Get Mystery Box with random crypto!

✿𝗠𝗨𝗦𝗟𝗜𝗠 ነን﷽

የቴሌግራም ቻናል አርማ muslimchannel2 — ✿𝗠𝗨𝗦𝗟𝗜𝗠 ነን﷽ 𝗠
የቴሌግራም ቻናል አርማ muslimchannel2 — ✿𝗠𝗨𝗦𝗟𝗜𝗠 ነን﷽
የሰርጥ አድራሻ: @muslimchannel2
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 3.79K
የሰርጥ መግለጫ

✅:አላማው ˙ እንዴት የኢስላማዊ አስተምህሮት ግንዛቤን መጨመር እንችላለን።
ᘛ በሌላም በኩል࿐
▮ሀዲስ📚
▮በድምፅ ትምህርቶች🎤
▮የቁርአን ቲላዋ📖
▮አጫጭር ትምህርቶች📝
▮ከታሪክ ማህደር📜
▮ጠቃሚ አፖች📲
▮ሌላም. . .📧
ᘛ ወደ ግሩፓችን ይቀላቀሉ ✓
⚘ @Muslim_group2 ⚘
─────⊱◈🌟◈⊰─────
📬:አስተያየት ༻
「 @Muslim_comment_bot 」

Ratings & Reviews

2.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-09-02 06:00:39
┏ ~የጁምዐ ግብዣ~
┃▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
┣ :ሱራህ አል-ከህፍ
┃▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
┣ :ዓፊፍ ሙሀመድ ታጅ
┃▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
┣ :ኢትዩጵያ , ወሎ , ኬሚሴ ኡስታዝ
┃▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
┣ :19.8MB
┃▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

#SHARE_THE_خير
220 views༺ رمـــــص۪۪۪۪۪۪۪۪۪۪۪۪۪۪۪۪۪۪۪۪۬ـــــــــــــا۟۟۟۟۟۟۟۟۟۟۟۟۟۟۟۟ݩے𝕧, 03:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 21:11:16 ~አል-ሙጊራህ ኢብኑ ሹዕበህ(ረዲየሏሁ አንህ)~
▭▬▭▬▭▬▭▬▭▬▭▬▭▬▭▬▭▬▭

እጅግ በጣም ብልሃተኛው ሶሃባ

:መልካም አስተሳሰብ የነበረው ሰው በመሆኑ በስፋት ይታወቃል። እርሱን አንድ ችግር አያጋጥመውም ለዚያ ችግሩ መውጫና ማምለጫ የሚያገኝለት ቢሆን እንጂ። ሁለት የሚያምታቱ አማራጮች ቢቀርቡለት ከሁለቱ የተሻለውንና በላጩን በመምረጥ ማንም አያክለውም። በዐረብ ጐሣዎች ሁሉ #በብልህነቱና #በዘዴኛነቱ የታወቀ ነው።
➥ይህ ሰው አል-ሙጊረህ ኢብኑ ሹዕበህ (ረዲየሏሁ አንህ) ሲሆን ግዙፍ ተክለ ሰውነትና ሰፊ ትከሻ እንደነበረውም ተወስቷል።

:የመጀመሪያው ኸሊፋ አቡበክር (ረዲየሏሁ አንህ) ከሞቱ በኋላ ኃላፊነቱን የተረከቡት ዑመር ኢብኑ አል-ኸጧብን ሰዎች “የአላህ መልዕክተኛ ምትክ ምትክ” (ኸሊፈቱል ኸሊፈቱ ሩሱሉላህ) በሚል የተራዘመ አጠራር ይጠሯቸው ጀመር። በዚህ ጊዜ
ዑመር “ይህ የተራዘመና የማይመች አጠራር ነው። አንድ ሰው ለኸሊፋነት በተመረጠ ጊዜ ሁሉ እንዲህ እያረዘምነው ልንሄድ አይገባም። እናንተ ምእመናን
ስትሆኑ እኔ ደግሞ አዛዥችሁ (አሚራችሁ) ነኝ" አሉ።


:#አል-ሙጊራህ_ኢብኑ_ሹዕበህ (ረዲየሏሁ አንህ) በዚህ ጊዜ እንዲህ አለ፦“ስለዚህ እርስዎ የምእመናን አዛዥ ነዎት ማለት ነው”። በዚህም ዑመርን (ረዲየሏሁ አንህ) የምእመናን አዛዥ (#አሚረል_ሙእሚኒን) ብሎ ለመጥራት የመጀመሪያው ሰው ሆነ።

