Get Mystery Box with random crypto!

ግብረ ሰዶማዊነት የሚስፋፋበት ሚስጢራዊ መንገድ፡ ግለ ወሲብ፥ የሰዉ ልጅ ከእንስሳ | ንቁ'የመዳን ቀን ዛሬ ነዉ!

ግብረ ሰዶማዊነት የሚስፋፋበት ሚስጢራዊ መንገድ፡

ግለ ወሲብ፥


የሰዉ ልጅ ከእንስሳ የሚለየዉ ማሰብ በመቻሉ ነዉ ምክንያቱም ከየት እንደመጣችና ወዴት እንደምትመለስ የምታዉቅ ሕያዊት የሆነች ረቂቅ ነፍስ በዉስጡ ስላለች ማለት ነዉ፡ ይህቺ ነፍስ በኀጢአት ቆሽሻ በጨለማ ስትዋጥ ሰዉ የተባለዉ ፍጡር አእምሮዉ ይጠብና ሆዱ ይሰፋል አእምሮ ወደ ሆድ ተቀየረ ማለት ደግሞ ሰዉ ለመብልና ለመጠጥ ለልብስና ለዉበት ለሀብትና ንብረት በሥጋ ስለ ሥጋ ብቻ የሚጨነቅ እኔ ባይ ሆኖ በመንጋ የሚጓዝ ይሆናል፡ እንደምናየዉ ፍቅር ጠፍቶ አንዱ አንዱን ለማጥፋት ደፋ ቀና የሚል የበዛዉ አእምሮ ጠቦ ሆድ ስለሰፋ ነዉ፡ እንስሳ ሰዉ ወደ መራዉ እንደሚጓዝ ሁሉ ሕሊናም በኀጢአት ቆሽሾ ሲጨልም ዲያቢሎስም ሰዎችን በመንጋ ወደ ፈለገዉ አቅጣጫ ይመራ ማለት ነዉ። በረከቱ ይደረብንና ሐዋሪያዉ ቅ•ጴጥሮስ በ1ኛ መልዕክቱ ምዕ፤5፤8 ላይ በመጠኑ ኑሩ ንቁም ባላጋራችሁ ዲያቢሎስ የሚዉጠዉን ፈልጎ እንደሚያገሳ አንበሳ ይዞራልና፡ ሲል ያስጠነቀቀን ሆድ ሲሰፋ አእምሮ ስለሚጠብ ነዉ። የጥንቶቹ ቅዱሳን ከመድሃኒቱ ጋር ሕብረት ፈጥረዉ በመጠኑ በመኖራቸዉ ከሰማያዊዉና ምድራዊ በረከት ተካፋይ ሆነዉ የሰዉን ሥጋ ተገን አድርጎ ዉጊያ የሚከፍትባቸዉን የጠላትን ሴራ እያፈራረሱ የመድሃኒቱ አባትነትና ክብር በእነርሱ ላይ ከፍ ብሎ ታይቶ ስልጣኔን ለዓለም አስተዋዉቀዉ በክብር ወደ መጡበት ተመልሰዋል ከመድሃኒቱ ጋር ሕብረት መፍጠር ያልፈለገዉ ትዉልድ ደግሞ ስልጣኔ መርዝ ሆኖበት የነፍስ ሟቲ ሆኖ ቀረ፥ ልብ በሉ! ስልጣኔ ያመጣብንን ጉዳት ደጋግሜ ሳወሳችሁ ስልጣኔ አያስፈልገነም ማለቴ አይደለም ያስፈልገናል ግን የእግዚአብሔር ሕብረት የሌለበት ስልጣኔ የሞት ሞት ስላመጣብን ንቁና ከመድሃኒቱ ጋር ሕብረት ፈጥራችሁ መርዙን ወደ ወተት ለዉጡት ነዉ የምላችሁ እንጂ ስልጣኔ አያስፈልገነም አላልኩም እንደምታዩት ከመድሃኒቱ ጋር ሕብረት ፈጥረን የምንጠቀምበት ስልጣኔ'ማ እኔና እናንተን በቀላሉ እያማማረን ነዉ፥ አዎ ወዳጄ መድሃኒቱ ጣልቃ ያልገባበት ስልጣኔ ተንቀሳቃሽ የቁም ሟቲ አድርጎናልና መንቃት ያስፈልገናል፡



