Get Mystery Box with random crypto!

አኽላቃችን አል_በይሀቂ  ሹዐቡል_ኢማን ላይ እንደዘገቡት አቡ-ደርዳእ የሚባሉት ታላቅ ሰሓቢይ  ر | Muslim Students

አኽላቃችን

አል_በይሀቂ  ሹዐቡል_ኢማን ላይ
እንደዘገቡት አቡ-ደርዳእ የሚባሉት
ታላቅ ሰሓቢይ  رضي الله عنه


አንድ ሌሊት ላይ ለይል እየሰገዱ
የሚከተለውን ዱዓእ ብቻ እየደጋገሙ
ለሊቱ ነጋ፣ (አሏህ ሆይ፦ ውጫዊ
ገጽታንዬን/አፈጣጠሬን እንዳሳመርከው
ሁሉ ስነ-ምግባሬንም አሳምርልኝ)

በማግስቱ ባለቤታቸው "የደርዳእ
አባት ሆይ፥ምነው ማታ ስለ መልካም
ስነ-ምግባር ብቻ ዱዓእ እያደረግክ አደርክ?!"

አለቻቸው። እሳቸውም "የደርዳእ እናት
ሆይ፥ ሙስሊም ስነ-ምግባሩ እያማረ..
እያማረ ሲሄድ መጨረሻ ላይ መልካም
ስነ-ምግባሩ ጀነት እንዲገባ ያደርገዋል፣

ስነ-ምግባሩ  እየተበላሸ... እየተበላሸ..
ሲሄድ  ደግሞ  መጨረሻ  ላይ  የጀሀነም
እሳት  ውስጥ  እንዲገባ ያደርገዋል..."
ብለው መለሱላት።

አሏህ አኽላቃችንን ያሳምርልን፣
እርሱና የአዕምሮ ባለቤቶች ከሚጠሉት
ዓይነት አኽላቅ በሙሉ ያርቀን።

መልካም አኽላቅ ይህን የላቀ ደረጃ
የሚያስገኘው  ለብዙ  መልካም ነገር
ሰበብ ስለሚሆን ነው።

መልካም ስነ-ምግባራችን ብዙዎች
ዲናችንን እንዲወዱ ያደርጋል፣ በህይወት
እያለንም ይሁን ከሞትን በኋላ ያስታወሱን
ሁሉ ዱዓእ ያደርጉልናል።

መጥፎ  ስነ-ምግባር  ደግሞ  ከዚህ
በተቃራኒ ብዙ ችግሮችን ያስከትላል።

ስለዚህ ሙስሊሞች ሆይ፥ ባላችሁበትና
በሄዳችሁበት ሁሉ መልካም ስነ-ምግባርን
ተላበሱ! ትሁት፣ ቅን፣ ታጋሽና ቻይ፣ አዛኝ፣
ለጋስና ታታሪ፣ ታላቅን አክባሪና ታናሽን
መካሪ ወዘተ እንሁን።

ይሄኔ አሏህ ይወደናል፣ ትክክለኛ የነቢዩ ‌‎ﷺ ተከታይም  እንሆናለን፣  ነገ በኣኺራም
ከርሳቸው  ቅርብና  ጎረቤት  የመሆንን
እድል እናገኛለን!

አሏህ ሆይ፥ ውጫዊ ገጽታዬን/ አፈጣጠሬን እንዳሳመርከው ሁሉ
ስነ-ምግባሬንም አሳምርልኝ!

አሏህ በተከበረው ቃሉ እንዲህ ይላል:-

وَتَزَوَّدُوا فَإِنَّ خَيْرَ الزَّادِ التَّقْوَىٰ ۚ وَاتَّقُونِ
يَا أُولِي الْأَلْبَابِ

"ስንቅ ያዙ፤ ከስንቆች ሁሉ በላጩ አሏህን
መፍራት ነው፤ የአእምሮ/ የልብ ባለቤቶች
ሆይ ፍሩኝ" ሱረቱል በቀራ /197
                ↷⇣ ⇣↷