Get Mystery Box with random crypto!

ይሄ ሁሉ ልፋትና ድካም ያስፈለጋቸዉ በመጨረሻዉ ዘመን (the new world order) የአዲሱን | ንቁ'የመዳን ቀን ዛሬ ነዉ!

ይሄ ሁሉ ልፋትና ድካም ያስፈለጋቸዉ በመጨረሻዉ ዘመን (the new world order) የአዲሱን ዓለም መንግስት ስርዓት መስርተዉ ዓለምን ጠቅልለዉ ለዲያቢሎስ ለማስገዛት ስለሚፈልጉና ቀጣዩም (generation) በቀላሉ ለዲያቢሎስ እንዲገዛ ከወዲሁ ኀጢአተ ሰዶምን በዓለም ለማስፋፋት ሲሉ በረቀቀ ስልታቸዉ አሳማኝ በሆነ በዉሸት ቃላት እርኩሰትን እያለማመዱ ስለሆነ ነዉ. 1.2 million ሰዉ በዚህ እርኩሰት ተጠመደ ማለት የዓለም የሕዝብ ቁጥርም በዚያዉ ልክ ይቀንሳል ማለት ነዉ ያዉ እንግዲህ ዲያቢሎስ የአዳም ዘር እንዲበዛ ስለማይፈልግ በረቀቀ ስልቱ በአንድም በሌላም እያደረገ የሕዝብ ቁጥርን እንዲቀን ለማድረግ ጠንክሮ ይሰራል ማለት ነዉ፡ ይሄ ስልቱ ሰፊ ዝርዝር ስላለዉ እመለስበታለዉ።



የግለ ወሲብ ጥገኛ መሆን የሚያስከትለዉ ጉዳት፡



የግለ ወሲብ ጥገኛ የሆነ ሰዉ በሰዉነት ዉስጥ ያለዉን ፕሮቲንና ካልሲየም እንዲቀንስ በማድረግ አቅመ ደካማ ያደርገዋል፡ ለስንፈተ ወሲብ ያጋለጣል፡ፈጣን ንቃተ ሕሊና ያሳጣል ድብርት ዉስጥ ያስገባል ያፈዛል ያደንዝዛል፡ የማስታወዝ አቅም ያዳክማል ከሰዎች ጋር መግባባት እንዳንችል ያደርጋል ብቸኝነትን እንድናዘዉትር ያደርጋል ሱስ በመሆን ሕይወትን ይቆጣጠራል፡ ከተቃራኒ ጾታ ያሸሻል፡ የወንዱ የዘር ፈሳሽ እንዲቀንስ በማድረግ ለፅንስ አዳጋች ያደርጋል፡ የበታችነት ስሜትን ስለሚያስከትል በሆነዉ ባልሆነ ተነጫናጭ ያደርጋል፡ ወዘተረፈ ልዩ ልዩ ጉዳቶች ያስከትላል፥ አስተዉሉ! ዲያቢሎስ ማለት አተርፍ ባይ አጉዳይ ነዉ ክብርና ከፍታን ሲፈልግ የነበረዉን ክብር ተገፎ ወደ ታች ወርዶ ከክብሩ ተዋርዷል ይሄ ትዕቢቱ ከዉድቀት ሊያነሳዉ አልቻለም ዛሬም ቀጥሎበት የእግዚአብሔር የሆነዉን ለመዉሰድ ይታትራል እንደማይሆንለት እያወቁ እንኳን ተስፋ የማይቆርጥ ጨለምተኛ ነዉ ባላጋራ ነዉና በአንድም በሌላም ሰዎችን ሲቆራኝ ይሄን ባሕሪዉን ስለሚያዋርስ ሰዎችም ኀጢአት ሲሰሩ የተሻለ ነገር አገኛልዉ በሚል አስተሳሰብ እርኩሰትን ይጀምሩና መዉጫ የሌለዉ ገደል ሲሆንባቸዉ ተስፋ ቆርጠዉ ጨለምተኛ ሕይወት ለመምራት ይገደዳሉ። አብዛኞች ግለ ወሲብ የሚጀምሩት አተርፍ ባይ ሆነዉ ነዉ የባሰ አዘቅጥ ዉስጥ ከገቡ በኋላ ሕይወት ከባድ ሲሆንባቸዉ የማይሆን እርምጃ እራሳቸዉ ላይ ለመዉሰድ የሚገደዱት በዚህ ጸያፍ ምግባር ተጠምደዉ ሱስ ከሆነባቸዉ በኋላ ከዚህ ሕይወት ዉስጥ መዉጣት አቅቷቸዉ ሀፍረተ ሥጋቸዉ ላይ ጉዳት እስከማድረስ የደረሱ ሰዎች አሉ፡ራሳቸዉን እስከማጥፋት የሚደርሱ አሉ፡ ግብረ ሰዶም የሆኑ አሉ፡ ወዳጄ፥ እግዚአብሔር አምላካችን ካለመኖር ወደ መኖር የሚያመጣን በእኛ ሊከብር በእኛ ሊመሰገን ነዉና ወደ እርሱ ቀርበን ከእርኩሰት ልንላቀቅ እጅጉኑ ያስፈልገናል እርሱ ለምን በደልከኝ አይልም ብትበድልም አፍቃሪ አባትህ ነኝና ወደኔ ቅረብና ጠላትህን ድል ልንሳልህ ይለናል እንጂ ለምን ኀጢአት ሰራቹ ብሎ አይተወንም በዉኑ ኀጢአተኛ ይሞት ዘንድ መፍቀድን እፈቅዳለሁን? ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር፤ ከክፉ መንገድ ይመለስ በሕይወት ይኖር ዘንድ ነዉ እንጂ ሕዝ፤18፤23 የፈለገዉን ያህል በኀጢአት ብንቆሽሽ ከነቁሻሻችን ተቀብሎ ከበረዶ ይልቅ የሚያነጣን መዝ፤51፤7 እጽብ አባት አለንና ልንሸማቀቅ አያስፈልገነም ብቻ ወደ እርሱ ከነድካማችሁ ቅረቡ ሌላዉ ዝሙት ሰዉ ላይ የሚሰልጥነዉ ምግብ ሲበዛና ሥጋ ሞቾት ሲበዛበት ነዉና ሳታቋርጡ በአቅማችሁ የአምልኮ ስግደት ስገዱ ጸልዩ ጹሙ ለጥቆ በንስሀ ታጥባችሁ በቅዱስ ቁርባን ታተሙ መፍትሔዉ ነዉ! ወጥነት ያለዉ መንፈሳዊ ዉጊያ ከተገበራችሁ ከየትኛዉም የኀጢአት አዘቅጥ ዉስጥ መዉጣት ትችላላችሁ ብቻ የአምልኮ ስግደት አታቋርጡ ጸሎት አታቋርጡ በምትችሉት ጹሙ በንስሀ ታጥባችሁ እየቆረባችሁ ከመድሃኒቱ ጋር ሕብረት ፍጠሩ ድሉ የእናንተዉ ነዉ፡፡

ይቀጥላል…

@Nkuyemedankenzare