Get Mystery Box with random crypto!

እመብርሃን መመኪያችን እመብርሃን መመኪያችን/2/ የአዳም ተስፋ አለኝታችን እመብርሃን መመኪያችን | ኑ እናመስግን

እመብርሃን መመኪያችን

እመብርሃን መመኪያችን/2/
የአዳም ተስፋ አለኝታችን
እመብርሃን መመኪያችን
አዝ-----
እመብርሃን የአባቶቻችን
እመብርሃን ቃና ለዛቸው
እመብርሀን በችግር ጊዜ
እመብርሀን መንገድ መሪያቸው
እመብርሃን ምን ብዬ ልጥራሽ
እመብርሃን ላወድስሽ
እመብርሃን የምግባር ደሀ
እመብርሃን ባዶ ልጅሽ
አዝ-----
እመብርሃን የቅዱሳኑ
እመብርሃን ጣዕመ ዜማቸው
እመብርሃን አንቺ ነሽና
እመብርሃን ውብ ድርሰታቸው
እመብርሃን የኛ ስጦታ
እመብርሃን የድል አክሊል
እመብርሃን ባማላጅነት
እመብርሃን ለታመነብሽ
አዝ-----
እመብርሀን የይስሀቅ መዓዛ
እመብርሃን በፍኖተ ሎዛ
እመብርሃን የያዕቆብ መሠላል
እመብርሃን የአቤል የዋኅት
እመብርሃን የዕሴ ቸርነት
እመብርሃን የኢያሱ ሐውልት
እመብርሃን የሕይወት ውሃ
እመብርሃን የሳሙኤል ዘይት
እመብርሃን ርግበ ሠናይት
እመብርሃን ንግሥተ ሠማይ
አዝ-----
እመብርሃን መልካሟ ርግብ
እመብርሃን የኖሕ መልክቱ
እመብርሃን የኅጥአን ተስፋ
እመብርሃን የልብ ብርታቱ
እመብርሃን ምስራቻችን
እመብርሃን ውስጣችን ያለሽ
እመብርሃን በምድር በሰማይ
እመብርሃን አምሳያም የለሽ

መልካም የፅጌ ፆም

@nu_enamasgin
@nu_enamasgin
@nu_enamasgin