Get Mystery Box with random crypto!

Neba Daniel - ነባ ዳንኤል

የቴሌግራም ቻናል አርማ nebyoudan — Neba Daniel - ነባ ዳንኤል N
የቴሌግራም ቻናል አርማ nebyoudan — Neba Daniel - ነባ ዳንኤል
የሰርጥ አድራሻ: @nebyoudan
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 5.85K
የሰርጥ መግለጫ

በዚህ ቻናል ላይ የተለያዩ መንፈሳዊ መረጃዎችን ስለማጋራችሁ ቻናሉን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
*************************
በፌስቡክ ገፃችን እንዲሁም በቴሌግራም ቻናላችን መንፈሳዊ ማስታወቂያዎች እንዲለቀቅልዎ ከፈልጉ ከታች ባለው ስልክ ደውለው ያናግሩን

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-08-13 22:04:46
በቦታው ከነበርኩት ከእኔ እውነቱን ስሙት

ዘሪቱ በህንፃው ውስጥ እና በሱቅ ላገኝቻቸው ኢየሱስ አዳኝ እንደሆነ በአፏ እና ከያዘችው ወረቀት እየሰጠች ስትሰብክ ሁለት ካሜራ በቅርበት ማንም በሚያየው መልኩ እየተከተሏት ስትቀረፅ ነበር: ከምስሉ እንደምትመለከቱት ቅሬታ አቅራቢ የሆነችውን ዶ/ር ጨምሮ ጥቂቶች ካሜራ እንዳለ እያወቁ በፈገግታ እና በጥሩ መግባባት ሰምተው ወረቀቱንም ተቀብለው አንዳንዶቹም ፍቅራቸውን ገልፀውላት ወደዋናው ቀረፃ ገብታለች።
በጣም በእርግጠኝነት ከተቀረፁት አንድም ሰው በድብቅ አልተቀረፀም ማንምም እንዳልቀረፅ ብሎ ቅሬታ አላቀረበም። ቅሬታ አቅራቢዋ ዶ/ርም ካሜራውን እንዳየች ማስቆም ከዛም ሲያልፍ ፈቅዳ እንኳን ተቀረፃ ቢሆን አታስገቡኝ ከዛም ተለቆ ህዝብ ጋር ደርሶ ከየትኛውም ሚዲያ ምስሌን አንሱ የማለት መብት እንዳላት አውቃለው: የዶ/ሯ በድብቅ ተቀረፅኩ በሚል ውንጀላ ያቀረበችው ፁሁፍ ግን ፍፁም ሀሰት እና ከዘሪቱ ስብእና ውጪ የሆነ ወሬውን የማድመቂያ ስልት ወይም ሌላ አጀንዳዋን የማስፈፀሚያ እንደሆነ አስባለው።
2.2K views19:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-13 21:43:33

1.9K views18:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-10 21:11:09
#እውነተኛው_የክርስቶስ_ፍቅር_በሙላት_ሲገባብን_ወንጌሉን_ለማስቀጠል_ምቹ_ሁኔታን_አንጠብቅም!!!
ስለ ወንጌል ሁሉን እናደርጋለን!!

#መቶ_ሃያ_(120) ተጠምቀው ወደ ቤተክርስቲያን ተጨምረዋል።

በመሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን በምስራቅ አዲስ አበባ አጥቢያ በተሠማሩ የወንጌል ሚስዮናዊያን አማካኝነት በቦረና የገጠራማው ክፍል የሚኖሩና በቁጥር 120 የሚሆኑ ሰዎች ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን አምነውና መሠረታዊ የክርስትና ትምህርት ተምረው የውሃ ጥምቀት ወስደዋል።
ወንጌላችን ገና ድል ያደርጋል
የእግዚአብሔር ቃል ገና አለምን ይዞራል
በአራቱም ማዕዘን ይዳረሳል
ሁሉን ይለውጣል ያሸንፋል
#ወንጌል_የጋራ_አጀንዳችን_ነው!!
2.3K views18:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 10:45:32 ከ part 1 የቀጠለ
ቤት ኪራይ መክፈል አቅቷቸው፤ አከራይ አሁን ውጡ ብሏቸው፤ ልጆቻቸውን የሚያበሉት አጥተው እኔስ ምንም ልሁን ልጆቼን ግን ምን ላብላ ብለው፤ ልጆቼ ቁርስ እንኳን አጥተው ትምህርት ቤት ሁለት ቀናቸው ነው ተብዬ ላንዳንዶቹ ካለኝ አካፍዬ ሌሎቹን ልቡ ያላቸውን ሰዎች አገናኝቼ፤ የተቀሩትንም እየሰሩ የሚያገለግሉበትን መንገድ አሳይቼ መነሻ አመቻችቼ አንዳንዶቹንም አስቀጥሬ፤ ሲያቅተኝም ስለሚያልፉበት ነገር አብሬያቸው አልቅሼ አውቃለሁ።

ይህ ሁሉ ግን ከክርስቶስ ፍቅር ሊለያቸው ከቶ አልቻለም። አንዳንዶቹ ያንን የጭንቅ ዘመን አልፈው ዛሬ ለሌሎች መቆረስ ጀምረዋል።

እናም የምወድህ ወንድሜ ሳሚዬ ሆይ የሚወድህ የሞተልህ ያገለገልከው ጌታ ተጠቅሞ የሚጥል ጥርግ በል የሚልህ "ሰው" አይደለም!

