Get Mystery Box with random crypto!

በሀሰት ከሚሰራጩ አፍራሽ ተልዕኮዎች እንጠንቀቅ። #Ethiopia : የአማራ ህዝብ በከፈለው ወደ | Natnael Mekonnen

በሀሰት ከሚሰራጩ አፍራሽ ተልዕኮዎች እንጠንቀቅ።

#Ethiopia : የአማራ ህዝብ በከፈለው ወደር የለሽ ተጋድሎ ያስመዘገበውን ድል በመቀልበስ ለጠላቶቹ አሳልፈው በመስጠት ለዳግም ባርነት ሊዳርጉት የውስጥ እና የውጭ ሃይሎች ሲሰሩ መቆየታቸው የሚታወቅ ነው። አማራውን ለማዋረድ ተቀናጅተው እየሰሩ የሚገኙ እነዚህ ሃይሎች በተለያዩ ጊዜያት የውሸት ሰነዶችን እያዘጋጁ ሲያሰራጩ የነበረ ሲሆን ዛሬም እንደትናንቱ መንግስት እውቅና የሰጣቸውን የምንጊዜም የኢትዮጵያ ጀግኖች የሆኑትን የአማራ ፋኖዎች እርምጃ ሊወስድ መሆኑን የሚገልጽ “የኦፕሬሽናል አፈጻጸም ዝርዝር ግዳጅ” የሚል የዳቦ ስም የሰጡት የበሬ ወለደ የፈጠራ ሰነድ በማሰራጨት ላይ ይገኛሉ።

የአማራን ህዝብ እንደ ህዝብ ኢትዮጵያን እንደ አገር ፊት ለፊት ገጥሞ ማሸነፍ እንደማይችል የተረዳው አሸባሪው ትህነግና ወኪሎቹ እያሰራጩት ያለው የፈጠራ ሰነድ የአማራ ክልል መንግስት የማያውቀው መሆኑን እየገለጽን ጠላት በቀጣይነትም በፈጠራ እና ውሸት የተሞሉ ሰነዶችን እያዘጋጀ ማሰራጨቱን መቀጠሉ አይቀሬ በመሆኑ መላው ሰላም ወዳድ የሆነው የክልላችን ህዝብ ከመሰል የፈጠራ ሰነዶች እራሱን እንዲጠብቅ እናሳስባለን።

የህዝባችን ተደጋጋሚ ጥያቄ የሆነውን የሰላም እና ደህንነት ጥያቄ ለመመለስ ምልዓተ ህዝባችንን በማሳተፍ የህግ የበላይነትን የማረጋገጥ እርምጃ እየወሰደ የሚገኝ ሲሆን በዚህም እርምጃ አንጸባራቂ ድል ተገኝቷል። ህዝባችን ከጸጥታ አካላት ጎን በመቆም ለዘመቻው መሳካት አኩሪ ተጋድሎ እያበረከተ የሚገኝ ሲሆን ይኸንን ትብብሩን አጠናክሮ እንዲቀጥል የክልል መንግስት በአክብሮት ያሳስባል።

የአማራ ፓሊስ ኮሚሽን