ቀደምቶቻችን በጠዋት ተነስተዉ ምግብ አያዉቁም ጸሎት እንጂ ሲሰሩ ዉለዉ ተመግብዉ መተኛት አያዉቁም ጸሎትና ስግደት እንጂ ፈተና ሲያጋጥማቸዉ ወደ ሰዉ መሮጥ አያዉቁም ወደ እግዚአብሔር እንጂ እኔና እናንተስ ከእንቅልፋችን እንደነቃን ቁርስና ከfb'ና Tg ከTwitter'ና Instagram ከYouTube'ና tiktok ላይ መረጃ መሰብሰብ ይታየናል እንጂ በጸሎትና በስግደት ለመድሃኒቱ መገዛት አያስፈልገነም ከሰዓታት በኋላ ደግሞ ተጨማሪ ምሳ ያስፈልገናል ለጥቆ ቀኑን በስራ ስላሳለፍን እራትና የተለያዩ ድህረ ገጾችን እየጎበኘን አእምሮን ዘና ለማድረግ (motivation) ንግግሮች ያስፈልገናል እንጂ በጸሎትና ስግደት መድሃኒቱን ማመስገን አያስፈልገንም ስለዚህ? ስለዚህማ ሆድ ሲሰፋ አእምሮ ጠበበና ሰማያዊዉና ምድራዊዉ ሚስጢረ ነገር ተሰወረብን ብናነብ የማይገባን ብንማር የማይገባን እየሰማን የማንሰማ እያየን የማናይ ስንሆን ጊዜ እንስሳዊ ባሕሪያችን ከፍ አለና ዝሙትና እርኩሰት ነገሰብን ማለት ነዉ በዚህም ምክንያት 95 ከመቶ ታማሚሆች ነን ችግሩ የነፍስ ሕመምተኛ መሆናችንን አምኖ መቀበሉ ላይ ነዉ እንጂ።



ወደ መነሻዉ መንገዴ ልመለስና ሰዶማዊነት በአዉሬዉ ዘመን መብት ሆኖ ይከበራል በምዕራቡ ዓለም ይሄ እርኩሰት ፍቃድ አግኝቶ ተግባራዊ ሆኗል በሀገራችንም በግልጥ ሳይሆን በድብቅ ዉስጥ ዉስጡን በመስፋፋት ላይ ይገኛል፥ በነገሬ ላይ አዉሬ እየተባለ የሚጠራዉ የሰዉ ልጅ ነዉ እንጂ ሌላ ነገር አይደለም በመጨረሻዉ ዘመን እኔ ክርስቶስ ነኝ ብሎ የሚመጣዉ ሀሳዊ መሲህ ነዉ አበዉ ይሄ ሀሳዊ መሲህ ከኤሳዉ ነገድ እንደሚወለድና ስሙም መርመርምያኖስ እንደሚባል እያንዳንዱን ነገር በዝርዝር አስቀምጠዉልናል፡ ያዉ እኛ ከመድሃኒቱ ጋር ሕብረት ስለሌለን ብዙ ነገሮች ተሰዉሮብና እንጂ ወደ ሀሳቤ ልመለስና ግብረ ሰዶማዊነት ባለፈዉ ክፍል ላይ እንደገለጥኩት አእምሮ ያላቸዉ የሚመስሉ ግን ፈፅሞ አእምሮ የሌላቸዉ ሰዎች ተግባር ነዉ ይሄ እርኩሰት ከሚስፋፋባቸዉ መንገዶች አንዱ ግለ ወሲብ ነዉ ግለ ወሲብ በልዩ ልዩ መንገዶች ይጀመራል' ልቅ በሆነ በቃላት ልዉዉጥ፥ የወሲብ ፊልም በመመልከት፥ የወሲብ ፍላጎት ቀስቃሽ በሆኑ ፅሑፎችን በማንበብ፥ ወሊድ መቆጣጠሪያ በሚል ሰበብ፥ አላስፈላጊ በሆኑ (picture'ሮችን) በመመልከት፥ በአቻ ለአቻ ግፊት' ከማህፀን በሚቆራኙ መናፍስቶችና ወዘተረፈ ……በብዙ መንገዶች ግለ ወሲብ ይጀመራል፤



