Get Mystery Box with random crypto!

ያለ እርሱ'……! አንዳንድ በሽታ በባሕሪዉ ሰዉን የማታለል ልምድ አለዉ በዚህ ባሕሪዉ ገሚሱን በዝ | ንቁ'የመዳን ቀን ዛሬ ነዉ!

ያለ እርሱ"……!

አንዳንድ በሽታ በባሕሪዉ ሰዉን የማታለል ልምድ አለዉ በዚህ ባሕሪዉ ገሚሱን በዝምታ እንደ ምስጥ ዉስጥ ዉስጣቸዉን ቦርቡሮ ከጨረሳቸዉ በኋላ እስከወዲያኛዉ ከዚህ ዓለም እንዲሰናበቱ ያደገርጋቸዋል ገሚሱን ደግሞ ቀለል ያለ ሕመም በማስከተል በማደንዘዣ ኪኒን ሰዉነት ዉስጥ ይደበቅና በዝምታ አስከፊ ደረጃ ላይ አድርሶ ሰዉነትን ካዳከመ በኋላ የሕመም ምልክት ማሳየት ይጀምራል በዚህ ጊዜ ወደ ሕክምና ሲኬድ ይሄ በሽታ መጥፎ ደረጃ ከመድረሱ የተነሳ ዋጋ የሚያስከፍል ሆኖ ይገኛል ታዲያ በእንዲህ ዓይነት በሽታ የተጠቁ ሰዎች የበሽታዉን አስከፊነትና ከምን ዓይነት አደጋ እንደተረፉ የሚረዱት የተሰጣቸዉን መድሃኒት በአግባቡ ወስደዉ ፈዉስ ካገኙ በኋላ ነዉ። አስተዉል ወዳጄ፥ ብዙሃኖቹ ኀጢአቶች እንደዚሁ በሽታ ፍጹም መንፈሳዊ አስመስለዉ በዝምታ ሰዉነትን ዉስጥ ዉስጡን በክፋት ጠርቀዉ በማሰር ዘለዓለማዊነትን የሚያሳጡ ናቸዉ፤ እንዲህ ዓይነቱ ኀጢአቶች ከሰዉነት ጋር ተዋህደዉ ጠባይ መስለዉ የሚደበቁ ስለሆኑ ያለ ቅዱስ ቁርባን በጾም ጸሎት ብቻ ድምጻቸዉን አያሰሙም የእነዚህ ኀጢአቶች አስከፊነት እግዚአብሔር የልብና የኩላሊትን አሳብ የማያዉቅ አስመስለዉ በማደንዘዝ ለእግዚአብሔር ታማኝ አገልጋይ እንዳንሆን ክርስትናን ለታይታና የይስሙላ እንድንኖረዉ የሚያደርጉ የክፋት ዓይነቶች ናቸዉ።



መድሃኒቱ! ፦ እናንተ ጻፎችና ፈሪሳዉያን በዉስጡ ቅሚያንና ስስትን ተሞልቶ ሳለ የጽዋዉንና የወጭቱን ዉጭ ስለምታጥቡ ወዮላችሁ! እንዳለ
ማቴ፤23፤25



