Get Mystery Box with random crypto!

ሃሰተኛ መምህራን እውነተኛ የሆነውን ትምህርት በመንፈቅ አፈንግጠው የሚወጡ ናቸው። አፈንግጠው ወጥተ | ናዝራዊ Tube

ሃሰተኛ መምህራን እውነተኛ የሆነውን ትምህርት በመንፈቅ አፈንግጠው የሚወጡ ናቸው። አፈንግጠው ወጥተው ግን አርፈው የሚቀመጡም የሚያስቀምጡም አይደሉም። ራሳቸውንና አስተምኅሯቸውን አስረገው በማስገባት የመንጋውንና የቤተክርስቲያንን ጤና ለማወክ ይዳክራሉ። ትምህርታቸውና እምነታቸው ከቅዱሳት መጽሐፍት በተቃርኖ የቆመ ቢሆንም ትምህርታቸውን አስርገው ለማስገባት ይጥራሉ።

ይህ ዶክመንተሪ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሰረቶችን እየፈተሸ፣ ትውፊትን እያጣቀሰ ከአጉል ተስፋዎች ይጠብቀናል። ብዙ ትኩረት ለሃሰተኞች በሚሰጥበት በዚህ ዘመን ሃሰተኞቹ ስለሚያወድሙት ምስኪን መንጋ ግድ የሚላቸው አገልጋዮች  እንደ እግዚአብሔር እውነት ሙግት ይቀርባል።

መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ሃሰተኛ መምህራን ምን ይላል? የሐዋርያት ቤተክርስቲያን ሃሰተኛ ሆነው ለተገኙ ትምህርቶች ምን ምላሽ ሰጡ? የቤተክርስቲያን አባቶችስ ምላሻቸው ምን ነበር? ለሃሰተኛና ሰርጎ ገብ ትምህርት ምላሽ መስጠት ለምን አስፈለገ? ግንኙነታችን ምን መሆን አለበት? ሃሰተኞች በንስሃ ሲመለሱ ምን መደረግ አለበትና እቅበተእምነት እንዴት መከወን እንዳለበት የሚናገረ ዘጋቢ ነው!

በቅርብ ቀን ይወጣልና እያጋራችሁ ጠብቁን!

https://youtube.com/@ethiopianevangelicalreform7708
___
@nazrawi_tube