ልብ በሉ! እርኩሳን መናፍስት ሥጋና አጥንት ስለሌላቸዉ አይጨበጡም አይዳሰሱም አይታዩም ስለዚህ እርኩሰትን ለሰዉ ልጆች ለማለማመድ የግድ ግዙፉ አካል ያስፈልጋቸዋል ዘፍ፤3 ማቴ፤24፤37-40 ማለት ነዉ። ከዚህ እርጉም ጋር ሕብረት ያላቸዉ የእርሱ መንገድ ጠራጊ የሆኑትን የምዕራባዊያንን ሥጋ ሽፋን በማድረግ በረቀቀ ስልቱ እርኩሰትን ለሰዉ ልጆች እያስተማረ የሲኦልን ነፍሳት ያበዛል ማለት ነዉ። ታዲያ ግለ ወሲብንም ሲያለማምድ አስቀድሞ ሰፊ ስራዉን የሚሰራዉ አእምሮ ላይ ነዉ እርግዝና እንዳይፈጠር ግለ ወሲብ መፍትሔ ነዉ፡ ወደፊት ትዳር ሲመስርቱ በሥጋ ሩካቤ ጊዜ እንዳይቸገሩ ግለ ወሲብ ያስፈልጋል የወሲብ ፍላጎት ቀስቃሽ ልቅ የሆነ ቃላት ልዉዉጥና ፅሑፎችን መላላክ እርድና ነዉ፡ ለስንፈተ ሩካቤ ወሲብ ቀስቃሽ የሆኑ ምስሎችን መመልከት ተገቢ ነዉ ነገሩን በጭፍኑ ከክፉ (angle) ሆነ ስንመለከተዉ ልክ የሚመስል ግን ልክ ያልሆነ በዉስጣቸዉ ገዳይ መርዝን የያዙ ናቸዉ። ይሄ እርኩሰት እግዚአብሔርን የሚያስቆጣዉ ሲልም የሞት ቅስፈት የሚያስከትል ዘፍ፤38፤8-10 ምግባር መሆኑን ጠላታችን ያዉቀዋል ስለዚህ አስቀድሞ አእምሮን አደንዝዞ ነገሮችን እርሱ ከሚያሳየን አቅጣጫ ብቻ እየተመለከትን እግዚአብሔርን ያሳዝነዉ አያሳዝነዉ ሳንመረምር በጭፍኑ ዘዉ ብለን የዲያቢሎስ ወጥመድ ዉስጥ ጥልቅ እንላለን እዚህ ጋር ሕዝቤዉ ዕዉቀት ከማጣቱ የተነሳ ጠፍቷል የሚለዉ የመፅሐፍ ቃል ተግባራዊ ሲሆን እናገኛለን ሆሴዕ፤4፤6፡፡ መፅሐፍን የመመርመር ዕድል ቢኖረን ሁሉም ነገር በግልጥ እናገኘዉ ነበር' አብዛኛዉ ወጣት ሆነ ባለትዳር ግለ ወሲብን አቅልለዉ ከጀመሩ በኋላ ከገቡበት ገደል መዉጣት የሚያቅታቸዉ ዲያቢሎስ አእምሮን አስቀድሞ ስለሚመርዝ ነዉ፡፡ የግለ ወሲብ ሱሰኛ የሆነ ሰዉ ከዚህ ጸያፍ ምግባር በንስሀ ታጥቦ በቅዱስ ቁርባን ታትሞ ወደ እግዚአብሔር ካልተመለሰ የወደፊት እጣ ፈንታዉ ግብረ ሰዶም መሆን ነዉ ምክንያቱም ግለ ወሲብ ከቃሉ እንደምንረዳዉ ከራስ ጋር የሚደረግ ጸያፍ እግዚአብሔር የሚጠላዉ ምግባር ነዉ በዚህ እርኩሰት የተጠመዱ ብዙሃኖች ከተቃራኒ ጾታ ጋር የሥጋ ሩካቤ መፈጸም አይፈልጉም ምክንያቱም ከራሳቸዉ ጋር የሚፈጽሙት እርኩሰት የሚሰጣቸዉን ደስታ ከተቃራኒ ጾታ ጋር የሚፈጽሙት የሥጋ ሩካቤ ደስታ ስለማይሰጣቸዉ ማለት ነዉ። አንዳንዶቹ ደግሞ በዚህ ሱስ ተጠምደዉ ከነጭራሹ ከተቃራኒ ጾታ የሚሸሹ ቤት ይቁጠራቸዉ ይሄ የሚያመልክተን ዲያቢሎስ ሰዎችን ለሰዶማዊነት እንዴት እያዘጋጃቸዉ እንደሆነ ነዉ ምዕራባዊያን ከ16 ዓመት በላይ ለሆኑት ታዳጊዎች የግለ ወሲብ ትምህርትን በሰፊዉ እየሰጡ እንደሆነ በድህረ ገጻቸዉ ላይ በዝርዝር አስፍረዋል ይሄንን ጸያፍ ምግባር በዓመት ለ1.2 million ሰዎች ማስተማር እንዳለባቸዉ አልፈዉ ተርፈዉም በማዕረግ እንደሚያስመርቁም ይናገራሉ፡