቀት ፍቱን መድሃኒት ነው፣ ከሰፊው የአኺራ ዓለም ጋራ ያለህ ግንኙነት በጠበቀ ቁጥር ስለ ጠባቧ ዱኒያ የሚኖርህ
ከልክ ያለፈ ጭንቀት
ምክንያት ያጣብሃል።
45 አላህን ብቻ በፍፁምነት በማምለክ፣ ከሁሉም አይነት ባርነቶች እራስሕን ነፃ አውጣ።

46. ኢማን ሌሎች ሰዎኅ ስላመኑ ብቻ፣ በጭፍን የሚከተሉት መሰረት አልባ አመለካከት ሳይሖን፣ የነፍስወከብ እውቀት የሚጠይቅ ምልከታ ነው።

47. የኢማንን መኖር
_ የሚያረጋግጠው መልካም ሥራ ሲሆን የዒባዳን ፍሬ የሚመሰክረው ደግሞ በጎ ሥነ-ምግባር ነው።

48 እስልምና ሕይወትን ከፋፍሎ የሚመለከት ሃይማኖት አይደለም፣ መንፈሳዊና ቁሳዊ ብሎ በመነጣጠል አንዱን ቀድሶ
ሌላኛውን አያራክስም፣ ኣኺራጥር .
ብሎ በመለያየት አንዱን አወድሶ ሌላኛውን አያወግዝም፤ መንፈሳዊ ልእልናን ከዓለማዊ ሕይወት ስኬት ጋር ያጣመረ
ድንቅ የሕይወት ጎዳና ነው።
49. ግጭት (Conflict) የሕይወት አንድ ገፅታ ነው። በትዳር ውስጥ፣ በስራ ቦታ፣
በአጠቃላይ ከሰዎች ጋር ባለን ግንኙነት ግጭት መፈጠሩ ተፈጥሯዊ ነው፤ ዋናው ጉዳይ የግጭት አፈታት ክህሎታችንን
ማዳበሩ ላይ ነው።
50. ግጭት በአስተማማኝ ሁኔታ ሊፈታ የሚችለው ሁለቱንም ወገኖች አሸናፊ
የሚያደርግ (Win-win) መፍትሄ ላይ መድረስ ሲቻል ነው። በአንፃሩ አንዱን ወገን አሸናፊ ሌላኛውን ወገን ከሳሪ
የሚያደርግ (Win-loss) የግጭት አፈታት ግን ጊዜውን ጠብቆ እንደሚፈነዳ የተቀበረ ቦንብ ከባድ ግጭት እንዲረገዝ
ያደርጋል።
51. ለአጭር ጊዜ ለምታገኘው ሰው መልካም መሆን ቀላል ሊሆን ይችላል፤ ሁሌም
አብራህ ለምትኖረዋ የትዳር አጋርህና ለቤተሰቦችህ መልካም መሆን ግን ያንተ ደግነት መለኪያ ነው። “ከናንተ ውስጥ
የተሻለውና በላጩ ለቤተሰቦቹ (ለባለቤቱ) ይበልጥ መልካም የሆነው ነው፤ ነቢዩ ሙሐመድ (ሰዐወ)
52. ልባዊ ፈገግታ የሰዎችን ልብ ይከፍታል፤ ለሰው ልጅ ያለህን አክብሮት
የምትገልፅበት ዓለም አቀፋዊ ቋንቋም ነው።
53 የልጆች አስተዳደግ የወደፊት ማንነታቸው መሰረት ነው።
የሚታጨደው የተዘራው ነው።


54 በልጅነት አዕምሮ ላይ የተፈጠረ ጠባሳ ለተንሻፈፈ ስብዕናና ለተዛባ ማንነት ዋነኛ
ምክንያት ነው። ተንቆ ያደገ ህፃን ሰው መናቁ፣ ተዋርዶ ያደገ ህፃን ሰው ማዋረጁ፣ ተፈጥሯዊ ውጤት ነው።
። ህፃናት አድገው
ሰው ያከብሩ ዘንድ ሊከበሩ፡ ለሰው ያዝኑ ዘንድ ሊታዘንላቸው የግድ ይላል።
55. የህፃናትን ኣእምሮ ማዳበር ለነገ የሚባል ስራ አይደለም፤ አሊያ ግን ሕብረተሰቡ ውስጥ የሕፃናት አዕምሮ ያላቸው ትልልቅ ሰዎች መበራከታቸው አይቀርም። እነዚሕ ትልልቅ ሰዎች የሚፈጥሩት ማኅበራዊ ቀውስ
በቀላሉ የሚታከም
አይሆንም።
56. የሕብረተሰባችን የወደፊት እጣ ፈንታ የታመሙ ስብዕናዎችን ለማከምና ንፁሃን ሕፃናትን ጤንነታቸውን ለመጠበቅ
በምናደርገው ትግል ይወሰናል፤ ስኬቱም በውጤቱ ይለካል።
57. <- በአንድ በሆነ አጋጣሚ እንደቀላል የተናገርነው አዋራጅ ቃል በተሰዳቢው ግለሰብ
ላይ የማይሽር ቁስል ሊፈጥር ይችላል፤ ቁስሉ እያመረቀዘ የግለሰቡን ስብዕና በክሎ እርሱም በተራው ሌላ ሰው
እንዲያቆስል ምክንያት ይሆናል።
58. . ጨካኝ አባቶች በልጆቻቸው ሥነ-ልቦና ውስጥ (በተለይም በሴቶች ልጆቻቸው