Get Mystery Box with random crypto!

ላይ) ከፍተኛ ጥላቻን ሲዘሩ የወደፊት የፍቅር ሕይወታቸው ላይ የሚያደርሱት ተፅዕኖ መገመት ከሚቻለው | Our World

ላይ) ከፍተኛ ጥላቻን ሲዘሩ የወደፊት የፍቅር ሕይወታቸው ላይ የሚያደርሱት ተፅዕኖ መገመት ከሚቻለው በላይ ነው።
በሌላ ፅንፍ ግድ የለሽና ራስ ወዳድ አባቶች ደግሞ ግድ የለሽና ለሰዎች ዋጋ የማይሰጡ ከዛም በላይ የበታችነት ስሜት -
የተጋቱ ልጆችን ያበቅላሉ።
59. የበርካታ ችግሮቻችን ዋነኛ ምክንያት በግለሰብ ደረጃ ማንነታችን የተገነባበት
መሠረት፣ እኛነታችን የተዋቀረበት ማገርና ስብዕናችን የቆመበት ምሰሶ ምንነት ነው ወላጅ፣ መምህር፣ የድርጅት
አስተዳዳሪ፣ የቢሮ ሠራተኛ፣ ወታደር፣ ሳይንቲስት፣ ሃኪም፣ የሀገር መሪ፣... የሚሆነው ይኼው ግለሰብ ነውና።
60. . ትዳር መልካም ማሳ ነው፣ በየጊዜው የፍቅር ውሃ ማጠጣት፣ የቂምና የጐሜ
አረሞችን መንቀልና በቂ የመተሳሰብና የመገነዛዘብ ብርሃን እንዲያገኝ ማድረግ ያሻል። ያኔ ማሳው መልካም ፍሬውን
ይለግሳል።
61. ቤታችን ፍቅር የሚዘንብበት፣ መከባበር የሰፈነበት፣ መተዛዘን የሚታይበት
መረዳዳት ልዩ ባህሪው የሆነ ማረፊያችን ይሆን ዘንድ መሥራት ይኖርብናል።
። በኢማን መድመቅና በመልካም ሥራ መዋብ
እንዲያ ዓይነት ቤት
ይፈጥራል።
62 ህፃናት ስብዕናቸውን ከሚያቆሽሽ ወይም ራሳቸውን ዝቅ አድርገው እንዲመለከቱ
ከሚያደርግ የትኛውም ዓይነት ጥቃት የሚጠበቁበትን ሁኔታ ማመቻቸት ለነገ የማይባል ማኅበራዊ ኃላፊነት ነው።
63. ክብርንና ነውርን ማወቅ ትልቅነት ነው፤ ክብር ነውር፥ ነውር ደግሞ ከብር የሆነበት ማኅበረሰብ የሞራል እሴቶች ሞት
የተበሰረበት ማኅበረሰብ ነው።
64 ሕይወትህ ወጥ፣ የማይዛነፍና በሁኔታዎች ወይም በግለሰቦች ተፅዕኖ
የማይፍረከረክ ይሆን ዘንድ መርህን ማዕከሉ ያደረገ Principle Centered) የሕይወት ፍልስፍና አዳብር።
65 ፍትህን አስፍን፤ እንዲያ በማድረግህ አንተን የሚጐዳ አጋጣሚ ቢፈጠር እንኳ።
የመለኮታዊ ቃሉ ትእዛዝም ይኸው ነው።
66. ምድር ያላት ሃብት ለሰው ልጆች ሁሉ ከበቂ በላይ ነው፤ ስግብግብነትን
አስወግደህ ለጋራ ብልፅግና ትጋ።
67. ደስታ የሚገኘው ለራስ ከማድረግ ይልቅ ለሌሎች በማድረግ፣ ለራስ ከመኖር
ይልቅ ለሌሎች በመኖር ነው።
68. ነፃነት ሁሉም ነገር ሊከፈልለት የሚገባ ውድ የሰው ልጅ ሃብት ነው።
69. ደስታን እንደ ዛፍ አስባት፤ ውሃዋ፣ ምግቧና አየሯ ኢማን ነው።
70. ይህች ሀገር ካለችበት የድህነት አረንቋ የምትወጣው በዕውቀት በጠገቡ
አዕምሮዎች፣ ቅን አስተሳሰብ በተሞሉ ልቦናዎችና ለሌሎች በሚኖሩ ሰብዕናዎች መሆኑን ሁሌም አስታውስ።