Get Mystery Box with random crypto!

ሶስት እግዚአብሔር ? የክርስትና ልዩትነት የነገረ መለኮት መፅሐፍ ቅዱሳዊ አረዳዳችን | ናዝራዊ Tube

ሶስት እግዚአብሔር ?

የክርስትና ልዩትነት የነገረ መለኮት መፅሐፍ ቅዱሳዊ አረዳዳችን ነው።ለቃሉ ታማኝ መሆን ፣ያለውን ማለት ፣ተቀበሉ ያለንን መቀበል ነው ።እንደምንፈልገው ቅዱስ ቃሉ እንዲፅፍልን አናስገድደውም ይህንን እንዲህ ቢፅፈው ጥሩ ነበር ብለን ስሁት ሙግት አንገጥምም ይልቅ ቃሉ ምን ይላል ብለን እንጠይቃለን ያለውን እናምናለን ።

የነገረ መለኮት አረዳዳችን ይህንን ታሳቢ ያደረገ ነው ። ነገረ ክርስቶስ (christology )ነገረ መንፈስ ቅዱስ (pnumatology ) ነገረ ሥላሴ (Trinity )ነገረ መፅሐፍ ቅዱስም ቢሆን ሌሎቹም በዚህ አረዳድ ያዋቀርናቸው ናቸው ።

ይህ እንዲሁ እንዳለ ስለ ነገረ ሥላሴ ሲነሳ ሁለት ነገሮች መነሳታቸው ግድ ነው ብዬ አስባለሁ ።

አንደኛው የትምርቱ እውተኛነት ነው ። መፅሐፍ ቅዱስ ውስጥ በአጥጋቢ መረጃዎች የተሰጠን አስተምህሮ ቢኖር ወይም በአጥጋቢ መረጃ የተደራጀ ትምህርት ቢኖር ነገረ ሥላሴ ነው። ከዘፈጥረት ጀምሮ እስከ ራዕይ ድረስ መረጃዎችን ( biblical data)ማቅረብ እንችላለን ።

ሁለተኛው ደግሞ ክርስቲያኖች ስለዚህ ትምርት ያላቸው መረጃ አናሳነት ነው ።ይሄ አሳሳቢው ጉዳይና ሁሉም ሊሰራበት የሚገባው አንገብጋቢ የቤት ስራ ነው ። ወደ ጉዳዬ ስመለስ ነገረ ሥላሴ ማለት ሌላ ነገር አይደለም የመፅሐፍ ቅዱሱ እግዚአብሔር ማለት ነው ። ይህንን እንዲህ ብለን ልንገልፀው እንችላለን እግዚአብሔር ሥላሴ ነው።

ይህ ማለት አንዱ እግዚአብሔር (መለኮት )ሶስት የተለያዩ አካላት እንዳሉት (distinct personality ) የተገለፀበት ነው ።እግዚአብሔር አብ እግዚአብሔር ወልድ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ !! ይህንን እኛ ፈልገን ያደረግነው ሳይሆን መፅሐፍ ቅዱስ የነገረን እውነታ ነው ።

ታዲያ የስላሴ አማኝ ያልሆኑ ሰዎች ስለ ሶስት እግዚአብሔሮች እንደምናስተምርና ይህም ትምርት ከአንድ በላይ እግዚአብሔር እንዳለን የሚያሳይ ነው በማለት ሲወነጅሉ ይታያሉ። ነገርን ከስሩ እንደሚባለው ምን ታምናላችሁ ተብለን መጠየቅ ያለብን እኛ ነን እንጂ እንዲህ ታምናላችሁ ስለዚህ እንዲህ ናችሁ ተብለን ልንፈረጅ አይገባንም።

እኛ አንዱ እግዚአብሔር ሶስት አካለት አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ አሉት አልን እንጂ ሶስት እግዚአብሔር አሉን አላልንም ።አስተምህሮተ ሥላሴ ስለ ሶስት እግዚአብሔር የሚያስተምር ሳይሆን ስለ አንድ እግዚአብሔር እንዲሁም ስለ ሶስት አካላት የሚያስተምር መፅሐፍ ቅዱሳዊ አስተምህሮ ነው ።

አንድ እግዚአብሔር አለን!

“#አንድ እግዚአብሔር አለና፥ በእግዚአብሔርና በሰውም መካከል ያለው መካከለኛው ደግሞ አንድ አለ፥ እርሱም ሰው የሆነ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው፤”
— 1ኛ ጢሞቴዎስ 2፥5

ሶስት አካላት

“እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ #በአብ #በወልድና #በመንፈስ_ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው፥ ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው፤ እነሆም እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ።”
— ማቴዎስ 28፥19-20

Girum difek
@nazrawi_tube