Get Mystery Box with random crypto!

ስጦታ⚘ለሙስሊሟ 🎀🎁 እህቴ ሂዳያ ቲቪ ቀጥተኛዉ መገድ📚ተዉሂድ የሁለት ሀገር የስኬት ቁልፍ ነዉ📖⚘

የቴሌግራም ቻናል አርማ hidayatv — ስጦታ⚘ለሙስሊሟ 🎀🎁 እህቴ ሂዳያ ቲቪ ቀጥተኛዉ መገድ📚ተዉሂድ የሁለት ሀገር የስኬት ቁልፍ ነዉ📖⚘
የቴሌግራም ቻናል አርማ hidayatv — ስጦታ⚘ለሙስሊሟ 🎀🎁 እህቴ ሂዳያ ቲቪ ቀጥተኛዉ መገድ📚ተዉሂድ የሁለት ሀገር የስኬት ቁልፍ ነዉ📖⚘
የሰርጥ አድራሻ: @hidayatv
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.68K
የሰርጥ መግለጫ

#አላማችን ሙስሊሙን ኡማ ቀጥተኛዉን መገድ መምራት ነዉ
#ትክክለኛውን ኢስላማዊ አስተምህሮት
ከቁርዓንና📖 ከሐዲሥ
ከታማኝ ዑለማዎች የሚሰጡ
ሙሃደራወችና ኢስላማዊ ግጥሞች
የነብያትና የሶሀባ ታሪኮች
ለእናቶቻችና ለእህቶቻችን አስደሳች
ዲናዊ ንግግሮችና ፈትዋ ይቀርቡበታል
#እዲሁም_ወቅታዊ_ኢስላማዊ_ጉዳዮችም_ይዳሰሳሉ
#ለማንኛዉም_ጥያቄና_አስተያየት_ካላቹ
@iAm_musliym

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-09-01 20:04:07 ስጦታ⚘ለሙስሊሟ እህቴ ሂዳያ ቲቪ ቀጥተኛዉ መገድ ተዉሂድ የሁለት ሀገር የስኬት ቁልፍ ነዉ ⚘

ቻቱን አቁሚ እና አንድ ጊዜ ይህን ፅሁፍ አንብቢ ውዷ እህቴ



   ነብዩን ትወጃለሽ??? ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም 

መልስሽ" አዎ" እንደሚሆን ጥርጣሬ የለውም። ነገር ግን እህቴ እሳቸውን እወዳለሁ እያልሽ ለምን ነብያችን ከከለከሉሽ ነገሮች አትርቂም??

ለምሳሌ አለባበስን ብናይ በሚያሳዝን ሁኔታ ሙስሊም መሆኗን እንድንጠራጠር የሚያደርግ አለባበስ ነው የሚለበሰው!!!

ነብያችን ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም

"ፀጉሯን እንደ
#ግመል ሻኛ የቆለለች ሴት የጀነትን ሽታ አታገኝም" እያሉሽ አንች ግን #"ጀነቱ ቀርቶብኝ በዱንያ #ይመርብኝ " ነው ሚመስለው ነገርሽ ለምን አትተይውም ፀጉርሽን ከዃላ ከፍ የሚያደርግ ማጎፈሪያ ማስያዣ አትጠቀሚ አላህን ፍሪ እህቴ እሳት ለመዘውተር ምክኒያት ነውና!!

ሌላው ጆሮን
#እያወጡ ፀጉርን ደግሞ ከፊት ገለጥ እያደረጉ የሚለበስ አለባበስ ነው ምን ማለት እንደሆነ ግራ የሚያጋባ ነው እስኪ እንደዚ የምትለብሺ እህቴ ከማን ነው ያየሽው ከእናቶቻችን #አኢሻ#ኸዲጃ - - - - - የተማርሽው ነው? አደለም ወላሂ ወደ አላህ ተመለሺ ዱንያ ላይ #ያምርብሻል የሚሉሽ ሁሉ አኼራ ላይ ዞር ብለው አያዩሽም እና ለተፈጠርሽበት አላማ ቅድሚያ ስጪ!!!

