Get Mystery Box with random crypto!

New Life Ministry

የቴሌግራም ቻናል አርማ new_life_ministry — New Life Ministry N
የቴሌግራም ቻናል አርማ new_life_ministry — New Life Ministry
የሰርጥ አድራሻ: @new_life_ministry
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 7.07K
የሰርጥ መግለጫ

በክርስቶስ አዲስ ሕይወት አገኘን!
እንግዲህ ክርስቶስ በአብ ክብር ከሙታን እንደ ተነሣ እንዲሁ እኛም በአዲስ ሕይወት እንድንመላለስ፥ ከሞቱ ጋር አንድ እንሆን ዘንድ በጥምቀት ከእርሱ ጋር ተቀበርን።
ወደ ሮሜ ሰዎች 6 : 4
@newlifeministrybot
2013 የከፍታ ዓመታችን ነው!!
@NEW_LIFE_MINISTRY
@AMBASSADORLIFE

Ratings & Reviews

1.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

2


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2021-10-07 10:51:12 ደሙ!

ዘጸአት 12:13

13፤ ደሙም ባላችሁበት ቤቶች ምልክት ይሆንላችኋል፤ ደሙንም ባየሁ ጊዜ ከእናንተ አልፋለሁ፤ እኔም የግብፅን አገር በመታሁ ጊዜ መቅሰፍቱ ለጥፋት አይመጣባችሁም።


የእስራኤልን ህዝብ ከሞት መልአክ ያዳናቸዉ በመቃንና በጉበናቸዉ ላይ የተቀባዉ የፋሲካዉ በግ ደም ነዉ እንጂ መልካም ባህሪያቸዉ አይደለም! እግዚአብሔርም "ደሙን ባየዉ ጊዜ ከእናንተ አልፋለዉ" አለ እንጂ ታዛዥነታችሁንና ቅዱስ አካሄዳችሁን በማየት አልፋቿለዉ አላለም! በዚህም፣ ከሞት መልአክ የመዳናቸዉ ምሥጢር ያለዉ በደሙና በደሙ ላይ ብቻ ነዉ!

በብሉይ የነበረዉ የፋሲካ በዓል የአዲሱ ኪዳን ጥላ ነበርና
የፋሲካ በጎች ለመታረድ ኢየሩሳሌም በሚገቡበት በዝያ ቀን የዓለም ሀጢአት የሚያስወግደዉ የእግዚአብሔር በግ ክርስቶስ ኢየሩሳሌም ገባ! በመስቀልም በመንጠልጠል "ደም ሳይፈስ ስርየት የለም" እንደሚል መጽሐፍ፣ ደሙን በማፍሰስ ዘላለማዊ ስርየትን በኪዳን ተከለ! በዚህም፣ ያመኑበት በሙሉ በደሙ ንጽህናና ክብር ልክ በእግዚአብሔር ፊት ተቀባይነትን አገኙ!

ወዳጄ፣ በደሙ በተደረገዉ አዲስ ኪዳን ምንም ሳትሰራ ተጠቃሚ ብቻ ወደ ሆንክበት የጸጋ ህይወት ገብተካል! ጸጋ ደግሞ ሰጪዉን ብቻ እንጂ ተቀባዩን የማይወክል ህይወት ነዉና በእያንዳንዱ ህይወትህ ላይ "ይህን በማድረጌ" በሚል ሽልማትን በሚጠብቅ ልብ ሳይሆን "እንዲሁ ስለተወደድኩ" ከሚል የጸጋ ስጦታ ህይወትን አጣጥማት!

በረከት ናችሁ!

ወንድም ቢንያም ተስፋዬ

@ye_adis_kidan_hiwot
@new_life_ministry
2.5K views07:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-03 12:19:54
2.1K views09:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-03 10:57:26 የአብርሀም ሎሌና መንፈስ ቅዱስ!

