2021-10-15 10:44:18
ክርስቶስ የአዲስ ኪዳን የፋሲካ በግ!
ዘጸአት 14
የብሉይ ፋሲካ መሥዋዕት ነዉር አልባ ነበር!
ክርስቶስ ነዉር የሌለበትና ፍጹም ንጹህ የሆነ የእግዚአብሔር በግ ነዉ!
የሞት መላዕክ የመሥዋዕቱን ደም በእስራኤላዉያን መቃንና ጉበን ላይ በማየት አለፋቸዉ!
መጽሐፍ፣ "ደም ሳይፈስ ስርየት የለም"፣ "የሀጢአት ደሞዝ ደሞ ሞት ነዉ" ይላልና በክርስቶስ ደም ስርየትን ስላገኘን ከዘላለም ሞት ድነናል!
የእስረኤል ህዝብ የበሉት የፋሲካዉ በግ ሥጋ በእሳት የተጠበሰ መሆን ነበረበት!
የእግዚአብሔር ፍርድና ቁጣ በመስቀል በክርስቶስ ላይ ነዷል፣ በዚህም የእግዚአብሔር ቁጣ ለዘላለም በርዷል!
የእስራኤል ህዝብ የተጠበሰዉን ሥጋ ከመራር ቅጠል ጋር በሉት! ይህም፣ የበጉን ፍርድ መካፈላቸዉን ያሳያል!
እኛም ከክርስቶስ ጋር በመሰቀል መከራን ተቀብለናል፣ ከእርሱ ጋር ተሰቅለናል፣ ከእርሱም ጋር ሞተናል!
የፋሲካዉን በግ ደም በሂሶጵ ቅጠል ነበር በመቃናቸዉና በጉበናቸዉ ላይ የቀቡት!
እኛም የአዲስ ኪዳን ሂሶጵ በሆነዉ እምነት የክርስቶስን ደም በህይወታችን ላይ ረጭተናል!
የፋሲካዉ በግ አጥንት እንዳይሰበር እግዚአብሔር አዘዛቸዉ!
በመስቀል የክርስቶስም አጥንት አልተሰበረም!
በጉ በአስረኛዉ ቀን ይያዝና እስከ አስራ አራተኛዉ ቀን ድረስ ተይዞ ይቆያል! ይህም መሥዋዕት ከመሆኑ በፊት 5 ቀን ይጠብቃል ማለት ነዉ!
ክርስቶስም ከተያዘ በኋላ 5 ቆየ፣ ከዝያም የዓለምን ሀጢአት ሊያስወግድ መሥዋዕት ሆነ!
የበጉን ሥጋ የበሉ ሁሉ ጤነኛ ሆኑ(መዝ 105:37)
የክርስቶስ ሥጋ ለጤንነታችን ተገርፏልና በመገረፉ ቁስል እኛ ተፈወስን!
በረከት ናችሁ!
ወንድም ቢንያም ተስፋዬ
@ye_adis_kidan_hiwot
@new_life_ministry
3.8K views07:44