Get Mystery Box with random crypto!

ስንት አማራ መሞት አለበት? አንተ በዲያስፓራ ላይ አንዲት ኑሮህ ዘነፍ ሳይልብህ እንቅልፍህን በ | Natnael Mekonnen

ስንት አማራ መሞት አለበት?

አንተ በዲያስፓራ ላይ አንዲት ኑሮህ ዘነፍ ሳይልብህ እንቅልፍህን በሰላም ለጥጠህ ከተነሳህ በኋላ ፍሪጅህን አተራምሰህ ሆድህ እስኪወጠር ከበላህ በኋላ ፌስቡክ ላይ ተጥደህ ምንም ትርጉም በሌለው ጦርነት ያለቁትን የድሀ ገበሬ ልጆች "የጀግና ሞት ነው የሞተው" "ታጋይ ይሞታል እንጂ ትግል አይሞትም" እና ዝባዝንኬ ተረቶችን እየቸከቸኩ ከፎቶ ጋር አድርጎ እየለጠፉ ማቅራራት እና የአዞ እንባ እያነቡ ያዘኑ መምሰል ለአማራው ማሰብ ሳይሆን በደሀ ነፍስ ማላገጥ ነው፡፡

ይልቅስ የአማራው ህዝብ ጉዳይ ይቆረቁረኛል ስለዚህ ጦርነት መፍትሄ ነው ብለህ ከልብህ ካመንክ ዲያስፓራ ላይ ተጎልተህ እያቅራራህ እና እየፎከረክ የደሀ ገበሬ ልጆች አንተ ለምትመኘው ስልጣን ወይንም ለውጥ ህይወታቸውን እየገበሩ እንዲያመጡልህ በየሶሻል ሚዲያው መቀስቀስ ሳይሆን፤ ወያኔ ካለህና የምር ለህዝብ ተቆርቋሪ ነኝ ብለህ የምታስብ ከሆነ ኑሮህን እርግፍ አድርገህ ጥለህ ተነስተህ ጫካ ገብተህ ዲሞትፎር እና ክላሽህን ተሽከምህ እየተዋጋህ በተግባር አሳየኝ እንጂ ፌስቡክ ላይ ጀግና ለመምሰል አታቅራራብኝ፡፡

አለበለዚያ አንተ ቅልጥጥ ያለ የተደላደለ ኑሮህን እየኖርክ ደሀው ገበሬ ህይወቱን እየገበረ፤ እየደማና እየቆሰለ፤ አካሉ እየጎደለ፤ ልጆቼን ዛሬ ደግሞ የት ልደብቅ እያለ እየተጨነቀ፤ ቤት ንብረቱ እየወደመበት፤ ከቀየው ሳይወድ በግዱ እየተሰደደ፤ በረሀብ እና በቸነፈር እየተጠበሰ እና በጦርነት ነበልባል በየቀኑ እየተለበለበ እስካሁን ያሳላፈቻው አሰቃቂ ህይወቶች ምንም ሳያሳዝኑህ ዛሬም ሶፋ ላይ ተጎልተህ ቦርጭህን እያሻሸህ ለዳግም ጦርነት ስትቀሰቅሰው እያዘንክለት እና እያሰብክለት ሳይሆን ዘላለማዊ ሲኦል ህይወቱን እንዲገፋ እየተመኘህለት እንደሆነ እውቀው፡፡

ለመሆኑ የአንተ የስልጣን ጥማት፤ አሊያም የንዋይ ፍቅር፤ አሊያም አብይ አህመድ ላይ ያለህ ጥላቻ ከውስጥህ እስኪወጣ ድረስ ስንት አማራ መሞት አለበት?

ለማንኛውም በድጋሚ በቅርቡ ህይወቱ ላለፈው ሻለቃ ውብአንተ እና በዚህ ጦርነት ውስጥ ህይወታቸውን ላጡ በሙሉ አላህ ፈጣሪ በገነት ያኑረው፡፡