ዛሬም እንደቀድሞ ሳይለወጥ በዚያው ፍቅር ይወድሃል፤ ልጄ መቼ ይመለስ ይሆን ብሎ ደጅ እያየ ይጠብቅሃል። ና ወደ ቤቱ ተመለስ ጉያው ይሻልሃል።

የተቸገርክበት ነገር ካለም እኔ ወንድምህም ሆንኩ እልፍ ደጋግ ወገኖችህ ከጎንህ ይቆማሉ፤ ከዛሬ ነገ ዘፈኑ ይለቀቃል በዛ መረዋ ድምፁ ሊዘፍን ነው ብሎ የቋምጠውን ሰይጣንን አሳፍረው።

ና ወንድማለም በንስሃ ወደ ቤቱ ተመለስ ጉያው ይሻልሃል። እጅግ በጣም እወድሃለሁ። አጥብቄም ስላንተ እፀልያለሁ።
(ሼር በማድረግ አድርሱልኝ!)
762 viewsedited  07:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 10:42:12
ይድረስ ለዘማሪ ሳሙኤል አበበ(ሳሚዬ)
ቤተክርስቲያን ተገቢውን ትኩረት አልሰጠችህ ይሆናል አገልግሎት መጋበዝ እስኪናፍቅህ ድረስ ብዙዎች መድረካቸውን ዘግተውብህ ይሆናል፤ ከፍቶህ ረሃብ፣ እርዛቱም ጠንቶብህ ይሆናል! አቅም ከድቶህ፣ ተስፋ ቆርጠህ፣ ዞር ብሎ የሚያይህ አጥተህ ይሆናል!
አዎ ይገባኛል! እንደሚባለው ቀላል አይደለም እጅግ ከባድ ነው ልብ ያደማል! ወንድሜ ሆይ እነዚህ ሁሉ ነገሮች ግን ከክርስቶስ ፍቅር ሊለዩህ አይችሉም።(ለመለየትህም ምክንያት አይሆኑም! በእውነት እነግርሃለሁ ውድ ወንድሜ ይህ አንተ ብቻ የምታልፍበት ወይም ያለፍክበት መንገድ አይደለም። ከተሞክሮዬ ትንሽ ልበልህ ብዙ ሲታዩ በሱፍ አምረው ችግር የማያውቃቸው የሚመስሉህ እውቅ ዘማሪዎች በብዙ መከራ ውስጥ እያለፉ ግራ ገብቷቸው አማክረውኝ ያውቃሉ፤ ዛሬም የሚያማክሩኝ አሉ። part 2 ይቀጥላል
734 views07:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 10:19:57

735 views07:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-12 23:57:49
የሰሞኑን አነጋጋሪ ጉዳይ
ዘማሪ ሳሙኤል አበበ ዘፈን ሊያወጣ ነው
ለዚህም ተጠያቂዋ ቤተክርስቲያን ናት ብሏል
936 views20:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-12 16:29:59
መልካም ወጣት ወደተለወጠው ህይወት 2014 በማስመልከት በMarsil press team ጋዜጣዊ መግለጫ ተሰጠ። በዘንድሮው አመት #በሀዋሳ_ከተማ_የሚደረገውን_ስልጠና_እና_በአዲስ_አበባ_የሚደረገውን_የመልካም_ወጣት_የመክፈቻ_ፕሮግራም አስመልክቶ የመልካም ወጣት ፕሬዚዳንት አገልጋይ ዮናታን አክሊሉ እና አገልጋዮች በሃገራችን ለሚገኙ ለተለያዩ የሚዲያ አካላት ጋዜጣዊ መግለጫ ዛሬ _ሐምሌ_5_ቀን_2014_ዓም_ሰተዋል መልካም ወጣትን በተመለከተ ከተለያዩ የሚዲያ አካላት ለተነሱት ጥያቄ በአገልጋይ ዮናታን አክሊሉ የመልካም ወጣት ፕሬዝዳንት በኩል ምላሽ እና ማብራሪያ ተሰቶባቸዋል ሙሉ መረጃውን በMarsil tv እና በማህበራዊ ሚዲያዎቻችን የምናስተላልፍ መሆኑን ለመግለፅ እንወዳለን።
1.1K views13:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-11 17:37:52
ዘላለማዊ ልብሴ #ኢየሱስ
1.2K views14:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 19:57:14
እግዚአብሔር ነው ብርሃኔ
ጨለማው ከብርሃኔ በላይ አይደለም
ህማሜ ከመድኀንቴ በላይ አይደለም (2*)
እግዚአብሔር ነው ብርሃኔ
እግዚአብሔር ነው መድኀንቴ
1.9K views16:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