Get Mystery Box with random crypto!

Neba Daniel - ነባ ዳንኤል

የቴሌግራም ቻናል አርማ nebyoudan — Neba Daniel - ነባ ዳንኤል N
የቴሌግራም ቻናል አርማ nebyoudan — Neba Daniel - ነባ ዳንኤል
የሰርጥ አድራሻ: @nebyoudan
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 5.85K
የሰርጥ መግለጫ

በዚህ ቻናል ላይ የተለያዩ መንፈሳዊ መረጃዎችን ስለማጋራችሁ ቻናሉን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
*************************
በፌስቡክ ገፃችን እንዲሁም በቴሌግራም ቻናላችን መንፈሳዊ ማስታወቂያዎች እንዲለቀቅልዎ ከፈልጉ ከታች ባለው ስልክ ደውለው ያናግሩን

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2022-07-07 08:46:08
ኢየሱስ ህይወት ነው
1.7K viewsedited  05:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 17:03:22
#ከወንድሞች #ተጠንቀቁ
አቤልን ማን ገደለው?
ወንድሙ
ዮሴፍን ማን ሸጠው?
ወንድሞቹ!
ዮፍታኄን ማን አነወረው?
ወንድሞቹ!
ዳዊትን ማን አንጓጠጠው?
ወንድሞቹ!
የጠፋው ልጅ ወደቤት ሲመለስ ማን ተንጨረጨረ?
የገዛ ወንድሙ!
እነዚሁ በወንድሞቻቸው የተንጓጠጡና የተካዱት ናቸው፤ በአምላክ በእጅጉ የተባረኩትእነዚሁ ወንድሞች የእግዚአብሔር ዕቅድ ማስፈፀሚያዎች ናቸውና፣ ባርኳቸው ፀልዩላቸውም።
ብሩክ ሁኑ፣
ጥላቻና ክፋቱ ከእነርሱ ይምጣ እንጂ፤ ጌታ ነገሩን እንዴት እንደሚያከስመውና ዕቅዱን እንዲፈፅም ያውቃል።
በጌታ ኢየሱስ ክቡርና ጻድቅ ሥም ብሩካን ሁኑ .
2.0K views14:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-05 08:14:24
#የተሰማኝን_ጥልቅ_ሀዘን_እገልጻለሁ!

በንጹሃን ላይ በደረሰው ጭፍጨፋ እጅግ አዝናለሁ ።

##የተሰማኝን_ጥልቅ_ሀዘን_እገልጻለሁ።

በኦሮሚያ ክልል ቄለም ወለጋ ውስጥ በሚገኙ በንፁሃን ዜጎች ላይ በደረሰው ጭፍጨፋ ሀዘኔን ስገልጽ በታላቅ የልብ ስብራት ነው።

ከትናንቱ ሀዘን ሳንጽናና ሌላ ሀዘን በመጨመር ከሰውነት የወረዱ ሰብዓዊነት የማይሰማቸው ግለሰቦች ተስፋችንን በማጨለም የልብ ክፋታቸውን በንፁሃንን በመጨፍጨፍ የተበቀሉ መስሎአቸው አንገታችንን ለማስደፋት እየሰሩ ነው የንፁሃን ደም ይጮኻል ፈጣሪም ብድራታቸውን ይከፍላል።

በዚህ ፈታኝ ጊዜ መንግስት ዜጎች ደህንነት እንዲሰማቸው የማድረግ ሃላፊነት አለበት በተለይ በተናበበ መንገድ ቀድሞ የመከላከል ስራውን አጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል።
በተለይ በአከባቢው የምትገኙ ሃይማኖት አባቶች፣አባገዳዎች፣ሃዳ ሲንቄዎች፣የሀገር ሽማግሌዎች ወጣቶች በንፁሃን ሰዎች ላይ እየደረሰ ያለውን ጭፍጨፋ ሞት በቃ በማለት ማወገዝ ይገባል።

እንዲህ አይነት ጥቃቶችን ሰው የሆነ ሁሉ ማወገዝ በቃ ብል ወቃወም አለበት።
1.8K views05:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-02 21:52:57
እግር ኳስ ተጫዋቾቻችን በአደባባይ ወንጌልን እየሰበኩ ነው
ተባረኩ
2.1K views18:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-02 17:41:10
ኢየሱስን አምኖ የሕይወቱ ጌታ ንጉሱ ያረገ
(ደግ አረገ ኤኤ ደግ አረገ)
ጌታን በማመኑ እንደ ሃይማኖት ከጂ አርጐ የተቆጠረ
(ደግ አረገ ኤሂ ደግ አረገ)
ቀድሞ ከነበሩት ከባልንጀሮቹ ተለይቶ ሄደ
(ደግ አረገ ኤኤ ደግ አረገ)
ላመነበት ነገር አንገቱን ለካራ ሊሰጥ የጨከነ
(ደግ አረገ ኤሂ ደግ አረገ)
2.3K views14:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-01 08:55:54
የአገልጋይ ዮናታን አክሊሉ መልዕክት
መለኮታዊ ጥሪ ባለው አገልጋይ ላይ መረጃ(ፍሬ)አልባ የሆኑ አሉባልታዋችና ወሬዋች ሊሰራጩበት ይችላል።አገልጋይ እዲህ አይነቱ መረጃና ፍሬ አልባ ወሬ ላይ ተመሥርቶ አይደናገጥም።ነህምያ ላይ የተነሱት ሰንበላጥና ጦቢያ ዓረባዊም ጌሳም ሥራውን ለማስቆም ብዙ ሙከራዋችን አድርገው አልሳካ ሲላቸው ወሬን ያስወሩበት ጀመር።ነህምያ ግን በወሬው ከመናወጥ ይልቅ "አንተ ከልብህ ፈጥረኸዋል እንጂ እንደተናገርከው ምንም የለም"ብሎ መለሰለት።(ነህ6:8 )ዓላማውን የሚያውቅ አገልጋይ ለፈጠራ ወሬ ጆሮውን ሰጥቶ እራሱን አያስቸግርም።በዚህች አጭር የአገልግሎት ጉዞዎቼ ውስጥ በፈጠራ ወሬዎችና ችግሮች ብዙ መከራ ተቀብያለሁ።ይሁን እንጂ ስራዬን ሳላቆም ቀጥያለሁ።ጌታም በዚህ ውስጥ ብዙ ረድቶኛል።የዘንድሮም መልካም ወጣት በጌታ ፀጋ ብዙ ምርኮ ያለበት እንደሚሆን አምናለሁ።ለእኔ ብርታት ለዶኢ ጤንነት ለሌዊ ጥበቃ እንዲሆንልን በፀሎታችሁ አስቡን።
2.2K views05:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-30 18:28:40
1.9K views15:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-28 20:24:04
#የአባት_እጅ_እንዳለ_ስታውቅ_አትሸማቀቅም!

#የአባት_እጅ ከአንተ ስር እንዳለ ስታውቅ በሁኔታዎች ሁሉ #መሳቅ እና #መደሰት ትጀምራለህ....... እንዳትወድቅ ደግፎ አቅፎ የሚይዝህ የአባትህ እጅ አለ!.....ጣልነው ብለው ሊደሰቱ ሲሉ እንኳ የሚጥሉህ የአባትህ እጅ ላይ ነው...

በጣም #በስኬት_ጎዳና ስትጓዝ ሳቅ የአባት አጅ ከበታቾችህ ሆነው ነው። በአስቸጋሪ ሁኔታዎች እያለፍክ ልትወድቅ ሲመስልህም ሳቅ የአባት እጅ ላይ ነው መጨረሻህ...ከሱ ዘንድ የወደቀ ደግሞ ባለ ድል እንጂ ተሸናፊ ሆኖ አያውቅም!
2.2K views17:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-28 15:14:18 በአሜሪካ የጸደቀውን አዲሱን ውርጃን የሚከለክል ህግ በመደገፍ የወንጌላዊያን አብያተክርስቲያናት መሪዎች ደስታቸውን በመግለጽ ላይ ይገኛሉ፡፡
ሮይ ቪ ዋድ የተሰኘውና ባለፉት 50 አመታት በስራ ላይ የነበረውን በአሜሪካ ውርጃን የሚፈቅደውን ህግ መሻር ተከትሎ በርካታ የወንጌላዊያን አብያተክርስቲያናት መሪዎች ድጋፋቸውንና ደስታቸውን እየገለጹ እንደሚገኙ ክርስቲያን ሄድ ላይንስ ዘግቧል፡፡
መሪዎቹ ለዚህ ህግ መሻር ላለፉት 50 አመታት ያላቋረጠ ትግል ሲያደረጉ የነበሩ የህይወት ደጋፊ ቡድኖችን ስለ ድካማቸው ውጤት ማምጣት የአድናቆትና የምስጋና መልዕክቶቻቸውን በማህበራዊ ሚዲያ መድረኮቻቸው እየገለጹ ይገኛሉ፡፡
ይሁን እንጂ ህጉ ወደክልሎች የተመራ በመሆኑ ሊሰሩ ስለሚገቡ ቀጣይ ስራዎችና ለችግር ተጋላጭ የሆኑ እናቶችና ቤተሰቦችን ስለመደገፍ የወንጌላዊያን አብያተክርስቲያናት መሪዎች ትኩረት ሰጥተው እየተነጋገሩ ናቸው፡፡
ጥናቶች እንደሚያሳዩት የሮይ ቪ ዋድ ህግ ተግባራዊ ሆኖ በቆየበት 50 አመታት በአሜሪካ ከ 63 ሚሊየን በላይ ውርጃዎች የተፈጸሙ ሲሆን በ2020 ብቻ 930 ሺ ህጻናት በውርጃ ተገለዋል፡፡
ህጻናት በእናታቸው ማህጸን እያሉ የመኖር መብታቸውን ተነጥቀው ሊገደሉ አይገባም የሚሉ በሚሊየን የሚቆጠሩ ሰዎች ህጉን የሚቃወሙ ሰልፎችን በማድረግና በመጸለይ ባለፉት 50 ዓመታት ያደረጉት ትግል ፍሬ አፍርቶ ህጉ ሊቀለበስ መቻሉን ክርስቲያኒቲ ቱዴይ ዘግቧል፡፡
1.9K views12:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