Get Mystery Box with random crypto!

ብልጥግና! 1ኛ ቆሮንቶስ 1 4፤ በክርስቶስ ኢየሱስ ስላመናችሁ በተሰጣችሁ በእግዚአብሔር ጸጋ ምክ | New Life Ministry

ብልጥግና!

1ኛ ቆሮንቶስ 1
4፤ በክርስቶስ ኢየሱስ ስላመናችሁ በተሰጣችሁ በእግዚአብሔር ጸጋ ምክንያት ሁልጊዜ ስለ እናንተ አምላክን አመሰግናለሁ፤

5-6፤ ለክርስቶስ መመስከሬ በእናንተ ዘንድ እንደ ጸና፥ በነገር ሁሉ በቃልም ሁሉ በእውቀትም ሁሉ በእርሱ ባለ ጠጎች እንድትሆኑ ተደርጋችኋልና።

ጳውሎስ፣ በቆሮንጦስ ላለችው ለእግዚአብሔር ቤተክርስትያን፣ ''በክርስቶስ ኢየሱስ ከማመናችሁ የተነሣ በነገር ሁሉ፣ በቃልም ሁሉ በእውቀትም ሁሉ ባለጠጋ ተደርጋችኋል!'' ብሎ አለ!

ወንጌል ያበለጥጋል! ወንጌል አያበለጥግም ብሎ ማለት ዉኃ ውስጥ ገብተህ ሳትረጥብ እንደ መቅረት ነው!

ብዙ ሰው በገንዘብ አቅጣጫ ያለውን የእግዚአብሔርን ፈቃድ መንካት ስለማይፈልግ፣ አዲስ ኪዳንን የመንፈሳዊ በረከት(ጽድቅ፣ ቅድስና፣ ክብር፣ ልጅነት) ብቻ አድርጎ ለማስቀመጥ ይሞክራል። በአዲስ ኪዳን፣ ከሰማያዊ ጥሪ ተካፋዮች በመደረግ፣ በክርስቶስ የመስቀል ሥራ ጽድቅና ቅድስና ልጅነትና ክብር ለእኛ ቢሆንም መንፈሳዊ በረከትን ባገኘንበት በዝያው በክርስቶስ የመስቀል ሥራ የአብርሀም ዘር በመሆን በአብርሀም በረከት ተባርከን የምድርም ባለጠጎች ተደርገናል!

ወዳጄ፣ ሰማይ ቤት ስትሄድ ታርፋለህ፣ ትበለጥጋለህ እያለ ለሞት ከሚያዘጋጅህ ትምህርት ፈጥነህ ራቅ! ሰማይ ቤት የሚነዳህ መኪና እንደሌለህ ላስታውስህ! መዝሙረኛው፣ ''እግዚአብሔር እረኛዬ ነው፣ የሚያሳጣኝም የለም'' ብሎ ያለው ለምድር ህይወቱ እንጂ ለሰማይ አይደለም! አባቴ ባለጠጋ ነው፣ እኔም በብልጥግናው እኖራለው!

ወንድም ቢንያም ተስፋዬ

@ye_adis_kidan_hiwot