አንች ማለት እኮ እህቴ
#ድንቅ እና  ውድ የሆንሽ የአላህ #ፍጡር ነሽ ኢስላም መገላለጥን ስለከለከለሽ #ተጨቆንኩ ብለሽ አታስቢ ምክኒያቱም #ኢስላም ከወንዶች ይልቅ አንችን ነው የበለጠ #ያከበረሽ በአንቺ ስም እኮ የአለማት ብርሃን የሆነው ምንም አይነት ስህተት የሌለው ቁርኣን ውስጥ ምእራፍ ተሰይሞልሻል ይሄ ላንቺ በቂሽ ነው ውዴ 

#ለምትጠፋ ዱኒያ #ዘላለማዊ
ህይወትሽን
#አታበላሽ



#ሼርር ለእህቶቻችን ታዳ ማንቂያ ይሆን ዘንድ
     አስታውሺ
➷ "ሀያዕ ከ ኢማን ነዉ
ይህ ምክሬ ላንቺ ለኔም  ነው"
ውዷ እህቴ ሆይ ተሸፈኚ

በሀያዕሽም ንግስት ሁኚ

【ምክር ለሙስሊሟ እህቴ➧

https://t.me/hidayatv
203 views ⚘يارب خفف ه‍مي ووجعي فاُنت وهحدك تحلم بحالي وم يجري بنفسي وك يو, 17:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 21:14:40 እንዲህ አይነትም ሰዋዊ ሰይጣኖች አሉና ሰሞኑን ተጠንቀቁ።

«Aselam Aleykum werahmetullahi weberekatu

ትላንት አመሻሽ ላይ ከቤት ሱቅ የተላከች ወጣት መንገድ ላይ መታወቂያ አሳይ ፍተሻ ነው ትባላለች::እንዳልያዘች እና ቤት ነው ስትል ትፈለጊያለሽ ተብላ አንዱ እያዋከበ ነጥሎ ይወስዳታል:: እሷም ወደ ፖሊስ ጣቢያ ሚወስዳት መስሏት ሳታንገራግር ትሄዳለች አሳቻ ቦታ ሲደርሱ ምት ይከተላታል መጨረሻ እራሷን ስታ ስትነቃ በደም ተጨማልቃ ተደፍራ ስውነቷ ቆሳስሎ  ፊቷ አባብጦ በልዞ እሯሷን አገኘችው::

ማታ ተረኛ ሆኜ ማክምበት ሆስፒታል ወላጆቿ ደም እንባ እያነቡ የነገሩኝ አስነዋሪ ድርጊት ነው::
ይህንን ቀውጢ ጊዜ እንደ አጋጣሚ ተጠቅሞ እንዲህ አይነት የእንስሳ ተግባር ሚፈፅሙ የሰው ህሊና የሌላቸው አረመኔዎች አሉና ሁሉም ጥንቃቄ ያድርግ::

አገራችንን ፈጣሪ ሰላም ያድርግልን::»

አንድ ወንድም በውስጥ የላከልኝ መልዕክት ነው። ምን አይነት እንስሳዎች ናቸው በአላህ!


እና ደግሞ መታወቂያ (የቀበሌ፣ መንጃ ፈቃድ፣ ፓስፖርት) እየያዛችሁ ጓዶች!
708 views ⚘يارب خفف ه‍مي ووجعي فاُنت وهحدك تحلم بحالي وم يجري بنفسي وك يو, 18:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 21:10:03
ከቻልክ ከሰዎችም በላይ ለአላህ የበለጠ ሐያእ ይኑርህ። ቢያንስ ግን ከሰዎች ሐያእ የምታደርገውን ያክል ሐያእ አድርግ። ሰዎች ፊት ለማድረግ የምታፍረውን ነገር አላህ ፊት እንደት ታደርጋለህ? መብራትም ይጥፋ፣ በሩም ይዘጋ፣ ከሰዎችም ተሰወር፤ ብቻ ግን በየትኛውም ሁኔታ ከአላህ እይታ በፍጹም አትሰወርም። አስተውል!
||
https://t.me/hidayatv
580 views ⚘يارب خفف ه‍مي ووجعي فاُنت وهحدك تحلم بحالي وم يجري بنفسي وك يو, edited  18:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 21:08:13
ዱዓህን አላህ እንዲቀበልህ ትሻለህ

