Get Mystery Box with random crypto!

ቅረበኝ፣ እዚያው ሁንና! (...ጥሞናን ለሚያውቅ፣ አሰላስሎትን ለለመደ) አባትነቱን አስበው ቢቀ | ናዝራዊ Tube

ቅረበኝ፣ እዚያው ሁንና!

(...ጥሞናን ለሚያውቅ፣ አሰላስሎትን ለለመደ)

አባትነቱን አስበው ቢቀርቡትም፣ ቅድስናው የሚያስፈራ ነው። በመገለጡ ብናውቀውም በስውርነቱ ሚስጥር ነው። በመንፈሱ ቢያድርብንም፣ በስፍራዎች ሁሉ መገኘቱ ከእኛ ውጭና በላይ ነው። ያለ እርሱ ቅርበት ህይወት የለም፣ የቅርበቱም ክብር አስፈሪ ነው። እግዚአብሔር የአንተ አይደለም፣ አንተ ግን የእርሱ ነህ። ስትቀርበው ትፈራለህ፣ ስትርቀው ትሞታለህ፣ እዚያው ሆኖ ቢቀርብህ ይሻልሃል፣ ቀርቦህም ቢርቅህ ይበጅሃል፣ እናም እግዚአብሔር ሚስጥር የሆነ ግልጥ ነው፣ ተገልጦልህም ስውር ነው። ስለዚህ ስለ እርሱ የማታውቀውን እወቅ፣ ያወቅኸውንም እንዳልጨረስክ እወቅ፣ ለገባህ ነገር በአደባባይ ስትቆም የእርሱ ጠበቃ የሆንክ እንዳይመስልህ፣ በሰው ልክ እርሱ ወረደልህ እንጂ በአምላክ ልክ ከፍ አላልክም! እናም በርሱ ሐሳብ ባህር ውስጥ መሆንን ግን አታቋርጥ ..።

ሰለሞን ጥላሁን
@nazrawi_tube