Get Mystery Box with random crypto!

ኤይደን ዊልሰን ቶዘር (መንፈሳዊ ስብከትን በተመለከተ የተናገሩት) ሰባኪን በሰዓሊ እመስለዋለሁ፡፡ | ናዝራዊ Tube

ኤይደን ዊልሰን ቶዘር
(መንፈሳዊ ስብከትን በተመለከተ የተናገሩት)

ሰባኪን በሰዓሊ እመስለዋለሁ፡፡ ሰዓሊ በውኃ፣ በዘይት፣ በአሸዋ፣ በድንጋይ፣ በወርቅና በመስተዋት ነው የሚሠራው፡፡ በተቃራኒው ሰባኪ የሚሠራው የሰው ልጅ ላይ ነው፡፡ ሰዓሊ አንድ ያሰበውና በልቡናው ያየው ውበት አለ፤ ያንን ነው ለማየት በስዕሉ የሚተጋው፡፡ ሰባኪ ደግሞ በልቡ የተሳለውን ክርስቶስ ነው በሰዎች ሕይወት ለመሳል የሚጥረው፡፡ ሰዓሊ የስዕል ክህሎት ሲኖረው፣ ሰባኪ መንፈስ ቅዱስ ነው ያለው፡፡ ሰዓሊው ያንን ብርሃንና መረዳት የሚቀበለው ከሌሎች ሰዓሊዎች ነው፡፡ ሰባኪ ግን በጸሎት ከአምላኩ ይቀበላል፡፡

ሰዓሊ ብሩሾች፣ መንደፊያ ሸራና ቀለም ይኖሩታል፡፡ ሰባኪ ግን ቃሎች ናቸው ያሉት፡፡ ዘጠና በመቶ አገልግሎቱ ቃላትን በመጠቀም ነው፡፡ ስለዚህ እንደ ሰዓሊ ሥራውን በሚገባ ማወቅ ይገባዋል፡፡ ብዙ ትጋትም ያስፈልገዋል፡፡ ሲጀምር ብዙ መስማት የማይገባቸው ስሕተቶች ይሠራ ይሆናል፡፡ እያደር ግን የተዋጣለት ሠራተኛ መሆኑ የማይቀር ሃቅ ነው፡፡

@nazrawi_tube