Get Mystery Box with random crypto!

ይድረስ ለዘማሪ ሳሙኤል አበበ(ሳሚዬ) ቤተክርስቲያን ተገቢውን ትኩረት አልሰጠችህ ይሆናል አገልግሎት | Neba Daniel - ነባ ዳንኤል

ይድረስ ለዘማሪ ሳሙኤል አበበ(ሳሚዬ)
ቤተክርስቲያን ተገቢውን ትኩረት አልሰጠችህ ይሆናል አገልግሎት መጋበዝ እስኪናፍቅህ ድረስ ብዙዎች መድረካቸውን ዘግተውብህ ይሆናል፤ ከፍቶህ ረሃብ፣ እርዛቱም ጠንቶብህ ይሆናል! አቅም ከድቶህ፣ ተስፋ ቆርጠህ፣ ዞር ብሎ የሚያይህ አጥተህ ይሆናል!
አዎ ይገባኛል! እንደሚባለው ቀላል አይደለም እጅግ ከባድ ነው ልብ ያደማል! ወንድሜ ሆይ እነዚህ ሁሉ ነገሮች ግን ከክርስቶስ ፍቅር ሊለዩህ አይችሉም።(ለመለየትህም ምክንያት አይሆኑም! በእውነት እነግርሃለሁ ውድ ወንድሜ ይህ አንተ ብቻ የምታልፍበት ወይም ያለፍክበት መንገድ አይደለም። ከተሞክሮዬ ትንሽ ልበልህ ብዙ ሲታዩ በሱፍ አምረው ችግር የማያውቃቸው የሚመስሉህ እውቅ ዘማሪዎች በብዙ መከራ ውስጥ እያለፉ ግራ ገብቷቸው አማክረውኝ ያውቃሉ፤ ዛሬም የሚያማክሩኝ አሉ። part 2 ይቀጥላል