Get Mystery Box with random crypto!

ፓኪስታናዊው ሰው ከስምንት ዓመት በፊት የተሰረቀበት ሞተር ሳይክል የፖሊስ ባለስልጣናት እየተጠቀሙበ | Our World

ፓኪስታናዊው ሰው ከስምንት ዓመት በፊት የተሰረቀበት ሞተር ሳይክል የፖሊስ ባለስልጣናት እየተጠቀሙበት ተገኘ

በፓኪስታን የሚኖርው ኢምራን የተባለው ግለሰብ ከስምንት አመት በፊት የተሰረቀውን ሞተር ሳይክሉ የፖሊስ ባለስልጻናት እየተጠቀሙበት ማግኘቱ እንዳስደነገጠው ገልጿል።ተጎጂው ለረጅም ጊዜ የጠፋው ብስክሌቱ በላሆር በሚገኘው ሳባዛር ሰፈር ውስጥ የፖሊስ ባለስልጣናት ለራሳቸው ጥቅም ሲያውሉት እንደቆየ ተረድቷል።

በፓኪስታን የሚገኘው ዘ ኤክስፕረስ ትሪቡን የተሰኘው የመገናኛ ብዙሀን እንደዘገበው የኢምራን ሆንዳ ሲዲ 70 ሞተር ሳይክል የተሰረቀው በላሆር ሙጋልፑራ አካባቢ ነው። በወቅቱ ለፖሊስ አቤቱታ አቅርቦ የነበረ ቢሆንም በጭራሽ ግን ሊገኝ አልቻለም።

ከስምንት አመታት በኋላ ባሚገርም ሁኔታ ፖሊሶች ሞተር ሳይክሉን እየተጠቀሙ መሆናቸውን የሚያሳይ በቴክኖሎጂ የታገዘ መረጃ ደርሶታል።ኢምራን ብዙ ማመልከቻዎችን አቅርቤ ነበር ነገር ግን ምንም ውጤት አልነበረውም ብሏል። ከፖሊሶች እጅ ሞተር ሳይክሉ እንዲመለስለት ቅሬታውን አቅርቧል።