Get Mystery Box with random crypto!

በባህርዳር ከተማ የአልሙኒየም ፎርምወርክ ቴክኖሎጂ ለመጀመሪያ ጊዜ በመጠቀም ዘመናዊ የመኖሪያ ህንፃ | The Niles ናይል 🇪🇹

በባህርዳር ከተማ የአልሙኒየም ፎርምወርክ ቴክኖሎጂ ለመጀመሪያ ጊዜ በመጠቀም ዘመናዊ የመኖሪያ ህንፃ ሊገነባ ነው

ለግንባታው የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን እና የአማራ ክልል ቤቶች ልማት ደርጅት የግንባታ ማመከር ውል ስምምነት ፈፅመዋል
~~~~~~

የአማራ ክልል ቤቶች ልማት ደርጅት በባህርዳር ከተማ በክልሉ ለመጀመሪያ ጊዜ አዲስ የሆነውን  የአልሙኒየም ፎርምወርክ ቴክኖሎጂን በመጠቀም ለሚያስገነባው ዘመናዊ የመኖሪያ ሕንጻ ግንባታ ዛሬ ከፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ጋር የግንባታ አማካሪነት ውል ተፈራርመዋል።

ስምምነቱን የፈዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ክቡር አቶ ረሻድ ከማል እና የአማራ ቤቶች ልማት  ደርጅት ዋና ዳይሬክተር አቶ አበረ ሙጨ ተፈራርመዋል፡፡

በስምምነቱ መሰረት የአማራ ቤቶች ልማት ደርጅት የአልሙኒየም ፎርም ቴክኖሎጂ በመጠቀም ለሚያስገነባው የግንባታ ፕሮጀክት የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ሙሉ የማመከር ሥራ የሚያከናውን ይሆናል፡፡

የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ረሻድ ከማል  እንዳሉት ኮርፓሬሽኑ በቤት ልማት ኢንዱስትሪ ይበልጥ በግምባታ እና ማማከር ዘርፍ ግንባር ቀደም ለመሆን እየሰራ ይገኛል። ባለፉት አራት አመታት የለውጥ ስራዎችን በመተግበር በጊዜ ፣ በጥራት እና በብዛት ውጤታማ የሆኑ የቤት ግምባታዎችን ማከናወን መቻሉን ተናግረዋል።

ስኬታማ ተሞክሮውን በማስቀጠል የአማራ ቤቶች ልማት ደርጅት በሁሉም መስፈርቶች የተሻሉ  ዘመናዊ የመኖሪያ ቤት ፕሮጀክቶችን እንዲገነባ ኮርፖሬሽኑ ድጋፍ እንደሚያደርግ ነው ዋና ሥራ አስፈጻሚው አቶ ረሻድ ተናግረዋል።


የአማራ ቤቶች ልማት ደርጅት ዋና ዳይሬክተር አቶ አበረ ሙጨ በበኩላቸው የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ለአማካሪ  መስፈርቶችን ያሟላና ውጤታማ የፕሮጀክት አስተዳደርና አመራር ልምድ ያካበተ ተቋም በመሆኑ አብሮ ለመስራት መምረጣቸውን ተናግረዋል ።፡

ኮርፖሬሽኑ በአዲስ አበባ ከተማ የአልሙኒየም ፎርምወርክ ቴክኖሎጂን በስፋት በመጠቀም በ18 ወራት ግዙፍ የመኖሪያ መንደር በመገንባት ያገኘው ተሞክሮ ለእኛም ኘሮጀክቶች ስኬታማነት ወሳኝ ነው ብለዋል።

በቀጣይም የአማራ ቤቶች ልማት ድርጅት ከፕሮጀክት ማመከር በዘለለ ከፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ጋር በትብብር እንደሚሰራም ተገልጿል።