━─━────༺༻────━─━

:ዑመር (ረዲየሏሁ አንህ) አል-ሙጊራን የባሕሬን ገዥ አድርገው ሾሙት። እዚያ ብዛት ያላቸው የማጂ (ዞሮአስተር) ሃይማኖት ተከታዮች ይገኙ ነበር። እነርሱም አል-ሙጊራን (ረዲየሏሁ አንህ) በጣም ይጠሉት ስለነበር የተለያዩ ተንኮሎችን በመሸረብ ኸሊፋው ከስልጣኑ እንዲያስወግዱት ይጥሩ ነበር። በዚህ ሂደት ላይ ሙከራቸው እንዳይከሽፍና ዑመር (ረዲየሏሁ አንህ) አል-ሙጊራን (ረዲየሏሁ አንህ) ወደ ቦታው መልሰው እንዳያስቀምጡት በጣም ጥንቃቄ ያደርጉም ነበር። በአንድ ወቅት አንድ መቶ ሺህ ዲርሃም ካሰባሰቡ በኋላ መሪያቸው ያንን ገንዘብ ወደ ዑመር (ረዲየሏሁ አንህ) ይዞ በመሄድ እንዲህ አለ፡-
“ይህ አል-ሙጊራህ የሰረቀው ገንዘብ ሲሆን እኔ በአደራ እንዳስቀምጥለት የሰጠኝ ነው።”
➣ዑመር (ረዲየሏሁ አንህ) አል-ሙጊራን (ረዲየሏሁ አንህ) ካስጠሩት በኋላ ስለገንዘቡ ጠየቁት።
ብልሃተኛው አል-ሙጊረህ (ረዲየሏሁ አንህ) እንዲህ አለ፡-ይህ መሪ ዋሽቷል። ገንዘቡ ሁለት መቶ ሺህ ዲርሃም ነው። “ለምንድን ነው የሰረቅከው?" በማለት ዑመር (ረዲየሏሁ አንህ) ጠየቁት። “ብዙ ልጆች ስላሉኝ ነው” አለ አል-ሙጊረህ (ረዲየሏሁ አንህ)። ይህን የሰማው መሪ በድንጋጤ እየተርበተበተ አል-ሙጊረህ እርሱ ዘንድ ምንም ዓይነት ገንዘብ እንዳላስቀመጠ እየማለ ይናገር ጀመር።
➥ዑመር (ረዲየሏሁ አንህ) አል-ሙጊራን (ረዲየሏሁ አንህ) ትኩር አድርገው ከተመለከቱት በኋላ
“ለምንድን ነው እንዲህ ያደረከው?” አሉት።
መልሱ አጭር ነበር፡- “ላዋርደው ፈልጌ ነው።”

━─━────༺༻────━─━

:የአል-ሙጊራ (ረዲየሏሁ አንህ) የዕድሜ ልክ ጓደኛ ቁበይሰህ ኢብኑ ጃቢር እንዲህ ይላል➘

እኔ የአል-ሙጊረህ ኢብኑ ሹዕበህ ጓደኛ ነበርኩ። በአንድ ከተማ ውስጥ ስምንት የመውጫ በሮች ቢኖሩና በማንኛውም በር ለመውጣት ዘዴኛና አታላይ መሆን ቢያስፈልግ አል-ሙጊረህ ኢብኑ ሹዕበህ በሁሉም በሮች መውጣት ይችላል
اجيـــــب

