Get Mystery Box with random crypto!

'ዲፕሎማቶች የተሰጠንን ተልዕኮ በብቃት በመተግበር ሀገር በማዳን እንቅስቃሴ ውስጥ ኃላፊነታችን | The Niles ናይል 🇪🇹

"ዲፕሎማቶች የተሰጠንን ተልዕኮ በብቃት በመተግበር ሀገር በማዳን እንቅስቃሴ ውስጥ ኃላፊነታችን መወጣት ይገባናል።"
ክብርት አምባሳደር ብርቱካን አያኖ
_________________________________________________________
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሰራተኞችና ተጠሪ ተቋማት በወቅታዊ አገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አድርገዋል።

በውይይቱ ላይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት አምባሳደር ብርቱካን አያኖ ሁሉም ሰራተኞች ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የኢትዮጵያን እውነታ እንዲገነዘብ በማድረግ ለሀገራቸው ሁለተናዊ ተሳትፎ በማድረግ የበኩላቸውን ድርሻ መወጣት አለባቸው ብለዋል፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አምባሳደር ተስፋዬ ይልማ በበኩላቸው የኢትዮጵያ መንግስት ለሰላማዊ መፍትሄ ረጅም ርቀት መጓዙን ማስረጃዎችን በማቅረብ ያብራሩ ሲሆን፤ ለአሁኑ ግጭትም ህወሃት መንስኤ መሆኑን ጠቅሰዋል። መንግሥት በአፍሪካ ህብረት ማዕቀፍ ስር ለሚደረግ ድርድር ዝግጁ መሆኑንምጠቁመዋል

ለውይይቱ የመነሻ ጽሑፍ ያቀረቡት የውጭ ጉዳይ ኢንስቲቲዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ጃፋር በድሩ በበኩላቸው ህወሓት የጦርነት አማራጭ መርጦ ለሦስተኛ ጊዜ ግጭት መቀስቀሱን አብራርተዋል።

አቶ ጃፋር አሁንም መንግስት የዜጎችን ደህንነት እና የአገር ሉዓላዊነት ከማስጠበቅ ጎን ለጎን ለሰላማዊ መፍትሄ ቅድሚያ የሚሰጥ መሆኑን አብራርተዋል።

ተሳታፊዎቹም መንግስት የሰላም አማራጭ ቀዳሚ ማድረጉ ትክክል መሆኑን ገልጸው ፣ በዲፕሎማሲው ዘርፍ ለአገራቸው የሚችሉን ለማበርከት በትጋት እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል።