Get Mystery Box with random crypto!

'ለውጥ' ከተሰኘው የበድሩ ሑሴን መጽሐፍ የተቀነጨበ ቀን 18/06/06 የእናት ምክር- ለተሳካ ት | Our World

"ለውጥ" ከተሰኘው የበድሩ ሑሴን መጽሐፍ የተቀነጨበ
ቀን 18/06/06
የእናት ምክር- ለተሳካ ትዳር
ዐውፍ ኢብን ሙሐሊም አሹ ሸይባኒ ከኢስላም በፊት በአረቦች ዘንድ እጅጉን የታወቀ የጎሳ አለቃ ነበር። ኡሙ ኢያስ
የተሠኘች ልጁን ለሓሪሥ ኢብን ዓምር አልኪንዲ ሊድርለት ወስኗል። ሙሽራዋ አስፈላጊው ሁሉ ከተሰናዳላት በኋላ
ወደ ባለቤቷ ቤት ለመሄድ ተዘጋጀች። እናት በሕይወት ዘመኗ ያካበተችውን ልምድ ለውድ ልጇ ለማካፈል፣ ልጅም
ለትዳሯስኬት የሚበጃትን ምክር ከእናቷ ለማድመጥ ፊት ለፊት ተቀምጠዋል። እናቷ ኡማማ ለልጇ የለገሠቻትን ምክር
እንደወረደ ከተብኩት።
“ውዷ ልጄ ሆይ! ትዳር የተከበረ ሥርዓት እና መልካም ቤተሰብ ላለው ሰው የማያስፈልገው ቢሆን ኖሮ በርግጥም አንቺ
ከባል የተብቃቃሽ በሆንሽ ነበር። ነገር ግን ወንዶች የተፈጠሩት ለሴቶች ሲሆን ሴቶችም የተፈጠሩት ለወንዶች ነው።
ውዷ ልጄ የለመድሽውን አካባቢ እና ያደግሽበትን ግቢ ለቀሽ ወደማታውቂው ጎጆ እና ወዳልተላመድሽው ጓደኛ
እየሄድሽ ነው። አንቺን የራሱ በማድረጉ እርሱ ንጉሥሽ ሆኗል፤ አገልጋዩ ሁኚለት ያኔ ባሪያሽ ይሆናል። አንቺ ለርሱ
ምድር ሁኚለት ያኔ እርሱ
ለአንቺ ሰማይ ይሆንልሻል። የምንጊዜም ስንቅና ማስታወሻ የሚሆኑሽን አስር ነጥቦች ያዥልኝ።
ደግሞ በመልካም እሺታ
አንደኛውና ሁለተኛው: ጉድኝትሽ በመብቃቃት፣ መኗኗርስ በመልካም እሺታና መታዘዝ ላይ የተመሰረተ ይሁን። ባለው ነገር መብቃቃት ልብን ሲያረካ፣ በእሺታና በመታዘዝ ውስጥ ደግሙ የአላህ ውዴታ ይገኛል።
ሦስተኛውና አራተኛው። አፍንጫውን ጠብቂለት፣ ዐይኑንም ተጠንቀቂለት። ዐይኑ ካንቺ ላይ ባለ የማያስደስት ነገር ላይ
እንዳያርፍ፣ አፍንጫውም ከአንቺ ምርጥ ሽታን እንጂ ሌላ እንዳያሸት። ኩል ጥሩ መዋቢያ ሲሆን፤ ውሃም ሽቶ በሌለ ጊዜ
ጥሩ ሽቶ ነው።
አምስተኛውና ስድስተኛው። የምግብ ሠዓቱን ጠብቂለት፣ የእንቅልፍ ጊዜውንም የተረጋጋ አድርጊለት። ምክንያቱም
የረሃብ ሐሩር አቃጣይ ሲሆን እንቅልፍ ሲረበሽ ደግሞ ቁጣን ይፈጥራል።
ሰባተኛውና ስምንተኛው፡ ወገኖቹን እና ዘመዶቹን አክብሪለት፤ ገንዘቡንም ጠብቂለት። ገንዘቡን መጠበቅሽ መልካም
አስተዳደርሽን የሚያሳይ ሲሆን ዘመዶቹን ማክበርሽ ደግሞ መልካም አኗኗርሽን ያመለክታል።
ዘጠነኛውና አስረኛው፡ ምስጢሩን አታናፍሺ፤ ትዕዛዙንም አትጣሺ። ምስጢሩን ካባከንሽ ከተንኮሉ አትድኚም፤