እንደዚህ ዓይነቱ ኀጢአቶች ዉስጥን አጥቁረዉ ከላይ አሳምረዉ በሰዉ ዘንድ ጻድቅ በማስመሰል ከንቱ የሆነ ምስጋናን የሚያስጎናጽፉ የኀጢአት ዓይነቶች ናቸዉ። እነዚህ ኀጢአቶች በቅዱስ ቁርባን ኀይል እንጂ በትሩፋት ብቻ የሚላቀቁን አይደሉም ምክንያቱም ጠባይን መስለዉ ትኩረት የማይስቡ የኀጢአት ዓይነቶች ስለሆኑ ያለ ቅዱስ ቁርባን ክፋት መሆናቸዉን እንኳን ለይተን ልናዉቃቸዉ አይቻለንም እንደሚታወቀዉ መድሃኒታችን ዘንድ ደግሞ ሰዋራዉ ሁሉ ግልጥ ስለሆነና ከእርሱ የሚሸሸግ ልሸሸግ ቢልም የሚቻለዉ አንድም ነገር ስለሌለ ከእርሱ ጋር ሕብረት ፈጥረን ስንኖር ብቻ ነዉ ከተሸሸጉበት መንቀሳቀስ የሚጀምሩት እንጂ ጠባይ መስለዉ ከሰዉነት ጋር የሚኖሩ የክፋት ዓይነቶች ናቸዉ ታዲያ የእነዚህን ኀጢአቶች አስከፊነት ተረድታችሁ ከምን ዓይነት መከራ እንዳመለጣችሁና ክፋት መሆናቸዉን የምትረዱት ቅዱስ ቁርባን ደግማችሁ ደጋግማችሁ ስትቀበሉ ብቻ ነዉ። አስተዉሉ! ለእንዲህ ዓይነቱ ኀጢአቶች ጾምና ጸሎቱ ልክ እንደ ማደንዘዣ ኪኒን ይሆናቸዋል እንጂ ፍቱን መድሃኒት ሆነዉ ከዉስጣችን ሊያራግፉልን አይቻላቸዉም ቅዱስ ቁርባን ዘለዓለማዊነትን ከማቀዳጀት አልፎ ዉስጣችን ተሰዉሮ የተሰገሰገዉን እያንዳንዱን ክፋት እያራገፈ ክርስትናን ወደ ምድር እንድናወርድ የሚያደርግ ነዉ፡፡ ወዳጄ፥ ያለ ቅዱስ ቁርባን ክርስትናን ወደ ምድር አወርዳለዉ ብለህ አታስብ የማይቻል ነገር ነዉና ከመንፈስ ፍሬዎች ለመመደብ የግድ ቅዱስ ቁርባን ያስፈልጋል፡፡ ገላ፤5፤22 በእርሱና ስለእርሱ የምንኖረዉ ከመድሃኒቱ ጋር ሕብረት ስንፈጥር ብቻ ነዉ። ዮሐ፤6፤56 የሰዉ ልጅ በማስተዋልና ጥበብ ተደግፎ ከክፋት እየተጠበቀ መኖር የሚቻለዉም ወደ ቅዱስ ቁርባን ቀርቦ አስመሳይ ከሆነ የጠላት ሴራ ሲያመልጥ ብቻ ነዉ መፅሐፈ ጥበብ፤10፤10-14 ሙሉን ምዕራፍ ብታነቡት……! ያለ እርሱ በድንግዝግዙ ሕይወትን ለመምራት መገደድ ይመጣልና ዉስጥ ዉስጡን እረፍት ከሚነሳችሁ አሰልቺ ክፋቶች ታርፉ ዘንድ በክፍያ ሳይሆን በነፃ ወደ ተሰጣችሁ ቅዱስ ቁርባን መቅረብ አስፈላጊ ነዉ። መድሃኒታችን እግዚአብሔር ከሕመምና ስቃይ አሳርፎ ዘለዓለማዊነትን ለማቀዳጀት እንደ ዓለም ሕክምና ረብጣ ብር አልጠየቀም እርሱ የጠየቀዉ አንድ ነገር ብቻ እርሱም እናንተ ደካሞች ወደ እኔ ኑ የሚል መስፈርት ነዉ ማቴ፤11፤28 መልካም የሆነ ሕክምናን ለማግኘት የሚፈልግ ወደ ሐኪሙ ቀርቦ መታከም ብቻ ነዉ የሚጠበቅበት ምናልባት በስግደት በጸሎት የሥጋ ፈዉስ ሆነ ሌሎች መልካም ነገሮች ሊገኝ ይችላል እርሱ ግን በቂ አይደለም፥ ወሳኙ ነገር ለምድራዊ ነገር መጨነቅ ሳይሆን ሰማያዊ ሕይወትን መላበስ ነዉ። ሌላዉ አንድ ክርስቲያን የሚያደርገዉን ነገር ለምንና ለማን እንደሚያደርግ በሥጋ ዕዉቀት ሳይሆን በነፍስ ዕዉቀት አዉቆ የሚያደርግ መሆን አለበት እንጂ አድርግ ስለተባለ የሚያደርግ ሂድ ስለተባለ የሚሄድ ና ስለተባለ የሚመጣ ወደ ነፈሰበት የሚነፍስ መሆን የለበትምና የነፍስ ዕዉቀት ይገኝ ዘንድ በቅዱስ ቁርባን መታተም አስፈላጊ ነዉ። በተጨማሪም፤ ክርስቲያን የመድሃኒታችን እግዚአብሔርን ፍቅር ምን ያህል እንደሆነ በታሪክ አዋቂ ሆኖ ሊቀመጥ የሚገባዉ ሳይሆን በሕይወት ኑሮዉ ፍቅሩን እያጣጣመ ሊኖር ይገባዋልና ቅዱስ ቁርባን እጅጉኑ አስፈላጊያችን ነዉ።
አዎ፦ያለ እርሱ ክፋት እንደሆኑ የማይታወቁ ነገር ግን ክፋት የሆኑ እንደ ጠባይ የሚታዩ ቁጥር የማይገድባቸዉ ሰዋራ ክፋቶች አሉና ወደ እርሱ ቀርቦ መታከሙ እጽብ ነዉ!'። በነገሬ፥ በተደጋጋሚ እንደሚወሳዉ ቅዱስ ቁርባን ጾም ጸሎትና ስግደት የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታዎች ናቸዉ ለዚህም ምስክሬ የታመነዉ ቃል ነዉ። ማቴ፤8፤1-13 ቁጥ፤ 28-34 ማቴ፤9፤18-34 ማቴ፤12፤9-37 ማቴ፤15፤21-28 ማቴ፤17፤14-23 በዚህም ስለዚህም ያለ መለያየት በአንድነት እንጠቀምባቸዉ ዘንድ ይገባናል!
ያለ እርሱ በእርሱና ስለእርሱ መኖር አይቻለንምና ወደ እርሱ እንቅረብ!።

@Nkuyemedankenzare