Get Mystery Box with random crypto!

በምድር ያለዉ ማደሪያ ቤታችን ቢፈርስም በሰማይ በእግዚአብሔር ዘንድ የሰዉ እጅ ያልሰራዉ ዘለዓለማዊ | ንቁ'የመዳን ቀን ዛሬ ነዉ!

በምድር ያለዉ ማደሪያ ቤታችን ቢፈርስም በሰማይ በእግዚአብሔር ዘንድ የሰዉ እጅ ያልሰራዉ ዘለዓለማዊ ቤት እንዳለን እናዉቃለን ስለ እርሱ የምንደክምለትን በሰማይ ያለዉን ቤታችንን እንለብስ ዘንድ እርሱን ተስፋ እናደርጋለን። ከለበስነዉም በኋላ ዕራቁታችንን የምንገኝ አይደለንም። በዚህ ቤት ዉስጥ ሳለንም ከከባድነቱ የተነሳ እጅግ እናዝናለን ነገር ግን ሟች በሕይወት ይዋጥ ዘንድ ሌላ ልንለብስ እንጂ ልንገፈፍ አንወድም ለዚህም ያዘጋጀን እግዚአብሔር ነዉ እርሱም የመንፈስ ቅዱስን ፈለማ ሰጠን። እንግዲህ ሁልጊዜ እመኑ ጨክኑም በዚህ ሥጋ ሳላችሁም እናንተ እንግዶች እንደ ሆናችሁ ታዉቃላችሁ ከሥጋችሁ ተለይታችሁ ወደ ጌታችን ትሄዳላችሁ በእምነት እንኖራለን በማየትም አይደለም ታምነናል ይልቁንም ከሥጋችን ተለይተን ወደ ጌታችን እንሄዳለንና ደስ ይለናል አሁንም ብንኖርና ብንሞትም እርሱን ደስ ለማሰኘት እንጥራለን መልካም ቢሆን ክፉም ቢሆን በሥጋችን እንደ ሠራነዉ ዋጋችንን እንቀበል ዘንድ ሁላችን በክርስቶስ የፍርድ ዙፋን ፊት እንቆማለን።
2ኛቆሮ፤5፤1-10 ንስሀ መግባትን አንዘንጋ።

@Nkuyemedankenzare