ታላላቅ ዑለማዎች አላህን ከመጠየቅ ይልቅ አላህን ማስታወስን ያስበልጣሉ።

ለምን መሰላችሁ?
አላህን ካስታወስከው እንደት ይረሳሃል? «አስታውሱኝ፣ አስታውሳችኋለሁ!» ብሎን የለ!
ስለዚህ አንተ ካስታወስከው እርሱ አይረሳህምና፤ የሚያስፈልግህንና የሚጠቅምህን ነገር ካንተ በላይ ላንተ እርሱ ያውቃልና አንተ ባትጠይቀውም እርሱ ስለሚያውቅ ይሰጥሃል። አስታዋሹ ከሆንክ እንኳን ጠይቀኸው ባትጠይቀውም የልብህን፣ የውስጥህን ያውቃል።
‏( من أسباب استجابة الدعاء )

جاءت أم سُليم إلى النبي ﷺ فقالت:
ኡሙ ሱለይም ወደ ነቢያችን ﷺ ዘንድ መጣችና፤

يا رسول الله عَلِّمْنِي كَلِمَاتٍ أَدْعُو بِهِنَّ،
«አንቱ የአላህ መልዕክተኛ ሆይ! አላህን የምለምንበትን ቃካት አስተምሩኝ?» አለቻቸው፤
قال ﷺ:
"تُسبحين الله عَشْرًا، وتحمدينه عَشْرًا وَتُكَبِّرِينَهُ عَشْرًا، ثُمَّ أسالي حاجتك فَإِنَّهُ يَقُولُ:
قَدْ فَعَلْتُ، قَدْ فَعَلْتُ"
አላህን 10 ጊዜ ታጠሪያለሽ (ሱብሐነልሏህ)፣ 10 ጊዜ ታመሰግኒዋለሽ (አልሐምዱ ሊላህ)፣ 10 ጊዜ ታልቂዋለሽ (አላሁ አክበር)፣ ከዚያም ጉዳይሽን ጠይቂው። እርሱም «በርግጥ ፈጽሚያለሁ፣ በርግጥ ፈጽሚያለሁ!» ይላል።
- أخرجه الترمذي .
https://t.me/hidayatv
596 views ⚘يارب خفف ه‍مي ووجعي فاُنت وهحدك تحلم بحالي وم يجري بنفسي وك يو, edited  18:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 15:04:35 ┈┈•••✿❒ ❒✿•••┈┈

❒ አብደላህ ኢብን ዑመር ረዲደላሁ ዐንሁ

ክፍል አንድ

«የኢብን ዑመርን ያህል የነብዩን ፈለግ (ሱናን) የተከተለ ማንም የለም» {አዒሻ ረዲየላሀ ዐንሃ)

በመዲና እና በኡሁድ መካከል ባለዉ መንገድ ላይ በምትገኘዉ ሻይኻን፥ በነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ይመራ የነበረዉ አንድ ሺህ የሙስሊም ጦር ለሶላት ቆመ። ፀሃይ በአድማስ በታች መጥለቅ ጀምራለች።ነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ሳክብ ከተባለዉ ፈረሳቸዉ ላይ ወረዱ። የተሞላ የዉጊያ ልብስ አድርገዋል። በብረት ቆባቸዉ ላይ ጥምጣም ታስሯል። የደረት መከላከያ ልብስ (ጡሩር) አጥልቀዋል። ከሥሩ ደግሞ የሰይፋቸዉ ማንገቻ የታሠ ረበት የሆድ ዕቃ መከላከያ የብረት ልብስ (ጡሩር) አለ። በጀርባቸዉ ላይ አንድ ጋሻ ተሸክመዋል። ሰይፋቸዉ ከጎናቸዉ በኩል ተንጠልጥሏል። ፀሐይ እንደጠለቀች ቢላል አዛን አደረገና ሰገዱ።

┈┈•••✿❒❒✿•••┈┈

ከዚያም ነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ወታደሮቻቸዉን ለሁለተኛ ጊዜ ተዘዋዉረዉ ተመለከቱ። ምንም እንኳ ዕድሜያቸዉ አነስተኛ ቢሆንም በዉጊያዉ ላይ ለመካፈል የተመኙ ስምንት ልጆች በመካከላቸዉ መኖራቸዉን የተገነዘቡት በዚህ ጊዜ ነበር። ከእነሱ መካከል የዘይድ ልጅ ዑሳማህና የ ዑመር ልጅ አብደላህ ይገኙበት ነበር። ሁለቱንም የአስራ ሶስት ዓመት ልጆች ነበሩ። ሁሉም በአስቸኳይ ወደየቤታቸዉ እንዲመለሱ ነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም አዘዙዋቸዉ ። ከልጆቹ መካከል ሁለቱ ብቃት ያላቸዉ ተዋጊዎች መሆናቸዉን ስላሳዩ ወደ ኡሁድ ዉጊያ ከሚያመራዉ ጦር ሠራዊት ጋር አብረዉ እንዲሄዱ ሲፈቀድላቸዉ፥ ሌሎቹ ግን ወደየቤተሶቦቻቸዉ ተላኩ።

አብደላህ ኢብን ዑመር ረዲየላሁ ዐንሁ ገና በልጅነት ዕድሜዉ ነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በነበሩባቸዉ ግዳጆች ሁሉ ላለመለየት የነበራቸዉን ከፍተኛ ጉጉት ያሳዬዉ በእንዲህ አይነት ሁኔታ ነበር። ኢስላምንም የተቀበለዉ ገና አሥር አመት ሳይሞላዉ ነበር።
ከአባቱና የኀላኃላ የነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ባለቤት ከሆነችዉ ሃፍሷህ ረዲየላሁ ዐንሃ ከተባለች እህቱ ጋር ሂጅራህ አድርጓል (ተሰደዋል)።
ከኡሁድ በፊት ከበድር ጦርነትም እንዲ መለስ ተደርጎ ነበር። እሱና ኡሳማህ በዚያን ጊዜ ሁለቱም የአሥራ አምስት ዓመት ልጆች ሆነዋል።እንዲሁም በእነሱ ዕድሜ ክልል የሚገኙ ሌሎች ልጆች ለምሽግ ቁፋሮ ብቻ ሳይሆን ጊዜዉ ሲደርስ ለዉጊያም ጭምር ከሌሎቹ ሰዎች ረድፍ እንዲቀላቀሉ እስከ ምሽጉ ጦርነት ድረስ አልተፈቀደላቸዉም ነበር።

አብደላህ ኢብን ዑመር ረዲየላሁ ዐንሁ ሂጂራ ካደረገት ጊዜ አንስቶ ከ 70 ዓመት በላይ ቆይቶ እስከ ሞተበት ዕለት ድረስ ኢስላምን በማገልገል አቻ የለሽ ክብር ተጎና ጽፏል።

┈┈•••✿❒❒✿•••┈┈

አቡ ሙሳ አል-አሺዐሪይ እንዳሉት ከሆነ 《አብደላህ በሙስሊሞ ች ዘንድ «ጥሩና የጥሩ ሰዉ ልጅ »ተደርጎ ይታይ ነበር። በዕዉቀቱ ፣ በትህትናዉ ፣ በቸርነቱ፣ በመልካም ፀባዩ፣ በሃቀኝቱ፣ ከንቅዘት የፀዳ በመሆኑ እና በዒባዳዎች ላይ በነበረዉ ጽናቱ ይታወቃል። ከታላቁና እጅግ ከተከበሩ አባቱ ከዑመር ብዙ ተምሯል። ሁለቱም ከሁሉም በላይ ታላቅ መምህር ከነበሩት የአላህ መልእክተኛ-ሙሐመድ -የመማር ዕድል ተጠቃሚዎች ሆነዋል።


ነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በተለያዩ ሁኔታዎች ያደረጉት የነበረዉን እያንዳንዱ ንግግር ወይም ይፈፅሙት የነበረዉን ድርጊት አብደላህ በቅርብ ሆኖ ይከታተላል።
የተከታተለዉንም በትጋት ተግባራዊ ያደርግ ነበር። ነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በአንድ የተወሰነ ቦታ ላይ ሶላት ሲሰግዱ አይቶ ከሆነ፥ የኀላ ኀላ አብደላህ በዚያችዉ ቦታ ላይ ይሰግድባት ነበር። ነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ቁመዉ ዱዓ (ፀሎት) ሲያደርጉ አይቶ ከሆነ እሱም ቁሞ ዱዓ ያደርጋል።

