Get Mystery Box with random crypto!

┈┈•••✿❒ ❒✿•••┈┈ ❒ አብደላህ ኢብን ዑመር ረዲደላሁ ዐንሁ ክፍል | ስጦታ⚘ለሙስሊሟ 🎀🎁 እህቴ ሂዳያ ቲቪ ቀጥተኛዉ መገድ📚ተዉሂድ የሁለት ሀገር የስኬት ቁልፍ ነዉ📖⚘

┈┈•••✿❒ ❒✿•••┈┈

❒ አብደላህ ኢብን ዑመር ረዲደላሁ ዐንሁ

ክፍል አንድ

«የኢብን ዑመርን ያህል የነብዩን ፈለግ (ሱናን) የተከተለ ማንም የለም» {አዒሻ ረዲየላሀ ዐንሃ)

በመዲና እና በኡሁድ መካከል ባለዉ መንገድ ላይ በምትገኘዉ ሻይኻን፥ በነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ይመራ የነበረዉ አንድ ሺህ የሙስሊም ጦር ለሶላት ቆመ። ፀሃይ በአድማስ በታች መጥለቅ ጀምራለች።ነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ሳክብ ከተባለዉ ፈረሳቸዉ ላይ ወረዱ። የተሞላ የዉጊያ ልብስ አድርገዋል። በብረት ቆባቸዉ ላይ ጥምጣም ታስሯል። የደረት መከላከያ ልብስ (ጡሩር) አጥልቀዋል። ከሥሩ ደግሞ የሰይፋቸዉ ማንገቻ የታሠ ረበት የሆድ ዕቃ መከላከያ የብረት ልብስ (ጡሩር) አለ። በጀርባቸዉ ላይ አንድ ጋሻ ተሸክመዋል። ሰይፋቸዉ ከጎናቸዉ በኩል ተንጠልጥሏል። ፀሐይ እንደጠለቀች ቢላል አዛን አደረገና ሰገዱ።

┈┈•••✿❒❒✿•••┈┈

ከዚያም ነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ወታደሮቻቸዉን ለሁለተኛ ጊዜ ተዘዋዉረዉ ተመለከቱ። ምንም እንኳ ዕድሜያቸዉ አነስተኛ ቢሆንም በዉጊያዉ ላይ ለመካፈል የተመኙ ስምንት ልጆች በመካከላቸዉ መኖራቸዉን የተገነዘቡት በዚህ ጊዜ ነበር። ከእነሱ መካከል የዘይድ ልጅ ዑሳማህና የ ዑመር ልጅ አብደላህ ይገኙበት ነበር። ሁለቱንም የአስራ ሶስት ዓመት ልጆች ነበሩ። ሁሉም በአስቸኳይ ወደየቤታቸዉ እንዲመለሱ ነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም አዘዙዋቸዉ ። ከልጆቹ መካከል ሁለቱ ብቃት ያላቸዉ ተዋጊዎች መሆናቸዉን ስላሳዩ ወደ ኡሁድ ዉጊያ ከሚያመራዉ ጦር ሠራዊት ጋር አብረዉ እንዲሄዱ ሲፈቀድላቸዉ፥ ሌሎቹ ግን ወደየቤተሶቦቻቸዉ ተላኩ።

አብደላህ ኢብን ዑመር ረዲየላሁ ዐንሁ ገና በልጅነት ዕድሜዉ ነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በነበሩባቸዉ ግዳጆች ሁሉ ላለመለየት የነበራቸዉን ከፍተኛ ጉጉት ያሳዬዉ በእንዲህ አይነት ሁኔታ ነበር። ኢስላምንም የተቀበለዉ ገና አሥር አመት ሳይሞላዉ ነበር።
ከአባቱና የኀላኃላ የነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ባለቤት ከሆነችዉ ሃፍሷህ ረዲየላሁ ዐንሃ ከተባለች እህቱ ጋር ሂጅራህ አድርጓል (ተሰደዋል)።
ከኡሁድ በፊት ከበድር ጦርነትም እንዲ መለስ ተደርጎ ነበር። እሱና ኡሳማህ በዚያን ጊዜ ሁለቱም የአሥራ አምስት ዓመት ልጆች ሆነዋል።እንዲሁም በእነሱ ዕድሜ ክልል የሚገኙ ሌሎች ልጆች ለምሽግ ቁፋሮ ብቻ ሳይሆን ጊዜዉ ሲደርስ ለዉጊያም ጭምር ከሌሎቹ ሰዎች ረድፍ እንዲቀላቀሉ እስከ ምሽጉ ጦርነት ድረስ አልተፈቀደላቸዉም ነበር።

አብደላህ ኢብን ዑመር ረዲየላሁ ዐንሁ ሂጂራ ካደረገት ጊዜ አንስቶ ከ 70 ዓመት በላይ ቆይቶ እስከ ሞተበት ዕለት ድረስ ኢስላምን በማገልገል አቻ የለሽ ክብር ተጎና ጽፏል።

┈┈•••✿❒❒✿•••┈┈

አቡ ሙሳ አል-አሺዐሪይ እንዳሉት ከሆነ 《አብደላህ በሙስሊሞ ች ዘንድ «ጥሩና የጥሩ ሰዉ ልጅ »ተደርጎ ይታይ ነበር። በዕዉቀቱ ፣ በትህትናዉ ፣ በቸርነቱ፣ በመልካም ፀባዩ፣ በሃቀኝቱ፣ ከንቅዘት የፀዳ በመሆኑ እና በዒባዳዎች ላይ በነበረዉ ጽናቱ ይታወቃል። ከታላቁና እጅግ ከተከበሩ አባቱ ከዑመር ብዙ ተምሯል። ሁለቱም ከሁሉም በላይ ታላቅ መምህር ከነበሩት የአላህ መልእክተኛ-ሙሐመድ -የመማር ዕድል ተጠቃሚዎች ሆነዋል።


ነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በተለያዩ ሁኔታዎች ያደረጉት የነበረዉን እያንዳንዱ ንግግር ወይም ይፈፅሙት የነበረዉን ድርጊት አብደላህ በቅርብ ሆኖ ይከታተላል።
የተከታተለዉንም በትጋት ተግባራዊ ያደርግ ነበር። ነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በአንድ የተወሰነ ቦታ ላይ ሶላት ሲሰግዱ አይቶ ከሆነ፥ የኀላ ኀላ አብደላህ በዚያችዉ ቦታ ላይ ይሰግድባት ነበር። ነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ቁመዉ ዱዓ (ፀሎት) ሲያደርጉ አይቶ ከሆነ እሱም ቁሞ ዱዓ ያደርጋል።

በመንገድ ላይ ነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ከግመላቸዉ ላይ ወርደዉ ሁለት ረከዓ ሶላት ሲሰግዱ አይቶና በዚያዉ መንገድ የመሄድ ዕድል አጋጥሞት ከሆነ እዚያችዉ ቦታ ላይ ቆሞ ሁለት ረከዓ ይሰግዳል። አንድ ጊዜ መካ ዉስጥ በአንድ ቦታ ላይ ነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ከግመላቸዉ ላይ ወርደዉ ሁለት ረከዓ ከመስገዳቸዉ በፊት ግመሏ ሁለት ጊዜ ተሽከርክራ (ዞራ) ስትቆም ይመለከታል። በርግጥ ግመሏ ያንን ያደረገችዉን በአጋጣሚ ሊሆን ይችላል። አብደላህ ኢብን ዑመር ረዲየላሁ ዐንሁ በሌላ ጊዜ እዚያ ቦታ የመገኘት እድል ሲገጥመዉ ግን ግመሉ ተንበርክካላት ከመዉረዱ በፊት ሁለት ጊ ዜ እንድትሽከረከር ነበር ያደረጋት።

┈┈•••✿❒❒✿•••┈┈

ከዚያም ነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ሲያደርጉ ባየዉ ሁኔታ ዝንፍ ሳይል ሁለት ረከዓ ሰገደ። አዓሻ ረዲየላሁ ዐንሃ አብደላህ ኢብን ዑመር ረዲየላሁ ዐንሁ የነብዩ ሙሐመድን ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ፈለግ ለመከተልና ለመተግበር አቻ እንደማ ይገኝለት መስክራለች።

አብደላህ ረዲየላሁ ዐንሁ የነብዩን ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ተግባራት በቅርብ ሆኖ ሲከታተል የነበረ ይሁን እንጂ የእሳቸዉን ንግግሮች ሲዘግብ ግን ከፍተኛ ጥንቃቄ ከማድረግ አልፎ ይፈራም ነበር። አንዲት ሐዲሥ ይናገር የነበረዉ ቃል በቃል እንደሚያስተዉሳት ሙሉ በሙሉ እርግጠኛ ከሆነ ብቻ ነበር። «ከነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ሶሃባዎች (ባልደረቦች) መካከል፣ ከነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ሐዲስ ላይ ላለመጨመር ወይም ላለመቀነስ ከአብደላህ ኢብን ዑመር የበለጠ ጠንቃቃ ሰዉ ማንም አልነ በረም።» ሲል ከእሱ ዘመን ሰዎች መካከል አንደኛዉ መስክሮለታል።


https://t.me/hidayatv