Get Mystery Box with random crypto!

አዚም ከተማ ውስጥ ሱፍ ለብሰው ሽክ ብለው ሰውን እያደነዘዙ ከሰው ያለውን ነገር ሁሉ የሚወስዱ | ናዝራዊ Tube

አዚም

ከተማ ውስጥ ሱፍ ለብሰው ሽክ ብለው ሰውን እያደነዘዙ ከሰው ያለውን ነገር ሁሉ የሚወስዱ ሰዎች ነበሩ እና አንድ ቀን አንድ የቅርብ ዘመዴን መንገድ ላይ አቁመው ለሠላምታ እጅ ሰጡት እና "ወዴት ነው የምትሄደው" አሉት፤ እርሱ ወደቤት ብሎ መለሰላቸው እና "እዚህ ከተማ ነው ምትኖረው አሉ?" አይ ከዚህ የአሥር ብር መንገድ ነው ቤቴ አላቸው። ከዛም "ስልክህን አምጣ አሉት" ሰጣቸው። "በኪስህ ያለውን ብር አምጣ" አሉት እና አሁንም ከፊተኛውም ከኃለኛውም ኪሱ ሰጣቸው እና እሱ ከሰጣቸው መልሶ ደግ ስለሆነ የትራንስፖርት አሥር ብር መልሰው ሰጡት እና "ሂድ" አሉት። እርሱም "እሺ" ብሎ በደመነፍስ ሄደ እነርሱም ከፊቱ ሸሹ እና በኪሱ ምንም እንደሌለ ያወቀው ቤት ከገባ በኃላ ነበር።

ሐዋርያው ጳውሎስ የማያስተውሉ የገላትያ አማኞችን "ማን አዚም አደረገባችሁ" ብሎ ይጠይቃቸዋል። "አዚም" የሚለውን አዲሱ መደበኛ ትርጉር "መተት" ይለዋል።
ሐዋርያው ጳውሎስ ለገላትያ ሰዎች የተሰበከው ወንጌል
የእግዚአብሔር ወንጌል፤ ክርስቶስ የገለጠለት ወንጌል፤ ወደ እግዚአብሔር የተጠሩበት ወንጌል፤ የዳኑበት ወንጌል እንደሆነ ያሳስባቸውና ይህንን የከበረውን ወንጌል ምን አይነት መተት ሰርተውባችሁ ነው የነጠቀባችሁ ብሎ ይጠይቃቸዋል።

በዚህ ክፍል "አዚም" የሚለውን ቃል እንግልዝኛው "bewitched" ይለዋል፤ ይህም ማለት በአንድ ነገር ከመጠን በላይ ተስቦ ሌላውን ነገር በትክክል ለማሰብ አለመቻል ማለት ነው።
ለምሳሌ "አንድ ወጣት በአንዲት ኮረዳ ውበት ፈዝዞ በዜብራ ላይ እንደቆመ መዘንጋት እንደማለት ነው።"

በኢየሱስ ክርስቶስ አምነን የዳንን ሰዎች በተለይ በዚህ ጊዜ በብዙ ነገር ፈዝዘን የያዝነውን እንቁ ነገር ትተን አላፊ በሆነ ነገር ላይ ልባችንን ጥለናል።
በልባችን ከተሳለው ከክርስቶስ በላይ፤ እግዚአብሔር ከገለጠልን ከወንጌሉ እውነት በላይ፤ ከአስደናቂው ከክርስቶስ መስቀል ሥራ በላይ ልባችንን ያፈዘዘው ገንዘብ፣ ዝና፣ በእርካሽ መንገድ መነጋገርያ መሆን እና ጊዜአዊ የሆኑ ነገሮች መሆኑ እጅግ የሚያሳዝን ነገር ነው።
የገላትያ ሰዎች የፈዘዙት "በሌላ ወንጌል ነው፤"
ዛሬ ላይ ልባችን ወርድ የሚያደርገው፤ አቅላችንን የሚያስተው፤ በክርስቶስ አምነን እንደዳንን እንዳናስተውል የሚያደነዝዘን ምን ይሁን?

አንባቢው ሆይ አይንህና ልብህ የፈዘዘው ምን እያዬ ነው?

ክብሩ
@nazrawi_tube