በመንገድ ላይ ነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ከግመላቸዉ ላይ ወርደዉ ሁለት ረከዓ ሶላት ሲሰግዱ አይቶና በዚያዉ መንገድ የመሄድ ዕድል አጋጥሞት ከሆነ እዚያችዉ ቦታ ላይ ቆሞ ሁለት ረከዓ ይሰግዳል። አንድ ጊዜ መካ ዉስጥ በአንድ ቦታ ላይ ነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ከግመላቸዉ ላይ ወርደዉ ሁለት ረከዓ ከመስገዳቸዉ በፊት ግመሏ ሁለት ጊዜ ተሽከርክራ (ዞራ) ስትቆም ይመለከታል። በርግጥ ግመሏ ያንን ያደረገችዉን በአጋጣሚ ሊሆን ይችላል። አብደላህ ኢብን ዑመር ረዲየላሁ ዐንሁ በሌላ ጊዜ እዚያ ቦታ የመገኘት እድል ሲገጥመዉ ግን ግመሉ ተንበርክካላት ከመዉረዱ በፊት ሁለት ጊ ዜ እንድትሽከረከር ነበር ያደረጋት።

┈┈•••✿❒❒✿•••┈┈

ከዚያም ነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ሲያደርጉ ባየዉ ሁኔታ ዝንፍ ሳይል ሁለት ረከዓ ሰገደ። አዓሻ ረዲየላሁ ዐንሃ አብደላህ ኢብን ዑመር ረዲየላሁ ዐንሁ የነብዩ ሙሐመድን ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ፈለግ ለመከተልና ለመተግበር አቻ እንደማ ይገኝለት መስክራለች።

አብደላህ ረዲየላሁ ዐንሁ የነብዩን ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ተግባራት በቅርብ ሆኖ ሲከታተል የነበረ ይሁን እንጂ የእሳቸዉን ንግግሮች ሲዘግብ ግን ከፍተኛ ጥንቃቄ ከማድረግ አልፎ ይፈራም ነበር። አንዲት ሐዲሥ ይናገር የነበረዉ ቃል በቃል እንደሚያስተዉሳት ሙሉ በሙሉ እርግጠኛ ከሆነ ብቻ ነበር። «ከነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ሶሃባዎች (ባልደረቦች) መካከል፣ ከነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ሐዲስ ላይ ላለመጨመር ወይም ላለመቀነስ ከአብደላህ ኢብን ዑመር የበለጠ ጠንቃቃ ሰዉ ማንም አልነ በረም።» ሲል ከእሱ ዘመን ሰዎች መካከል አንደኛዉ መስክሮለታል።


https://t.me/hidayatv
752 views ⚘يارب خفف ه‍مي ووجعي فاُنت وهحدك تحلم بحالي وم يجري بنفسي وك يو, 12:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 21:03:11 الشيخ فوزان حفظه الله
እንድህ አሉ :-   ተንቢሀት ኪታባቸው ።

አንዳንድ ሴቶች ሂጃብ  በሚለበስበት ና በሂጃብ

ዙሪያ  አጥብቀው በሚለብሱ   ማህበረሰብ ዘንድ በሆኑ ግዜ   ይለብሳሉ።

ሂጃብ   በማይለብሱ ማህበረሰብ  በሆኑ ግዜ ደግሞ አይሸፈኑም ያወልቁታል።
ልክ አሁን ላይ ያሉ ሴቶች እንደሚያረጉት  

  ከሚሸፈኑት ውስጥ ደግሞ    ንግድ ቦታ : ወይ ሀኪም ቤት :   በገባች ጊዜ  ወይ አንድ

የጌጣ ጌጥ የሚሸጥን ።  ወይ አንድ የሴት ልብስ የሚሰፋን   በምታናግር ጊዜ  ፊቷን

ክንዷን  ትገለጣለች  ልክ ከባሏ ጋር ወይም ከሙህሪሟ ጋር እንደምትሆነው

ይህን የምታረጊ የሆንሽ አሏህን ፍሪ

በርግጥም ተመልክተናል  ከፊል  ሴቶችን

ከሌላ ሀገር ወደ ሳውድ የሚገቡትን    ከአውሮፕላን ሲወርዱጅ አይሸፈኑም ።

ሂጃብን በሸሪአ የተደነገገ ሳይሆን   ከተለምዶ አድርገው ይዘውታል 

አንቺ ሙስሊም እህቴ። ሆይ ሂጃብኮ  መርዛማ ከሆነ እይታዎች  ከበሽተኛ ልብና  ከሰው ውሻ    ይጠብቁሻል 
  የተቃጠለ ከሆነ ክጃሎት ይቆርጥልሻል  

