Get Mystery Box with random crypto!

111 ሕገ-ወጥ የዲጂታል ሚዲያዎች ላይ ክስ መመስቱን የፌደራል ፖሊስ አስታወቀ ~~~~~~~~~~~~ | The Niles ናይል 🇪🇹

111 ሕገ-ወጥ የዲጂታል ሚዲያዎች ላይ ክስ መመስቱን የፌደራል ፖሊስ አስታወቀ
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~

ሀሰተኛ መረጃዎችን በማሰራጨት ኢትዮጵያን የብጥብጥ ማዕከል ለማድረግ ሲሠሩ በነበሩ 111 ሕገ-ወጥ የዲጂታል ሚዲያዎች ላይ ክስ መመስረቱን የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡

በኮሚሽኑ የታክቲክ ወንጀሎች ምርመራ ምክትል ዋና መምሪያ ሃላፊ ረዳት ኮሚሽነር ብርሃኑ አበበ፤ ህዝብን ለአመጽ በማነሳሳት ድብቅ ዓላማቸውን ለማሳካት ሲንቀሳቀሱ እንደነበርም በምርመራ መረጋገጡን ገልጸዋል።

ከዚህ ጋር ተያይዞ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በተደራጁና የሽብር ወንጀሎች፣ በሙስና፣ በፋይናንስና ንግድ ነክ፣ በታክስና ጉሙሩክ ወንጀሎች ላይ ጥቆማዎችን መነሻ በማድረግ ምርመራዎች ተከናውነዋል ብለዋል።

ይሄውም በበጀት ዓመቱ 2 ሺህ 668 ጥቆማዎችን በመቀበል 1 ሺህ 438 መዝገቦችን መርምሮ ለፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ መላካቸውንም ገልጸዋል፡፡

ግለሰቦቹ ከ57 ሚሊየን ብር በላይ መዝረፋቸው በምርመራ በመረጋገጡ ክስ ተመስርቶባቸዋል ማለታቸውን ከኢዜአ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

The Niles