Get Mystery Box with random crypto!

“30' የመፅሐፍ ቅዱስ ትዛዛት፦! '---------------------------------' 1:-እ | ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ልጆች

“30" የመፅሐፍ ቅዱስ ትዛዛት፦!
"---------------------------------"
1:-እርስ በርሳችሁ አትጣሉ::(ዘፍ 45:24)
2:_እርስ በርሳችሁ ሐሰት አትነጋገሩ::(ዘሌ 19:11)
3:_እርስ በርሳችሁም ተስማሙ::(ማር 9:50)
4:_እርስ በርሳችሁ አታንጎራጉሩ::(ዮሐ 6:43)
5:_እርስ በርሳችሁ ተዋደዱ::(ሮሜ 12:10)
6:_እርስ በርሳችሁ ተከባበሩ::(ሮሜ 12:10)
7:_እርስ በርሳችሁ በአንድ ሀሳብ ተስማሙ::(ሮሜ 12:16)
8:_እርስ በርሳችሁ ከመዋደድ በቀር ለማንም እዳ አይኑርባችው::(ሮሜ 13:8)
9:_እርስ በርሳችሁ በአንድ ሐሳብ መሆንን ይስጣችሁ::(ሮሜ 15:5-6)
10:_እርስ በርሳችሁ ተቀባበሉ::(ሮሜ 15:7)
11:_እርስ በርሳችሁ ሰላምታ ተሰጣጡ::(ሮሜ 16:16)
12:_እርስ በርሳችሁ አትከላከሉ::(1ኛ ቆሮ 7:5)
13:_እርስ በርሳችሁ ተጠባበቁ::(1ኛ ቆሮ 11:33)
14:_እርስ በርሳችሁ እንደ ባሪያወች ሁኑ::(ገላ 5:13)
15:_እርስ በርሳችሁ እንዳትጠፍፉ ተጠንቀቁ::(ገላ 5:15)
16:_እርስ በርሳችሁ በፍቅር ታገሱ::(ኤፌ 4:2)
17:_እርስ በርሳችሁ ቸሮችና ሩህሩሆች ሁኑ::(ኤፌ 4:32)
18:_እርስ በርሳችሁ ተነጋገሩ፤ለጌታ በልባችሁ ተቀኙና ዘምሩ::(ኤፌ 5:19)
19:_እርስ በርሳችሁ ትዕግስትን አድርጉ::(ቆላ 3:13)
20:_እርስ በርሳችሁ አስተምሩና ገስፁ::(ቆላ3:16)
21:_እርስ በርሳችሁ በዚህ ቃል ተፅናኑ::(1ኛ ተሰ 4:18)
22:_እርስ በርሳችሁ ተመካከሩ::(1ኛ ተሰ 5:11)
23:_እርስ በርሳችሁ በሰላም ሁኑ::(1ኛ ተሰ5:12-13)
24:_እርስ በርሳችሁ ለሁሉም መልካሙን ለማድረግ ትጉ::(1ኛ ተሰ 5:15)
25:_እርስ በርሳችሁ ተመካከሩ::(ዕብ 3:13)
26:_እርስ በርሳችሁ አትተማሙ::(ያዕቆ 4:11)
27:_እርስ በርሳችሁ በሐጥያታችሁ ተናዘዙ::(ያዕቆ 5:16)
28:_እርስ በርሳችሁ እንግድነትን ተቀባበሉ::(1ኛ ጴጥ 4:9)
29:_እርስ በርሳችሁ አገልግሉ::(1ኛ ጴጥ 4:10)
30:_እርስ በርሳችሁ እየተዋደዳችሁ ትህትናን እንደ ልብስ ታጠቁ::(1ኛ ጴጥ5:5)

#አምላካችን እንደ ቃሉ እንኖር ዘንድ
ፍቅር፣ሰላም አንድነትን ያድለን!!!

"የጌታ የእየሱስ ክርስቶስ ፀጋ የእግዚአብሔርም
ፍቅር የመንፈስ ቅዱስም ህብረት ከሁላችን ጋር ይሁን::አሜን
2ኛ ቆሮ 13:14

    #shear .....
Join @ortodoxslijoch