መጽሐፍ፣ የእዉነት መንፈስ በመጣ ጊዜ ወደ እዉነት ሁሉ ይመራችኋል ይላልና መንፈስ ቅዱስ በመምጣቱ የክርስቶስ ዉበትና የእዉነት እዉቀት ተገለጠ! ይህንም ጥላ በሆነዉ በአብርሀም ሎሌ ህይወት ዉስጥ በመለኮት እቅድ ታይቷል!

የአብርሀም ሎሌ ለይስሐቅ ሚስትን ሊፈልግ ከሀገሩ ወደ ሌላ ሀገር ሄደ(ዘፍ 24:10)!

መንፈስ ቅዱስም ለክርስቶስ ሚስትን ሊፈልግ ከሰማይ ወረደ!

የአብርሀም ሎሌ መልዕክተ ይስሐቅ ነዉ(ዘፍ 24:33)!
የመንፈስ ቅዱስ መልዕክት ኢየሱስ ነዉ!

የአብርሀም ሎሌ፣ አብርሀም ያለዉን ሀብት ብርና ወርቅ በሙሉ ለልጁ እንደሰጠዉ ለርብቃ በመንገር የይስሐቅን ብልጥግና ገለጠ(ዘፍ 24:36)!

መንፈስ ቅዱስ፣ ክርስቶስ የአባቴ የሆነዉ ሁሉ የእኔ ነዉ ብሏልና ይህንን የተትረፈረፈ ብልጥግና ለቤተክርስትያን ይገልጥላታል!

የአብርሀም ሎሌ የያዘዉን የከበረ ስጦታ፣ ብርና ወርቅ ለርብቃ ሰጠ(ዘፍ 24:53)!

መንፈስ ቅዱስም ቤተክርስትያን በክርስቶስ ብልጥግናና የከበረ ሀብት እንድትኖር ያደርጋታል!

በረከት ናችሁ!

ወንድም ቢንያም ተስፋዬ

@ye_adis_kidan_hiwot
@new_life_ministry
2.5K views07:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-29 09:42:47 እግዚአብሔር ያዉቅሀል!

ማቴዎስ 7:21-23

21 በሰማያት ያለውን የአባቴን ፈቃድ የሚያደርግ እንጂ፥ ጌታ ሆይ፥ ጌታ ሆይ፥ የሚለኝ ሁሉ መንግሥተ ሰማያት የሚገባ አይደለም።

22 በዚያ ቀን ብዙዎች። ጌታ ሆይ፥ ጌታ ሆይ፥ በስምህ ትንቢት አልተናገርንምን፥ በስምህስ አጋንንትን አላወጣንምን፥ በስምህስ ብዙ ተአምራትን አላደረግንምን? ይሉኛል።

23 የዚያን ጊዜም። ከቶ አላወቅኋችሁም፤ እናንተ ዓመፀኞች፥ ከእኔ ራቁ ብዬ እመሰክርባቸዋለሁ።

መጽሐፍ፣ ጸጋዉ በእምነት አድኗቿል በማለት ደህንነት እግዚአብሔር በጸጋ ሰርቶ የጨረሰዉና በእምነት ብቻ ሰዎች ጋር የሚደርስ ነጻ ስጦታ መሆኑን በግልጽ ቃል ነገረን! ነገር ግን፣ ብዙ ሰዎች ከላይ ያለዉን ጥቅስ ከሕግ ጋር በመስፋት፣ መልካም ሥራ ያልሰራ ሰዉ በመጨረሻ ቀን በክርስቶስ "አላዉቅህም" እንደሚባልና ይህ እንዳይሆን ግን ሰዉ ሕግን መጠበቅ እንዳለበት በማስተማር አማኝን ከጸጋዉ ክብር ላይ ገፍተዉ ወደ ብሉይ አድርግ አታድርግ ትዕዛዝ ሲጥሉት ማየት የተለመደ ሆኗል! ይህ ግን ቃሉን በትክክል ካለመረዳት የመጣ የሀይማኖት እዉርነት ነዉ!

