Get Mystery Box with random crypto!

በመንግስትና በኦነግ ሸኔ መካከል ሲደረግ የነበረው ድርድር ያለስምምነት ተጠናቀቀ ዋዜማ- በመንግስ | አገልግል

በመንግስትና በኦነግ ሸኔ መካከል ሲደረግ የነበረው ድርድር ያለስምምነት ተጠናቀቀ

ዋዜማ- በመንግስትና በኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት (ኦነግ ሸኔ) መካከል ላለፈው አንድ ሳምንት ሲደረግ የነበረው ድርድር ያለስምምነት መጠናቀቁን የመንግስት ዋና ተደራዳሪ ሬድዋን ሁሴን አስታወቁ።

ሬድዋን በፅሁፍ መግለጫቸው ሁለቱ ወገኖች በታንዛኒያ በመጀመሪያው ዙር ያደረጉት ድርድር ገንቢ እንደነበር ነገር ግን በአንዳንድ ጉዳዮች ላይ ከስምምነት መድረስ አለመቻሉን ገልፀዋል። ስምምነት ያልተደረሰባቸውን ጉዳዮች ግን አልተናገሩም።

የሰላም ድርድሩ አስፈላጊነት ላይ በሁለቱም ወገን መግባባት መኖሩንና በቀጣይ ተመሳሳይ ድርድር ለማድረግ ዝግጁነት መኖሩንም ሬድዋን አመልክተዋል። አደራዳሪዎችን ያመሰገኑት ሬድዋን መንግስት ለሰላም ዝግጁ መሆኑንና በሀገሪቱ ህገመንግስት ማዕቀፍ ውስጥ ማናቸውንም ግጭቶች ለመፍታት ቁርጠኛ መሆኑን አመልክተዋል።
በድርድሩ ዙሪያ ከኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት (ኦነግ ሸኔ) በኩል ይህ ዘገባ እከተዘጋጀበት ሰዓት ድረስ የተባለ ነገርየለም።