አጥብቀሽ ያዥው   በሱም ላይ ሙጭኝ በይ

ሂጃብን ወደ ሚዋጉ ለሂጃብ ጸር ወደሆኑ አካላቶች አትዙሪ አትዘንበይ

እነሱ ሸርንጅ አይፈልጉልሽም ልክ الله سبحنه وتعلا እንዳለው

وَاللَّهُ يُرِيدُ أَن يَتُوبَ عَلَيْكُمْ وَيُرِيدُ الَّذِينَ يَتَّبِعُونَ الشَّهَوَاتِ أَن تَمِيلُوا مَيْلًا عَظِيمًا (27) سوره النساء
አላህም በእናንተ ላይ ጸጸትን ሊቀበል ይሻል፡፡ እነዚያም ፍላጎታቸውን የሚከተሉት (ከውነት) ትልቅን መዘንበል እንድትዘነበሉ ይፈልጋሉ፡፡
====================
https://t.me/hidayatv
427 views ⚘يارب خفف ه‍مي ووجعي فاُنت وهحدك تحلم بحالي وم يجري بنفسي وك يو, 18:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 19:26:31 የደሴና የኮምቦልቻ ባንኮች
-------
ህዝቡን አታሸብሩት፣ ገንዘቡን እናንተ ጋር ያስቀመጠው በቸገረው ቀን ሊጠቀምበት እንጂ በቸገረው ሰዓት  ፊታችሁን ልታዞሩበት አይደለም። አሰራራችሁና ለደህንነት ብላችሁ የዘየዳችሁት ብልሃት የህዝብን አደራ ለመጠበቅ ከሚያግዝ ይልቅ ህዝቡ እንዳይረጋጋ፣ አንዳች ያለወቀው ከባድ ጉዳይ የመጣ እንዲመስለው፣  ላልተፈለገ ወጭ እንዲዳረግና ጠላት ይሄንኑ ማህበራዊ አለመረጋጋት ጥቅም ላይ እንዲያውለው እድል የሚሰጥ ነው። በመሆኑም ውሳኔያችሁን ከልሱ፣ አሰራራችሁ ወቅታዊውን ሁኔታ መሰረት አድርጎ የደንበኞቻችሁን ችግር የሚፈታ ይሁን።

የየከተሞቹ አስተዳደሮች ጉዳዩ ለአለመረጋጋትና ማህበራዊ ቀውስ ቁልፍ ምክንያት ስለሆነ ከባንክ አስታዳዳሪዎች ጋር በቅርብ ይነጋገሩበት።
136 views ⚘يارب خفف ه‍مي ووجعي فاُنت وهحدك تحلم بحالي وم يجري بنفسي وك يو, 16:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 16:51:54 ሰማይ የቱንም ያህል ርቆ ብታየንም
ከሰማዩ በላይ ያለው የዐርሹ ባለቤት ጌታችን ግን እጅግ በጣም ቅርባችን ነው።
507 views ⚘يارب خفف ه‍مي ووجعي فاُنت وهحدك تحلم بحالي وم يجري بنفسي وك يو, edited  13:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 16:25:38 የገጠር ሰዎችን አትጸየፉ፣ አትናቁ፣ ሙድ አትያዙባቸው። በነርሱና በናንተ መካከል ያለው ሰፊ ልዩነት የተቀደደና ያልተቀደደ፣ ንጹሕ የሆነና ያልሆነ ልብስ፣ የተሻለ ምግብና መጠጥ መኖርና አለመኖር እንጂ በንጹሕ ልቦናና በጎነት ከሆነ ግን ብዙዎች ከተሜውን ይቦንሱታል።

እውነት ለመናገር በስመ ከተሜነትና ዘመናዊነት/ፋሽን የብዙዎች ቀልብ የሌለ ቆሽሿል። የነርሱ ልብስ በሳሙና አንድ ጊዜ ከታጠበ ይጠራል። የኛ በወንጀል የቆሸሸች ልብ ግን በተደጋጋሚ በትክክለኛ ተውበት ካልታጠበች ይዛን እንዳትጠፋ ያሰጋል።

