Get Mystery Box with random crypto!

የጾም ጥቅም! ምግብ ሲበዛ ለአደጋ ያጋልጣል መኪና ፍሬኑን ሲበጥስ መንገድ ስቶ ወደ ገደል እንደሚ | ንቁ'የመዳን ቀን ዛሬ ነዉ!

የጾም ጥቅም!

ምግብ ሲበዛ ለአደጋ ያጋልጣል መኪና ፍሬኑን ሲበጥስ መንገድ ስቶ ወደ ገደል እንደሚገባዉ ሁሉ የሰዉ ልጅም ለሥጋ ምቾቱ አድልቶ እየበላና እየጠጣ የሚኖር ብቻ ከሆነ ለተራበና ለተቸገረ የማያዝን፥ ለሰዉ ክብር የሌለዉ ሰዉነትን በቁስ ነገር የሚለካ፥ አምላኩን በአፍ እንጂ ከቶ የማያዉቅ ፍጥረት ይሆንና በሥጋ ስለ ሥጋ ብቻ የሚኖር ስለሚሆን የመጾም ጥቅሙ እየበላዉና እየጠጣዉ በምቾት ልኑር የሚለዉን የሥጋ ፈቃድ ስለሚገታ ለተራበ፥ ለተጠማ ለተቸገረ ሰዉ እንድናዝን ያደርገናል ማለት ነዉ፥ በነገሬ ላይ የሰዉ ልጅ ክፉና ጨካኝ የሚሆነዉ ነፍስ በኀጢአት አዘቅጥ ዉስጥ ወድቃ እንስሳዊ ባሕሪዉ ጎልቶ ሲወጣ ነዉ ( የሥጋ ፈቃድ ነፍስ ላይ ሲሰለጥን ማለት ነዉ) መሰረታዊ የጾም ጥቅሙ ደግሞ በነፍስ ጽድቅን ያሰጣል፥ ከእግዚአብሔር ጋር ያስታርቃል። ልብ በሉ፥ መጾም የሚከብዳችሁ በረከተ እግዚአብሔር ስለሚርቃችሁ ነዉ። መድሃኒታችን እግዚአብሔር ሰይጣን ካቀረበለት ፈተናዎች አንዱ ድንጋዩን ዳቦ አድርግ የሚል የስስት ፈተና ሲሆን መድሃኒቱም መልሶ የሰዉ ልጅ ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣዉ ቃል እንጂ በእንጀራ ብቻ አይኖርም ብሎ የዲያቢሎስን ፈተና ድል እንደነሳል ሁሉ ማቴ፤4 ጾም የሚጾመዉ በምግብ ኀይልና በራስ አቅም ሳይሆን በእግዚአብሔር ቸርነትና እርዳታ ነዉና አስቀድማችሁ በምግብ ኀይልና በራሳችሁ አቅም እንደምትጾሙ ማሰባችሁን ከአእምሮአችሁ አዉጥታችሁ በእርሱ ቸርነት እንደምትጾሙ አስባችሁ መጾም አለባችሁ መድሃኒታችን የማይችሉትን አቅመ ደካሞችን ብርቱ የሚያደርግ እጹብ ድንቅ አባት ነዉና በእርሱ ተመርኩዛችሁ ጹሙ። ስትጾሙም የረሀብ አድማ ራሳችሁ ላይ አዉጃችሁ መመገብ ሳይሆን በፈቃዳችሁ ተርባችሁ ያለ ፈቃዱ እየተራበ ያለዉን ወንድማችሁን እየመገባችሁ መሆን አለበት።

@Nkuyemedankenzare