ትዕዛዙንም ከጣስሽ ልቡን ታውኪዋለሽ።
አምስቱ የለውጥ መሰረቶች
1. የለውጥ ሑሉ መነሻና መሰረት የአስተሳሰብ ለውጥ ነው።
2. ሐላፊነች መውሰድ።
3. ሕመሙን መቋቋም።
4. የምንሰራውን ስራ በጥራት ወይም በማሳመር መስራት።
5. ለውጥን አስቀጥል።

የሉቅማን ማስታወሻ
1 የለውጥ ሁሉ መነሻው የአስተሳሰብ ለውጥ መሆኑን አትዘንጋ፤ ከየትኛውም ውሳኔ
በፊት ዕውቀትን አስቀድም፤ ዕውቀትህን ለማዳበርም ሁሉንም ዓይነት መንገዶት ተጠቀም።
2. ትውልድ የግለሰቦች ቅብብሎሽ ነው፤ ራስህን በመለወጥ ለትውልዱ ጥራት

የበኩልህን ኃላፊነት ተወጣ።
3. የመጀመሪያው መለኮታዊ ቃል “አንብብ!” የሚል መሆኑን ሁሌም አስታውስ፣ ከንባብ ጋር እራስሕን በፅኑ አስተሳስር፤
የሕይወትህ መሠረት በዕውቀት ላይ
ይታነፅ።
4.የስልጣኔን ልጓም የሚጨብጡት አንባቢ ሕዝቦች ናቸው፤ በጥንቱ ዘመን ግሪካዊያንና ሮማዊያን፣ በመካከለኛው ዘመን
ሙስሊሞች፣ በዘመናችን ደግሞ ምዕራባዊያን በንባብ አፍቃሪነታቸው የሚታወቁ ሕዝቦች ናቸው።
5 ከቁስ ድህነት ይልቅ የአዕምሮ ድህነት አደገኛ መሆኑን እወቅ። የበለፀገ አዕምሮ
የቁሱን ዓለም የማበልፀግ አቅም አለው፤ የአዕምሮ ድህነት ግን የበለፀገን የቁስ ዓለም ያወድማል።
6. አዕምሮውን ለማልማት የማይሠራ ትውልድ ወደ ጥፋት የሚያደርሰውን አጭር | ጐዳና በመከተል ላይ ነው።
7 ዘመኑ ያመጣውን ሁሉ ሙሉ በሙሉ አትቀበል፤ የጥንቱንም ሁሉ አትቀድስ።
ከዘመኑ መልካሙን፥ ከጥንቱም ጥሩውን መምረጥ የሚያስችል የአስተሳሰብ ሚዛን አዳብር።
8 ከጭፍን የሃይማኖት ወይም የፖለቲካ አመለካከት ደቀ መዝሙርነት ራስህን
ጠብቀ፤ ዕውቀት ላይ የተመሰረተ እምነት አዳብር። ዕውቀት ልቦናን ያሰፋል፤ እይታን ያስተካክላል፤ ነፍስን ከጭንቀት፣
ከሃዘንና ከመደበት ይገላግላታል።
9. የትኛውም ትውልድ ለሀገሩ የሠራው መልካም ሥራ ሊያስወድሰው፣ በሐገሩና በወገኑ ላይ የፈፀመው በደል ያስውግዘዋል። ታሪክ መልካሙን ለማጎልበትና ከስህተት ለመማር መዋል ይኖርበታል
። በዚህም የተሻለ ዘመን ይፈጠራል።
10. በታሪክ ውስጥ አይነኬ ነገር የለም።
፤ በተለይ የሀገራችን ታሪክ በአዲስ መልክ ሊፈጠር ግድ ይለዋል፤ በሳይንሳዊ መንገድ መፈተሽ ይኖርበታል፤ ይህ
ሲሆን ግን የተሳለች ኢትዮጵያን መፍጠር ዋነኛ ግቡ መሆን ይኖርበታል
• በታሪክ ውስጥ ለተፈፀመ ስህተት ተጠያቂ ትውልድ አሁን የለም፣ የአሑኑ ትውልድ የሚጠየቀው ራሱ በሠራው ታሪክ ነው። በታሪክ ውስጥ ለታየ ስኬትም ተሸላሚ ትውልድ አሁን የለም፣