:ሀያቱ ሶሃባ
┊  ┊  ┊  ┊
┊  ┊  ┊  ✿
┊  ┊  ❀
┊  ✿
❀               
╠═════ •『 ﷽ 』• ═════╣
┣𝐆𝐫𝐨𝐮𝐩•
@Muslim_group2      
┣━━━━━━╗ ╔━━━━━━━⎙
┣𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥•
@Muslimchannel2
╠═══════•❁❀❁•══════╣
#SHARE_The_خير
1.3K views༺ رمـــــص۪۪۪۪۪۪۪۪۪۪۪۪۪۪۪۪۪۪۪۪۬ـــــــــــــا۟۟۟۟۟۟۟۟۟۟۟۟۟۟۟۟ݩے𝕧, 18:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 18:36:15
:ለመጀመሪያ ጊዜ ለ ዑመር ኢብኑ አል-ኸጧብ(ረዲየሏሁ አንህ) "አሚረል ሙዕሚኒን(የሙዕሚኖች አዛዥ)" ብሎ የጠራቸው ማን ነው
Anonymous Quiz
19%
አቢ ሙሳ አል-ዓሽዐሪይ(ረዲየሏሁ አንህ)
22%
አቡ ደርዳዕ(ረዲየሏሁ አንህ)
21%
አል-ሙጊራህ ኢብኑ ሹዕባህ(ረዲየሏሁ አንህ)
38%
ዓሊይ (ረዲየሏሁ አንህ)
113 voters983 views༺ رمـــــص۪۪۪۪۪۪۪۪۪۪۪۪۪۪۪۪۪۪۪۪۬ـــــــــــــا۟۟۟۟۟۟۟۟۟۟۟۟۟۟۟۟ݩے𝕧, 15:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 18:00:12 ~የወሰደ መልሶ ይሰጣል~
▭▬▭▬▭▬▭▬▭▬▭▬
:አብሽር ሐቢቢ ተስፋ አድርግ፡፡ ይወስድብኛል ብለህ ያልገመትከውን ነገር የወሰደብህ አላህ ይሰጠኛል ብለህ ያልገመትከውንም እሱ ራሱ ይሰጥሃል። ችግራችን ሲወስድበን ወሰደብን ብለን እናስወራለን፡፡ ሲሰጠን ግን ሰጠን ብለን አንናገርም፡፡ በመውሰዱ እንዳመንነው ሁሉ
በመስጠቱም እንመን፡፡ አዎን መልሶ ይሰጠናል!!!
┊  ┊  ┊  ┊
┊  ┊  ┊  ✿
┊  ┊  ❀
┊  ✿
❀                
╠═════ •『 ﷽ 』• ═════╣
┣𝐆𝐫𝐨𝐮𝐩•
@Muslim_group2      
┣━━━━━━╗ ╔━━━━━━━⎙
┣𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥•
@Muslimchannel2
╠═══════•❁❀❁•══════╣
#SHARE_The_خير
1.3K views ︎رمـــــص۪۪۪۪۪۪۪۪۪۪۪۪۪۪۪۪۪۬ـــــــــــــاݩے𝕧, 15:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 05:58:36
┏ ~የጭስ ምዕራፍ~
┃▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
┣ :ገራሚ የቁርዐን ቲላዋ
┃▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
┣ :የጭስ ምዕራፍ | سورة الدخان
┃▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
┣ :በአማርኛ ትርጉም
┃▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
┣ :5.8 MB
┃▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
#SHARE_THE_خير
653 views ︎رمـــــص۪۪۪۪۪۪۪۪۪۪۪۪۪۪۪۪۪۬ـــــــــــــاݩے𝕧, 02:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 16:40:25
~በባህሮች መካከል ግርዶሽ መኖር ~
▭▬▭▬▭▬▭▬▭▬▭▬▭▬▭▬
የስነ ባህር ጥናት

:ጠበብት ካረጋገጡት እውነታ ውስጥ ሁለት የውሃ ክፍሎች ባላቸው የተለያዩ የጨው መጠን የሙቀት ደረጃ እና የእፍጋት(ዴንሲቲ) ደረጃ መጠን
መቀላቀል እንደማይችሉ አረጋግጠዋል።

➠የሜዲትራኒያን ባህርና የአትላንቲክ ውቅያኖስ በነዚህ ከላይ በተገለፁት ምክንያቶች ሳቢያ እንደማይቀላቀሉ ይህ #እውነታ ተስተውሏል።

:በእርግጥ በጣፋጭ ውሃና በጨውማ ውሃ መካከል ግርዶሽ መኖሩንና ይህም እውነታ ከ1400 ዓመታት በፊት
#በቁርዐን ተገልጿል፡፡

:مَرجَ الْبَحرَينِ يَلْتَقِيَانِ

:ሁለቱን ባሕሮች የሚገናኙ ሲኾኑ ለቀቃቸው፡፡

:بَيْنَهُمَا بَرْزَخٌ لَّا يَبْغِيَانِ

:(እንዳይዋሐዱ) በመካከላቸው ጋራጅ አልለ፡፡ (አንዱ ባንዱ ላይ) ወሰን አያልፉም፡፡55:19-20

۞ وهو الَّذي مرج الْبحرينِ هَٰذا عذبٌ فُراتٌ وهَٰذا ملحٌ أُجاجٌ وجعل بينهُما برزخًا وحجرًا مَّحجُورًا

:እርሱም ያ ሁለቱን ባሕሮች አጎራብቶ የለቀቀ ነው፡፡ ይህ ጥምን የሚቆርጥ ጣፋጭ ነው፡፡ ይህም የሚመረግግ ጨው ነው፡፡ በመካከላቸውም (ከመቀላቀል) መለያንና የተከለለን ክልል ያደረገ ነው፡፡25:53

