Get Mystery Box with random crypto!

በጅማ ዩኒቨርሲቲ መምህራን እና ተማሪዎች የተሠራውና አፈር መርምሮ ምን ቢዘራ አዋጭ እንደሆነ የሚለ | Our World

በጅማ ዩኒቨርሲቲ መምህራን እና ተማሪዎች የተሠራውና አፈር መርምሮ ምን ቢዘራ አዋጭ እንደሆነ የሚለው መሣሪያ ዓለም አቀፍ ዕውቅና አግኝቷል።

መሣሪያው ከሌሎች በጅምር ላይ ካሉ ኩባንያዎች ጋር በኡጋንዳ፣ ካምፓላ ተወዳድሮ አንደኛ ደረጃን በመያዝ የ25 ሺህ ዶላር ሽልማት ማግኘቱም ነው የተገለፀው።

ይህ በዓለም አቀፍ መድረክ ዕውቅና ያገኘው ‘ኦሚሽቱ-ጆይ’ ተብሎ የተሰየመው አፈር መመርመሪያ መሣሪያ ከጥቂት ዓመታት በፊት በጅማ ዩኒቨርሲቲ መምህራን እና ተማሪዎች የተሠራው ነው።

አነስተኛ መጠን ያለው መሣሪያው፣ በአፈር ውስጥ ያሉትን ንጥረ ነገሮች በመመርመር በዛ አፈር ውስጥ የትኛው ተክል ቢተከል ወይም የትኛው ዘር ቢዘራ የተሻለ ውጤት እንደሚያስገኝ ይለያል ተብሏል።

ኦሚሽቱ-ጆይ በዓለም ባንክ በሚደገፈው 'Africa Start Up Award' ውድድር ከ23 አገራት ከተወጣጡ ሥራዎች ጋር ተወዳድሮ ነው በአንደኛነት በማጠናቀቁ ሽልማቱን የተረከበው።

መሣሪያው የአፈርን የንጥረ ነገር ይዘት፣ የሙቀት መጠን (ቴምፕሬቸር) እና እርጥባማነት ለይቶ ውጤቱን ወደ ስማርት ስልኮች ይልካል።

2013 ላይ ተማሪዎች ለመመረቂያ ፕሮጀክት ያነሱት ጽንሰ ሐሳብ በመምህራን ተደግፎ ከዚህ መድረሱን በዩኒቨርሲቲው የኮምፒዩተር ሳይንስ መምህር ጃርሚያ ባይሳ ለቢቢሲ ተናግረዋል።

በአንድ አካባቢ ዘር ከመዘራቱ በፊት አፈሩ ለየትኛው የዘር ዓይነት ምቹ እንደሆነ መለየት መቻል የምርት ውጤትን ከፍ ያደርጋልም ተብሏል።