Get Mystery Box with random crypto!

አስተማሪ ምክር ከመጽሐፍ ቅዱስ አንብቡት # ለጭንቀትና # ፍርሃት መፍትሄ የሆኑ ጥቅሶች «===== | ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ልጆች

አስተማሪ ምክር ከመጽሐፍ ቅዱስ አንብቡት
# ለጭንቀትና # ፍርሃት መፍትሄ የሆኑ ጥቅሶች
«===========
፩• ጽኑ አይዞአችሁ አትፍሩ ከፊታቸውም አትደንግጡ አምላክህ እግዚአብሔር እርሱ ከአንተ ጋር ይሄዳል።/ዘዳ 31÷6/
፪• በእግዚአብሔር ዘንድ ልመናችሁን አስታውቁ እንጂ በአንዳች አትጨነቁ። \ፊሊጵ 4÷6/
፫• በምትሄድበት ሁሉ አምላክህ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ነውና ጽና አይዞህ አትፍራ።/ኢያሱ 1÷9/
፬• ሰላሜን እሰጣችኋለሁ ልባችሁ አይታወክ።/ዮሐ 14÷27/
፭• እግዚአብሔርን ፈለግሁት መለሰልኝም ከመከራዬም ሁሉ አዳነኝ። /መዝ 34÷4/
፮• የክርስቶስ ሰላም በልባችሁ ይግዛ።/ቆላስ 3÷15/
፯• የሰላምም ጌታ ራሱ በሁሉ መንገድ ዘወትር ሰላምንይስጣችሁ። /2ኛ ተሰሎ 3÷16/
፰•እግዚአብሔር እረዳቴ ነው አልፈራም ሰው ምን ያደርገኛል። /መዝ 118÷6/
፱• ፍፁም ፍቅር ፍርሃትን አውጥቶ ይጥላል እንጂ በፍቅር ፍርሃት የለም። /1ኛ ዮሐ 4÷18/
፲• እርሱ ስለ እናተ ያስባልና የሚያስጨንቃችሁን ሁሉ በእርሱ ላይ ጣሉት። /1ኛ ጴጥ 5÷7/
# ከሰዎች # ጋር # በሰላም # ለመኖር # የሚረዱህ # ምክሮች
=====================================
፩• ስትሰጥ ምላሽ አትጠብቅ። /ምሳሌ 21÷26/
፪• ካለመጠርጠር እመን። /1ኛ ቆሮ 13÷7/
፫•ይቅር ስትል ቂም አትያዝ። \ቆላስ 3÷13_14/
፬• የሰው ንግግር ሳታቋርጥ አዳምጥ።/ምሳ 18
፭•ሰዎች ላይ ክፉ አታስብ። /ፊልጵ 2÷14/
፮• መልስ ስትሰጥ አትከራከር። /ምሳ 17÷1/
፯• ቃልህን ጠብቅ። /ማቴ 5÷37/
፰• ለመስማት እንጂ ለመናገር አትፍጠን።/ ያዕቆ 1÷19/
፱• በሁሉም ነገር ትግዕስተኛ ሁን። \1ኛ ቆሮ 13÷4/
፲• ይቅር መባባልን ሁሌም አትዘንጋ። /ኤፌሶ 4÷31_32/
# ለትዳር # ጠቃሚ # ምክር
=====================================
፩• ሁልግዜም ትዳርህን አጥብቀህ ያዝ። /ማር 10÷9/
፪• ለትዳርህ ታማኝ ሁን። /ምሳሌ 5÷15_23/
፫•ለመንፈሳዊ ውጊያዎች ዝግጁ ሁን። /ኤፌ 6÷11\
፬• ፈተናዎችን ለማለፍ ልብህን ጠብቅ። /ምሳ 4÷23/
፭• በጸሎት መጽናት እዳለብህ አትዘንጋ። /ሮሜ 12÷12/
፮• ባለቤትህን አፍቃሪ ሁን።/1ኛ ቆሮ 13÷7/
፯• በሁሉም ነገሮች አመስጋኝ ሁን።/1ኛ ተሰሎ 5÷18/
፰• የተበደልከውን አትቁጠር። /1ኛ ቆሮ 13÷5/
፱• አነጋገርህ በቅንነት የተሞላ ይሁን።/ ምሳ 16÷24/
፲• ሁልጊዜም ይቅር ባይ ሁን። /ማቴ 18÷21_22/
# ጠቃሚ # ምክር
====================================
፩• እግዚአብሔርን ከሁሉም በፊት አስቀድም።/ማቴ 6÷33/
፪• ሳታቋርጥ ጸልይ። \1ኛ ተሰሎ5÷17_18/
፫• በሁሉም አመስግን።/ መዝ 100÷4/
፬• ቃልህን ጠብቅ። /ሮሜ 4÷21/
፭• ይቅር በል። /ቆላስ 3÷13/
፮• በትጋት ስራ። /ቆላስ 3÷23/
፯• ሁልግዜ እውነትች ተናገር። /ምሳሌ 12÷22/
፰• ቸርና ርኅሩህ ሁን። \ኤፌ 4÷32\
፱• እርስ በርሳችሁ ተጽናኑ። \1ኛ ተሰሎ 4÷18/
፲• እርስ በርሳችሁ ተዋደዱ። 1ኛ ጴጥሮ 1÷22/