Get Mystery Box with random crypto!

ያጠፋችሁ ነበር! ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦ ﴿وَالَّذِي نَفْسِي بِيَدِهِ، | Muslim Students

ያጠፋችሁ ነበር!

ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦

﴿وَالَّذِي نَفْسِي بِيَدِهِ، لَوْ لَمْ تُذْنِبُوا لَذَهَبَ اللَّهُ بِكُمْ، وَلَجَاءَ بِقَوْمٍ يُذْنِبُونَ، فَيَسْتَغْفِرُونَ اللَّهَ فَيَغْفِرُ لَهُمْ﴾

“ነፍሴ በእጁ በሆነችው አላህ እምላለሁ!  እናንተ ሀጢያት የማትፈፅሙ ቢሆን ኖሮ አላህ ያጠፋችሁ ነበር። ከዛ ሀጢያት የሚፈፅሙ ህዝቦችን ያመጣና በሀጢያታቸው ምክንያት አላህን ምህረት ይጠይቁታል እሱም ይምራቸዋል።”

ሙስሊም ዘግበውታል: 2749

ሰለዋት አውርድ!  አድራሽ አለውና!

ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦

﴿إِنَّ لِلَّهِ مَلَائِكَةً سَيَّاحِينَ فِي الْأَرْضِ يُبَلِّغُونِي مِنْ أُمَّتِيَ السَّلَام﴾

“የህዝቦቼን ሰላምታ ለእኔ የሚያደርሱ በምድር ተንቀሳቃሽ የአላህ መላኢካዎች አሉ።”

ሲልሲለቱ አሶሂሃ: 6853