ተሸላሚዎቹ ያንኑ ታሪክ የሠሩት ትውልዶኅ ናቸው። የዘመኑ ትውልድ ከታሪክ በመማር የተሻለ ታሪክ ሊሠራ እንጂ
በታሪክ ሊኮፈስ ወይም ሊያፍር አይገባውም።
12. ለሥነ-ምግባር እነፃ ትልቅ ቦታ ስጥ፤ የሰው ልጅ ማኅበራዊ ስኬት በሥነ-ምግባሩ
ደረጃ ይለካልና።
13. ከራስህ ጋር እርቅ ፍጠር፤ ለህሊናህ የሚጎረብጥ አንዳች ነገር በምንም መልኩ
ላለመፈፀም ጥረት አድርግ።
14. ስሜትህ ከህሊናህ በላይ እንዳይነግስ ታገለው፤ ስሜት በአንድ ሰው ሕይወት
ውስጥ ከገዘፈ ወደ ጥፋት ማምራቱ አይቀሬ ነው።
15 ደመ-ነፍሳዊ ስሜት (ሕዋ) ታች የሌለው ጉድጓድ እንደማለት ነው፣ ምንም ያህል
ነገር ቢጨመርበት የማይሞላ ዓይነት። ጉድጓዱን የሚሞላው ለስርዓት ተገዥ መሆን ብቻ ነው።
16. ፍጥረተ-ዓለሙ የተገነባው በሥርዓት ነው፤ አንተም ሕይወትህን በሥርዓት
በመምራት ከፍጥረተ-ዓለሙ ጋር ተጣጣም።
17, ጥሩ አድማጭ ሁን፣ ነፃ ዕይታን በማዳበር ከቅድመ-ፍረጃ ራስህን ጠብቅ። ሰዎች
ሃሳብህን እንዲረዱ ከመሻትህ በፊት አንተ ቅድሚያ ተረዳቸው።
18. ራስህን ብቻ ከማድመጥ ተቆጠብ፤ አለያ በዙሪያህ ያሉ ሁሉ ካንተ ጋር ባላቸው
ግንኙነት ራሳቸውን ብቻ የሚያደምጡ ሆነው ታገኛቸዋለህ። ሰዎችን በሙሉ ልቦናህ አድምጣቸው፤ ያኔ እነርሱም
በሙሉ ልቦናቸው ያደምጡሃል።
19. በአንድ ጫካ ውስጥ ከሚገኙ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ዛፎች ላይ የበቀሉ
ቅጠሎች እንኳ አንድ ዓይነት አይደሉም፤ ልዩነትን አድንቅ፡፡
20. የእኔ እምነት (ሃይማኖት) ብቻ ትክክል ነው፤ ሌሎች እምነቶች በሙሉ ስሕተት
ናቸው' ብሎ ማሰብ ፅንፈኝነት አይደለም። ምክንያቱም እምነትና ተራ የግል አስተያየት የተለያዩ ናቸውና። የግል አስተያየት ትክከል ሊሆንም ላይሖንም
ይችላል ተብሎ ይታሰባል፤ እምነት ግን ለአማኙ ፍፁም ትክከል ነው። ፅንፈኝነት ሌላው እምነት በምድር ላይ እንዲኖር አለመፍቀድ
ነው::
21. አንተ ትክክል ነኝ የማለት መብት ለራስህ እንደሰጠህ ሁሉ ሌሎችም በተመሳሳይ . ትክክል ነኝ የማለት መብት እንዳላቸው
አትዘንጋ።
22. የዘር፣ ፣ የሃይማኖት፣ የቀዬ ወይም ሌላ የሚያቀራርብ ምክንያት አንድን ሰው ይበልጥ እንድትወደው ሊያደርግህ ይችላል፤
ይህ ከመሆኑ ጋር የሰው ልጅን በአጠቃላይ ግን ሰው በመሆኑ ብቻ ልታከብረው ግድ ይላል።
23. ሰዎች በናቅካቸው ልክ እንደሚንቁህ፣ ባዋረድካቸው መጠን እንደሚያዋርዱህና
በጠላኻቸው ያክል እንደሚጠሉህ እወቅ። ሰዎችን እየናቃቸው እን