ምናልባትም አላህ ዘንድ ከኛ የተሻለ ቦታ ይኖራቸዋልና ስለነርሱ ባለን አመለካከት ላይ ሚዛናዊ እንሁን።


አላህ ደግሞ ወደ አካላዊ ገፅታችንና ቁሳዊ ነገሮች ሳይሆን የሚመለከተው ወደ ቀልባችንና ሥራችን ነው።

قالَ رَسُولُ اللهِ ﷺ «إِنَّ الله لا يَنْظُرُ إِلى أَجْسامِكْم، وَلا إِلى صُوَرِكُمْ، وَلَكِنْ يَنْظُرُ إِلَى قُلُوبِكُمْ»


{ وَمِنَ ٱلۡأَعۡرَابِ مَن یُؤۡمِنُ بِٱللَّهِ وَٱلۡیَوۡمِ ٱلۡـَٔاخِرِ وَیَتَّخِذُ مَا یُنفِقُ قُرُبَـٰتٍ عِندَ ٱللَّهِ وَصَلَوَ ٰ⁠تِ ٱلرَّسُولِۚ أَلَاۤ إِنَّهَا قُرۡبَةࣱ لَّهُمۡۚ سَیُدۡخِلُهُمُ ٱللَّهُ فِی رَحۡمَتِهِۦۤۚ إِنَّ ٱللَّهَ غَفُورࣱ رَّحِیمࣱ }
https://t.me/hidayatv
565 views ⚘يارب خفف ه‍مي ووجعي فاُنت وهحدك تحلم بحالي وم يجري بنفسي وك يو, edited  13:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 15:50:59 መ.6 አላህንና መልዕክተኛውን በመታዘዝና ትዛዛቸዉን በመከተል እንወዳቿለን. ከፍ ያለው አላህ እንዲህ ይላል: “በላቸው: አላህን የምትወዱ ከሆነ, ተከተሉኝ: አላህ ይወዳቿል ለናንተ ወንጃላቹንም ይምራቿል: አላህ መሃሪ እና አዛኝ ነው". (ሱራህ አል-ዒምራን 3:31)
የአላህ መልዕክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል: “ አንዳቹ አላመነም እኔ ከልጆቹ ከወላጆቹ እንዲሁም ከሰው ልጆች በሙሉ የበለጠ እሱን ዘንዳ የተወደድኩ እስካልሆነ ድረስ. ” (ቡኻሪ እና ሙስሊም ዘግበውታል

س٧ - : هَلۡ نَتۡرُكُ الۡعَمَلَ وَنَتَّكِلُ عَلَىالۡقَدَرِ ؟

ج٧ - : لَا نَتۡرُكُ الۡعَمَلَ لِقَوۡلِهِ تَعَالَى: ﴿ فَأَمَّا مَنۡ أَعۡطَىٰ وَٱتَّقَىٰ ۝ وَصَدَّقَ بِٱلۡحُسۡنَىٰ ۝ فَسَنُيَسِّرُهُۥ لِلۡيُسۡرَىٰ ﴾ (سورة الليل).
وَقَوۡلِهِ ﷺ: (اعۡمَلُوا فَكُلٌّ مُيَسَّرٌ لِمَا خُلِقَ لَهُ) (رَوَاهُ الۡبُخَارِيُّ وَمُسۡلِمٌ).

.7 ስራ መስራትን ትተን በቀደር እንመካለንን?

መ.7 ስራ መስራትን ትተን በቀደር አንመካም ምክንያቱም ከፍ ያለው አላህ እንዲህ ይላል: “ የሰጠ የሆነ ሰው, አላህንም የፈራ, በመልካም ነገርም ሰደቃን የሰጠ ለመልካም ነገር የተገራ እናረገዋለን" (ሱራህ አልለይል 92:5-7)
የአላህ መልዕክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል: “መልካምን ነገር ስሩ, ሁሉም ለተፈጠረላት ነገር የተገራ ነው." (ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል)

ይቀጥላል........
https://t.me/hidayatv
405 views ⚘يارب خفف ه‍مي ووجعي فاُنت وهحدك تحلم بحالي وم يجري بنفسي وك يو, 12:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