Get Mystery Box with random crypto!

ብሔራዊ ባንክ ዲጂታል መገበያያዎች በኢትዮጵያ እውቅና የላቸውም አለ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እንደ | Our World

ብሔራዊ ባንክ ዲጂታል መገበያያዎች በኢትዮጵያ እውቅና የላቸውም አለ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እንደ ቢትኮይን ያሉ ክሪፕቶከረንሲዎች በአገሪቱ ውስጥ ለግብይት መጠቀም ዕውቅና አልተሰጣቸውም በማለት ጥቅም ላይ እንዳይውሉ ከለከለ።
ብሔራዊ ባንክ በአገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን አማካይነት ባወጣው መግለጫ፤ በክሪፕቶከረንሲዎች ግብይት መፈጸም ሕገ ወጥ ተግባር በመሆኑ ኅብረተሰቡ እራሱን ከመሰል ተግባራት ይጠብቅ ብሏል።
ክሪፕቶከረንሲ ምንድን ነው?
ክሪፕቶከረንሲ በአጭር ቋንቋ የማይዳሰስ ዲጂታል ገንዘብ ማለት ነው።
ኦክስፎርድ መዝገበ ቃላት ክሪፕቶከረንሲን፤ የገንዘብ ልውውጦችን ደኅንነት የሚያረጋግጥ፣ የተጨማሪ አሃዶችን መፈጠርን የሚቆጣጠር እና ገንዘብ መተላለፉን የሚያረጋግጥ፣ ጠንካራ ክራፕቶግራፊ የሚጠቀም መገበያያ እንዲሆን ተደርጎ የተቀረጸ ዲጂታል ገንዘብ ነው ሲል ይገልጸዋል።
በአሁኑ ወቅት በርካታ ዓይነት ክሪፕቶካረንሲዎች አሉ። በስፋት ከሚታወቁት መካከል ቢትኮይን፣ ኤቴሪያም፣ ካርዳኖ እና ዶጅኮይን ተጠቃሽ ናቸው።
ክሪፕቶ በኢትዮጵያ?
ብሔራዊ ባንክ ዛሬ ባወጣው መግለጫ በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ሰዎች እንደ ቢትኮይን ያሉ ክሪፕቶከረንሲዎችን በመጠቀም ለምርት እና አገልግሎት ክፍያ እየፈጸሙ እንደሆነ ጠቁሟል።
ምንም እንኳን ባንኩ ይህን ይበል እንጂ በኢትዮጵያ ለሚሰጡት ምርት እና አገልግሎት ክፍያ በክሪፕቶከረንሲ የሚቀበሉ ድርጅቶች ስለመኖራቸው ግልጽ አይደለም።
እንዲህ ዓይነቶቹ የዲጂታል መገበያያ ዘዴዎች በአገሪቱ እየተስፋፉ መምጣታቸውን በመግለጽ በአገሪቱ ተቀባይነት የሌለው ሕገ ወጥ ድርጊት መሆኑን ብሔራዊ ባንክ አስታውቋል።
በአሁኑ ወቅት በበርካታ አገራት ሰዎች ለሚያገኟቸው ምርት እና አገልግሎቶች በክሪፕቶከረንሲዎች አማካይነት ክፍያ መፈጸም እየተለመደ መጥቷል።
ማይክሮሶፍት፣ ፔይፓል፣ የጉዞ ወኪሉ ኤክስፔዲያን ከመሳሰሉ ባለብዙ ሚሊዮን ገንዘብ ኩባንያዎችን አንስቶ እስከ ሆቴሎች እና ካፊቴሪያዎች ቢትኮይንን በክፍያ መልክ ይቀበላሉ።
ብሔራዊ ባንክ የኢትዮጵያ ይፋዊ መገበያያ ገንዘብ ብር መሆኑን አስታውሶ፤ “በየትኛውም የክፍያ መፈጸሚያ ሰነድም ሆነ ሥርዓት ያለ ብሔራዊ ባንክ ፍቃድ የገንዘብ ዝውውርም ሆነ ገንዘብ ነክ አገልግሎት መስጠት አይቻልም” ብሏል።
ክሪፕቶ እንደ ስጋት?
በክሪፕቶከረንሲ ግብይት ላይ መንግሥታት ቁጥጥር ለማድረግ ያዳግታቸዋል።
በክሪፕቶከረንሲ በሚደረጉ ግብይቶች ላይም የሻጭ እና ገዢ ማንነት ይፋ ሳይደረግ ግብይት ማድረግ ይቻላል።
በዚህም ምክንያት ሕገ ወጥ ቡድኖች/ግለሰቦች የተከለከሉ ቁሶች ሊገዙ እና ሊሽጡ ይቻላሉ። በሕገ ወጥ መንገድ የተገኘን ገንዘብ ሕጋዊ አድርገው ሊጠቀሙም ይችላሉ።
ይህም ለአገራት ስጋት ሆኖ ቀጥሏል።
ብሔራዊ ባንክም በዛሬው መግለጫው ክሪፕቶከረንሲዎች “በወንጀል የተገኘን ገንዘብ ለማሸሽ ምቹ ሁኔታን እየፈጠረ እንደሆነ ለመረዳት ተችሏል” ብሏል።
“ይህን ፈጽመው በሚገኙ አካላት ላይ ብሔራዊ ባንክ ሕጋዊ እርምጃ ይወስዳል” ካለ በኋላ ኅብረተሰቡም በዚህ “ሕገ ወጥ ተግባር” ላይ የተሰማሩትን አካላትን ለብሔራዊ ባንክ እና ለሚመለከታቸው ሕግ አስከባሪ አካላት እንዲጠቁም ጥሪውን አስተላልፏል።
የትኞቹ አገራት እውቅና ይሰጣሉ?
ብሔራዊ ባንክም በዛሬው መግለጫው ክሪፕቶከረንሲዎች “በወንጀል የተገኘን ገንዘብ ለማሸሽ ምቹ ሁኔታን እየፈጠረ እንደሆነ ለመረዳት ተችሏል” ብሏል።
“ይህን ፈጽመው በሚገኙ አካላት ላይ ብሔራዊ ባንክ ሕጋዊ እርምጃ ይወስዳል” ካለ በኋላ ኅብረተሰቡም በዚህ “ሕገ ወጥ ተግባር” ላይ የተሰማሩትን አካላትን ለብሔራዊ ባንክ እና ለሚመለከታቸው ሕግ አስከባሪ አካላት እንዲጠቁም ጥሪውን አስተላልፏል።
የትኞቹ አገራት እውቅና ይሰጣሉ?
ማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ እንዱሁም ኤል ሳልቫዶር በቅርቡ ቢትኮይንን ሕጋዊ መገበያያ አድርገዋል። ይህ ማለት ሰዎች በእነዚህ አገራት ለሚያገኙት አገልግሎት ክፍያ በቢትኮይን መፈጸም ይችላሉ።
በተቀሩት አገራት በተለይ ደግሞ በምዕራባውያን አገራት ሕገ ወጥ ነው ማለት ግን አይደለም።
አንደ ቦሊቪያ፣ ቻይና፣ ኢራን እና ኮሎምቢያ ያሉ አገራት ግን ቢትኮይን ላይ ክልከላ ጥለዋል ወይም ሕገ ወጥ አድርገውታል።