Get Mystery Box with random crypto!

የተወደዳችሁ ወገኖች የጌታ ሰላም ይሁንላችሁ፤ ይብዛላችሁም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት | ናዝራዊ Tube

የተወደዳችሁ ወገኖች የጌታ ሰላም ይሁንላችሁ፤ ይብዛላችሁም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት በመሥራት ላለፉት ብዙ ዓመታት ቆይቻለሁ። በተለይ ያለፉትን ጥቂት ዓመታት ሙሉ ጊዜ ሰጥቼ ስሠራው ቆይቻለሁ። በጌታ ቸርነት ከ23 ዓመታት በኋላ ባለፈው ወር፥ ልክ የዛሬ ወር ተጠናቅቋል። እግዚአብሔር ይመስገን።

ይህ መዝገበ ቃላት ወደ 1350 ገጾችና ከ4ሺህ 800 ቃላት በላይ የያዘ፥ ለእያንዳንዱ ቃል ከምንጭ ቋንቋዎች አቻ ቃላትን፥ ትርጕምና ዝርዝር መፍቻ፥ እንዲሁም በቂ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችን ያካተተ ነው። ይህ ሥራ በተጠቃሚዎች ሁሉ፥ በተለይም በክርስቲያኖችና በአገልጋዮች እጅ ትልቅ እሴት የሚሆን መጽሐፍ ነው።

በኢትዮጵያ ይህን ሥራ ለማሳተም የእናንተ እርዳታ አስፈልጎኛል፤ ለጋስ እጃችሁንና ቸርነታችሁን እጠይቃለሁ። የgofundme አካውንቱ ሊንክ ይህ ነው፤ https://gofund.me/2c4353f8

እግዚአብሔር ይባርካችሁ፤ ለበረከትም ያድርጋችሁ። ዘላለም ነኝ።

Hello my friends. May the peace of Christ be on you. I have been working on the Amharic Bible Dictionary (ABD). The last few years were entirely dedicated to this prodigious work. It came to completion last month (exactly a month ago) after 23 years. Praise God.

The ABD is a 1350 plus pages work with over 4800 entries complete with source language equivalents, meanings, extensive definitions as well as ample Bible verse references. This work would be an asset in the hands of all users; especially Christians and ministers.

To have it printed in Ethiopia I need support, and here I am asking for your helping hands and generosity. The gofundme account link is: https://gofund.me/2c4353f8

God bless you and make you a blessing.

___
አገር ቤት ያላችሁ ይህንን ሥራ ለመደገፍ የምትወድዱ ወገኖች በብርሃን ባንክ የአካውንት ቁጥር፦
1010670778124
መላክ ትችላላችሁ።

ጌታ ይባርካችሁ።
_

Zelalem Mengistu
___