Get Mystery Box with random crypto!

እንዳንሳሳት! እግዚአብሔር ለእርሱ የሆኑትን ያውቃል። እኛ ባለ ራእይና መስራች ሆነን የምንቆርጥባ | ናዝራዊ Tube

እንዳንሳሳት!
እግዚአብሔር ለእርሱ የሆኑትን ያውቃል።

እኛ ባለ ራእይና መስራች ሆነን የምንቆርጥባትና የምንፈልጥባት ቤተስኪያንና "አገልጋዮቿ" እንጂ ቴአትር ቤትና ኮሜዲያን የሆኑት የክርስቶስ አካል አሁንም የእውነት ዓምድና መሠረት፥ የሕያው እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን ናት፡

እግዚአብሔር አሁንም ጉልበታቸውን ለባኦል ያላንበረከኩና የማሲንቆውን፣ የዋሽንቱን፣ የፀናፅሉን፣ የክራሩንና፣ የእምቢልታውን ድምፅ ሲሰሙ በዱራ ሜዳ ለቆመው ምስል የማይሰግዱ ጥቂቶች አሉት:

እግዚአብሔር ቴአትር ቤትና ኮሜዲያኖች ሳይሆን በመንፈስ ተሞልተው ቃሉን ሳይሸቅጡ የሚናገሩ አገልጋዮች አሉት:

ጥቂቶች ቢሆኑም የራሳቸውን ሳይሆን የክርስቶስን ብቻ የሚፈልጉ ትጉሃን አሉት:

የእግዚአብሔር ቤተክርስቲያን የሆነችው የክርስቶስ አካል በጥቂት የራሳቸውን ብቻ በሚፈልጉና ለራሳቸው አጀንዳ በሚሯሯጡ ሰዎች አትለካም:

እግዚአብሔር ክርስቶስ አካል ውስጥ የተጠመቁ ህያዋን ብልቶች እንጂ ቀን ጠባቂ አባሎች የሉትም:

ቤተክርስቲያን ቴአትር ቤት አገልጋዮቿ ደግሞ ኮሜዲያን እስኪሆኑ ድረስ የት ሄደን ነበር? እኛው ነን ተጠያቂዎቹ: እስከዛሬ ድረስ በአገልግሎታችን ኮሜዲያን ስናመርት ነበር ማለት ነው?

ቴአትር ቤቶችና ቅጥረኞች ኮሜዲያን ሊኖሩ ይችላሉ ነገር ግን የክርስቶስ አካል ቴአትር ቤትም አይደለችም አገልጋዮቿም ኮሜዲያን አይደሉም:

እኛ በመሰረትናትና ባለራዕይ በሆንባት ቤተስኪያን ብቻ ላይ ነው እንደፈለግነው መናገር የምንችለው እንጂ "በገዛ ደሙ በዋጃት ቤተክርስቲያን" ላይ የመጣልንን የመናገር መብትም ስልጣንም የለንም:

የክርስቶስ አካልና፣ ለጥቅማቸው አድረው ክርስቶስን ባበረሩ ግለሰቦች የሚመሩ ስብሰባዎች ለየቅል መሆናቸውን መዘንጋት የለብንም፡

መዝሙርና ስብከት የሚመስል ነገር ያለበት ቦታ ሁሉ ቤተክርስቲያን አይደለም።

ይልቃል ዳንኤል
@nazrawi_tube