ክርስቶስ፣ የአባቴን ፈቃድ የሚያደርግ እንጂ ሲል ይህ የአባቱ ፈቃድ ሕግን መጠበቅና በራስ ሥራ እግዚአብሔርን ለመቅረብ መሞከር ሳይሆን እግዚአብሔር በክርስቶስ ሰርቶ የጨረሰዉን በእምነት መቀበልን ያመላክታል(ዮሐ 6:29)!

በክርስቶስ በማመናችን በእግዚአብሔር ዘንድ ታዉቀናል፣ በዚህም ስማችን በህይወት መዝገብ ላይ ተጽፏል! ከዚህም የተነሳ ከቶ አላዉቃችሁም(I never knew you) የሚለዉ ቃል፣ የህይወት መዝገብ የማያዉቃቸዉን እንጂ በክርስቶስ ደም የታጠቡትን፣ የመንፈሱንም መያዣ የተቀበሉትን አማኞች የሚመለከት አይደለም! ምክንያቱም እግዚአብሔር እዉነተኛ አምላክ ነዉና አንዴ ካወቀን በኋላ ከቶ አላዉቃችሁም(I never knew you) ብሎ ሊዋሽ አይቻለዉም!

ወዳጄ፣ በክርስቶስ በማመን ደህንነትህን ላታጣዉ በመንፈስ ቅዱስ ታትመካል! በዚህም ከክርስቶስ እጅ ማንም ሊነጥቅህ አይችልም! በዚህ እዉነት ልብህን አሳርፈዉ!

በረከት ናችሁ!

ወንድም ቢንያም ተስፋዬ

@ye_adis_kidan_hiwot
@new_life_ministry
2.3K views06:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-19 10:10:10
2.1K views07:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-19 10:10:05 ወርሰናል!

ሮሜ 8:16-17

16 የእግዚአብሔር ልጆች መሆናችንን ያ መንፈስ ራሱ ከመንፈሳችን ጋር ይመሰክራል።

17 ልጆች ከሆንን ወራሾች ደግሞ ነን፤ ማለት የእግዚአብሔር ወራሾች ነን፥ አብረንም ደግሞ እንድንከበር አብረን መከራ ብንቀበል #ከክርስቶስ_ጋር_አብረን_ወራሾች #ነን።

ብዙ ጊዜ የረገጥኩትን አወረሰኝ ሲባል ነዉ የምንሰማዉ፣ በአዲሱ ኪዳን እዉነታ ግን የወረስነዉን ነዉ የምንረግጠዉ! አየህ፣ ከክርስቶስ ጋር ወራሽ ተደርገናልና የወረስነዉን ሁሉ እየገለጥን እንኖራለን እንጂ ስንረግጠዉ የምንወርሰዉ ዉርስ የለም!

እግዚአብሔር አባታችን ታላቅ ወንድማችን የሆነዉን ክርስቶስን ያወረሰዉን ሁሉ እኛንም አዉርሶናል! ክርስቶስ አብን የተረከልን ብቻ ሳይሆን የእኛን እዉነተኛ ማንነት የተረከልን ትክክለኛ የማንነታችን ነጸብራቅ ነዉ! በዚህም፣ እርሱን ማወቅ እራስን ማወቅ ነዉ! ምክንያቱም መጽሐፍ ክርስቶስ ብሎ ሳይሆን በክርስቶስ፣ ልጁ ብሎ ሳይሆን በልጁ ብሎ ይነግረናልና!

ወዳጄ፣ አንተ በምድር ያለኸዉ ቁርጥ ክርስቶስ በሰማይ ባለበት የህይወት ስርአት ነዉ! አሁን እርሱ ያለበትን ሰላም፣ ሀሤት፣ ጤንነት፣ ብልጽግና፣ ህብረት፣ ጽድቅና ቅድስና ይዘህ አንተ በዚህ ነህ! ምክንያቱም ከእርሱ ጋር የእግዚአብሔር የሆነዉን ሁሉ ወርሰሀልና!

