Get Mystery Box with random crypto!

ዕዉቀትን ተግባራዊ ማድረግ! እያንዳንዱ ቀን የየራሱ የሆነ አስተምህሮ አለዉ መምህሩም መድሃኒታች | ንቁ'የመዳን ቀን ዛሬ ነዉ!

ዕዉቀትን ተግባራዊ ማድረግ!


እያንዳንዱ ቀን የየራሱ የሆነ አስተምህሮ አለዉ መምህሩም መድሃኒታችን ነዉ አዳዲስ ቀኖች የሚሰጠንም ዉስጣችን የተሰገሰገዉን ክፋቶች ወደ እግዚአብሔር ቀርበን እያራገፍን የቅድስና ሕይወትን እየተላበስንና አዲስ ማንነትን እየተቀዳጀን እንድንሄ የሚሰጠን ዉድና ዳግም የማይገኝ ዕድል ነዉ። የሰዉ ልጅ ቁስ ነገር ቢጠፋበት በተመሳሳይ ቁስ ነገር ሊተካዉ ይችላል ነገር ግን ከዕድሜዉ ላይ አንዲት ቀን በከንቱ ብትቀነስበት ይህችን ቀን ዳግም ተመልሶ ሊያገኛት አይችልም ጊዜ ወደፊት የሚገሰግስ እንጂ ወደኋላ የሚሄድ አይደለምና ዉድና ተመልሶ ማግኘት የማይቻል ነገር ቢኖር እግዚአብሔር እንለዉጥበት ዘንድ የሰጠን ጊዜ ነዉ። አብዛኛዉ ጊዜ ያኔ እንዲህ አድርጌ በነበረ እየተባለ በቁጭት የሚወራዉ ያለፈ ጊዜን ዳግም ማግኘት ስለማይቻለን ነዉ። እግዚአብሔር አዲስ አዲስ ቀን የሚሰጠን ከክፋታችን ተመልሰን ከዛሬ ነገ የተሻለ ስብዕናን ተላብሰን ወደ እርሱ እንመለስ ዘንድ ነዉ እንጂ ዕድሜአችንን በከንቱ ለከንቱ ነገር እንድናባክነዉ አይደለም። መምህራችን እግዚአብሔር አንድን ፅሑፍ እንድናነብ አልያ ስብከት እንድናዳምጥ የሚያደርገን ያለ አንዳች ምክንያት አይደለም። እዛ ፅሑፍና ስብከት ዉስጥ አንዳች ድክመታችን ላይ ነቅተን በዛ ድክመታችን የእርሱን እርዳታ ጠይቀን ነጻ እንድንወጣ እንጂ ምጽ የእኔ ችግር እያልን መልዕክቱን እንድንዘለዉ አልያ የፀሐፊዉንና የሰባኪዉን ጠንካራ ጎንና ደካማ ጎን እያወጣን እያወረድን እንድንተችና እንድናሞካሽ አይደለም። ሊቁ ዮሐንስ አፈወርቅ አስተምሮዬ የእናንተን ሕይወት የማይለዉጥ ከሆነ የእናንተ ጭብጨባና እልልታ ምንም አያደርግልኝም እንዳለዉ። ጊዜ ወስዳችሁ የምታነቡትን ፅሑፍና የምትሰሙት ስብከት በሕይወታችሁ ለዉጥ ሳያመጣ እንዲሁ ዕዉቀት ብቻ ሆኖ በአእምሮአችሁ ብትይዙት ምንም ሊጠቅማችሁ አይችል። እግዚአብሔር ይሄንን ፅሑፍ እንዳነበና ይሄንን ስብከት እንድሰማዉ የፈለገዉ ምን ሊያስተምረኝ ፈልጎ ነዉ ብላችሁ ሊያነቃችሁ በፈለገዉ ነገር ላይ ቶሎ ነቅታችሁ ለዛ ደካማ ጎናችሁ መፍትሔ ከእርሱ በመጠየቅ ሕይወታችሁ ዉስጥ ለዉጥ እንዲመጣ ማድረግ አለባችሁ እንጂ አዉቃችሁ የእኔ ችግር እያላችሁ አልያ አድናቆት ሰጥታችሁ እንድታልፉ አይደለምና ወደ ሕይወታችሁ በሚመጣዉ መልዕክት ዉስጣችሁን ፈትሹ መድሃኒታችንን እሩቅ ፈላጊ አትሁኑ ልክ ከቀደምቶቻችን ጋር ቅርብ ለቅርብ ሆኖ እያስተማረና እየገሰጸ ቀጥተኛዉን መንገድ እንዳሳየቸዉ ሁሉ የእኛ ሕይወት ዉስጥም ቅርባችን ሆኖ በየዕለቱ ወደ ተስፋይቱ ምድር የሚወስደንን መንገድ እያስተማረ ይመራናልና እሩቅ አትፈልጉት ደግሞ በገሃዱ ዓለም
የሚል…አልወጣኝም በመንፈስ ማለቴ እንጂ



ልብ በሉ፥ እየተቸገርን ያለነዉ አንዳች አንቂ መልዕክት ወደ ሕይወታችን ሲመጣ ተግባራዊ ማድረግ ሳይሆን ዕዉቀት ብቻ አድርገን ስለምናልፋቸዉ ነዉ። ዕዉቀት ተግባራዊ ካልሆነ ሕይወት ዉስጥ ለዉጥ አይመጣም እንደምናየዉ ወንጌልን አዉቀን በሕይወት ኑሮ ተግባራዊ ባለማድረጋችን ነዉ አንድ ሊሆን የሚገባዉ ምግባራችን ልዩ ልዩ ሆኖ የቀረዉ። ዕዉቀት ብቻዉን ቆንጆ ተናጋሪ አድርጎ ሕይወትን መንፈሰ ቢስ ሲያደርግ ዕዉቀትን በሕይወት ኑሮ ተግባራዊ ማድረግ ደግሞ ሕይወትን አስዉቦ መንፈሰ ሙሉ ያደርጋል ከሁሉም በላይ በሰማይ ያለዉ አባታችሁን ያመሰግኑት ዘንድ እንዲሁ ብርሃናችሁ በሰዉ ፊት ይብራ። እንዳለ የመፅሐፍ ቃል እግዚአብሔር አምላካችን በእኛ እንዲመሰገን ያደርጋል። ማቴ፤5፤16 መተዉ ያለባችሁን ጉስቁልና እንድትተዉ የተሰጣችሁ ቀንና ጊዜ በከንቱ እንዲባክን አትፍቀዱለት ጊዜ አጥፍታችሁ ለማንበብ ሆነ ለመስማት ስትቀመጡ የሆነ ነገር ተምራችሁ ዕዉቀትን ተግባራዊ በማድረግ ራሳችሁን ለመወጥ መሆን አለበት እንጂ መረጃ ብቻ ለመሰብሰብ አይሁን። የሰዉ ልጅ ራሱን ማንበብና ዉስጡን ማዳመጥ ከቻለ በሕይወቱ ብዙ ለዉጥ ማምጣት ይችላል። የክርስትና ሕይወት እንዲሁ እንደሚወራዉ ቀላል አይደለም ክርስትናን ማወቅና ክርስትናን ተግባራዊ አድርጎ በሕይወት ኑሮ መኖር የሰማይና የምድር ያህል ልዩነት አላቸዉ ወንጌል በሕይወት ትገለጥ ዘንድ ዕዉቀትን ተግባራዊ ማድረግ ተለማመዱ።

@Nkuyemedankenzare