Get Mystery Box with random crypto!

በሕይወትህ በረከት እንዲበዛልህ አመስጋኝ ሁን! ”            በሕይወታችን ብዙ ል | ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ልጆች

በሕይወትህ በረከት እንዲበዛልህ አመስጋኝ ሁን! ”

          

በሕይወታችን ብዙ ልናሟላቸው የምንፈልጋቸው ነገሮች
ይኖራሉ። ጠቢቡ ሰለሞን በመጽሐፈ መክብብ 1:7 ላይ ሲናገር
" ፈሳሾች ሁሉ ወደ ባሕሩ ይሄዳሉ ባሕሩ ግን አይሞላም "
ይላል።

ይህም ምን ቢሰጠው የትኛውም ያህል ቢትረፈረፍለት
የሰው ልጅ ምኞትና ፍላጎት ማለቂያ የለውምና። እኛም ገንዘብ፤
ስራ፤ ፍቅር፤ ዝና፤ ስልጣን፤ በምኞት ቋጠሯችን ውስጥ
ካካበትናቸው ጥቂቶቹ ናቸው።
መመኘቱ ባልከፋ …..ነገር ግን ብዙዎቻችን የሌለንን ስንመለከት
ያሉንን ነገሮች ዓይን እንነፍጋቸዋለን ስለዚህ መጠየቅ እንጂ
ማመስገን ይሳነናል፤ በዚህም ሁልግዜ ጠያቂዎች እንጂ
አመስጋኞች አይደለንም። ልብ በሉ ምኞቶቻችን ሁሉ ሊሳኩ
የሚችሉት ባለን ነገሮች መጀመሪያ መደሰት እና ማመስገን
ስንጀምር ነው።

ለምሳሌ፦ አንድ ወዳጃችን በችግራችን ደርሶ ረዳን እንበል፤
ላደረገልን እርዳታ ምስጋና ካልሰጠነው እንዴት ብሎ በሌላ
ችግራችን ይደርስልናል?፤ አምላካችን እግዚአብሔርም
ላደረገልን ነገር ባመሰገንነው ቁጥር ሌሎች ልመናችንን ሰምቶ
በበረከት ላይ በረከት ያትረፈርፍልናል።

ስለዚህ ሁልግዜ
አመስጋኝ አንደበት ሊኖረን ይገባል።
ነገር ግን በምስጋና ፈንታ “በቂ ገንዘብ አላገኝም”፤ “ኑሮዬ
ምስቅልቅሉ የወጣ ነው” ፤ “መልካም የትዳር አጋር
አላገኘሁም”፤ “ስኬታማ አይደለሁም” " እግዚአብሔር
አይሰማኝም" የምንልና የምንማረር ከሆነ ያለንን ነገሮች
እንዳናይ ከማድረጋቸውም በላይ በረከታችንን የማራቅና ያለንም
በረከት ልናጣና ልንነጠቅ እንችላለን።
ብዙዎቻችን ግን ይህንን አንረዳም።

ለደቂቃ ልቦናችንን ሰብስበን
ካስተዋልነው እያንዳንዶቻችን በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ ብንሆን
እንኳን፤ ልናመሰግን የምንችልበት ብዙ ምክንያቶች አሉን።

እንደው ዋጋቸውን እያራከስን ነው እንጂ እያንዳንዶቻችን ሌሎች
የሚመኟቸው ነገሮች እኛ ጋር ዋጋ አጥተው ተቀምጠዋል።

ለምሳሌ፦ የአልጋ ቁራኛ የሆነ ሰው በህይወቱ የሚመኘው ነገር
ሙሉ ጤንነትን ሆኖ ሳለ፤ ጤነኛው ሰው ግን ስላለው ጤና
አለማመስገኑ አይገርምም?
ካስተዋልነው አንዲት ቃል ህይወታችንን በርግጥም

ትለውጣለች….. ለጠቢብ ሰው አንዲት ቃል ይበቃዋል ይባል
የለ በማቴዎስ ወንጌል 25:29 “ ላለው ሁሉ ይሰጠዋል
ይበዛለትማል…. ለሌለው ግን ያው ያለውም እንኳን
ይወሰድበታል” የሚለው ቃል የሚያስረዳን ሁላችንም ለተሰጠን
ማንኛውም መክሊት መጀመሪያ ምስጋና እናቅርብ ያኔ…ሌሎች
በረከቶቻችንን፣ ይመጣሉ።
እግዚአብሔርንም ስለሰጠን ነገር ሁሉ ካመሰገንነው ባለን ላይ
ሁሉ ለመጨመር አያመነታም ።

                    ሼር

      Join @ortodoxslijoch