በረከት ናችሁ!

ወንድም ቢንያም ተስፋዬ

@ye_adis_kidan_hiwot
@new_life_ministry
2.3K views07:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-17 07:37:50
1.8K views04:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-17 07:37:46 ተፈዉሰናል!

1ኛ ጴጥሮስ 2:24-25

24 ለኃጢአት ሞተን ለጽድቅ እንድንኖር፥ እርሱ ራሱ በሥጋው ኃጢአታችንን በእንጨት ላይ ተሸከመ፤

25 በመገረፉ ቁስል ተፈወሳችሁ። እንደ በጎች ትቅበዘበዙ ነበርና፥ አሁን ግን ወደ ነፍሳችሁ እረኛና ጠባቂ ተመልሳችኋል።

የክርስቶስን የምድር ህይወትና አገልግሎት ስንመለከት፣ ሁልጊዜ በባህር ላይ ሲራመድና ንፋስን ሲገስጽ አናየዉም፣ ነገር ግን ሁል ጊዜ በበሽታ የተያዙትን ሁሉ ሲፈዉስ እናያለን። በዚህም፣ ለሰዎች የእግዚአብሔር ልብ በጤንነት እንዲኖሩ መሆኑን እንረዳለን! ለዝያም ነዉ፣ አስቀድሞ ነብዩ ኢሣያስ በትንቢት መንፈስ የአዲሱን ኪዳን ህይወት በመመልከት፣ "በመገረፉ ቁስል ተፈወሳችሁ" ብሎ ሲናገር ጴጥሮስ ደግሞ አዲሱ የጸጋዉ ኪዳን በክርስቶስ ደም ከተመሰረተ በኋላ በተፈጸመዉ ትንቢት ላይ በመቆም፣ በመገረፉ ቁስል ተፈወሳችሁ በማለት መለኮታዊ ጤንነት የክርስቶስ የመስቀል ሥራ ስጦታ መሆኑን የነገረን።

ብዙ ሰዎች፣ በመገረፉ ቁስል ተፈወሳችሁ የሚለዉ ቃል ስለ መለኮታዊ ጤንነት ሳይሆን በክርስቶስ የተገኘዉን ከኃጢአት በሽታ መዳን ነዉ የሚናገረዉ ብለዉ ጥቅሱ የማይለዉን ለማስባል ይጠመዝዙታል! ነገር ጥቅሱ ምን እንደሚል ክርስቶስ በምድር ህይወቱ ተርጉሞልን ሄዷልና በክርስቶስ ቃል እንኖራለን!

ማቴዎስ 8:16-17

16-17 በመሸም ጊዜ አጋንንት ያደረባቸውን ብዙዎችን ወደ እርሱ አመጡ፤ በነቢዩ በኢሳይያስ። እርሱ ድካማችንን ተቀበለ ደዌያችንንም ተሸከመ የተባለው ይፈጸም ዘንድ፥ መናፍስትን በቃሉ አወጣ፥ #የታመሙትንም_ሁሉ_ፈወሰ።

ወዳጄ፣ እንኳን አባትህ እግዚአብሔር ይቅርና ምድራዊ መንግስት እራሱ፣ " ዘመኑ የሰላምና የጤና እንዲሁም የብልጽግና " ይሁንላችሁ ብሎ ይላል! መለኮታዊ ጤንነት ኩልል ያለ የእግዚአብሔር ፈቃድ ነዉ! በክርስቶስም እኛ ጋር ደርሷል!

በረከት ናችሁ!

ወንድም ቢንያም ተስፋዬ

@ye_adis_kidan_hiwot
@new_life_ministry
1.8K views04:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-13 13:42:43
1.9K views10:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