:
ይህን አስደናቂ ሁኔታ በባህረ ሰላጤው የሚገኙ የሉል አስጋሪዎች የሚያውቁት የተፈጥሮ ክስተት ነው፡፡በአረቢያው ባህረ ሰላጤ ውስጥ ከሚገኙ ጨዋማ ውሃዎች ውስጥ ከአራት እስከ ስድስት ሜትር በታች ጣፋጭ ውሃ እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡በዚህም የረጅም ወራት የሉል ፍለጋ የባህር ቆይታቸው ከነዚህ ምንጮች ጥማቸውን እንደሚያረኩ ገልፀዋል፡፡ከነዚህ ምንጮች ውስጥ በሳዑዲ አረቢያ ሰሜን ምስራቅ በጁበይል ከተማ የሚገኘው ዐይን ኢግቢሳ የሚጠቀስ ነው፡፡
1.3K views ︎رمـــــص۪۪۪۪۪۪۪۪۪۪۪۪۪۪۪۪۪۬ـــــــــــــاݩے𝕧, 13:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 06:37:43 ~የቁርዐን ቲላዋ ስብስቦች~
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
:ቲላወቱል ኻሺዐ(التلاوت الخاشع)
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
:99.7 MB
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
ማሂር
ሚሻሪ
ያስር
ሱደይስ
ኻሊድ አል-ጀሊል
ኢድሪስ
መንሱር ሳልሚ
ሃዛዕ አል-ቡሉሺ
ሙሀመድ
ሃኒ አሪፋዒይ
አብዱል ዓዚዝ
አብዱል ባሲጥ
ሰልማን
አህመድ አጀሚይ

┊  ┊  ┊  ┊
┊  ┊  ┊  ✿
┊  ┊  ❀
┊  ✿
❀               
1.1K views ︎رمـــــص۪۪۪۪۪۪۪۪۪۪۪۪۪۪۪۪۪۬ـــــــــــــاݩے𝕧, 03:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 21:35:48 ~መከራና ችግር~
▭▬▭▬▭▬▭▬▭▬
:አትፍራ ወዳጄ! ልብ በል ሐቢቢ‥. አላህ (ሱብሃነሁ) ከዋለልን ፀጋዎች አንፃር ስናይ የመከራ ዕድሜ ትንሽ ነው፡፡ እድሜ ልኩን በምድር ላይ ሲንከራተት ኖሮ የሞተ ሰው የለም፡፡ ዱኒያ አንድ ቀን ብታስለቅሰን አንድ ቀን ልትስቅልን ግድ ነው።

:የሚገርመው ፍፁም ፍትሃዊ የሆነ ጌታችን አላህ (ሱብሃነሁ ወተዐላ) በሷ ላይ በሚያገኘን ትንሽም ሆነ ትልቅ ችግር ምንዳ ለገሰን፡፡ የመከራ
#ምንዳው #በጤናና #በድሎት ጊዜ ከሚያገኙት በላይ
ነው፡፡ ከሱ የሚገኘው ልምድም ከየትኛው የህይወት ትምህርት በላይ ነው፤ ጥቅሙም ከማንኛውም ሀብት የላቀ ነው~

:አንድ ቀን የሆነ ሰው
#ኢማሙ_አሽሻፊዒን “ፈተና ከበዛበትና እርጋታ ከሞለበት ህይወት ለአንድ ሰው የትኛው ይሻለዋል?” በማለት ጠየቃቸው:: ኢማሙም እንዲህ በማለት መለሡ➘

▮ፈተና የበዛበት ህይወት ይሻለዋል: ምክንያቱም አላህ ነቢዩ ኑህን፣ ነቢዩ ኢብራሂምን፣ ነቢዩ ሙሣን፣ ነቢዩ ዒሣን እና ነቢያችን ሙሐመድን ﷺ ፈተናቸው። በመጨረሻም የተረጋጋ ህይወት ሠጣቸው▮
┊  ┊  ┊  ┊
┊  ┊  ┊  ✿
┊  ┊  ❀
┊  ✿
❀                
╠═════ •『 ﷽ 』• ═════╣
┣𝐆𝐫𝐨𝐮𝐩•
@Muslim_group2      
┣━━━━━━╗ ╔━━━━━━━⎙
┣𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥•
@Muslimchannel2
╠═══════•❁❀❁•══════╣
#SHARE_The_خير
2.0K views ︎رمـــــص۪۪۪۪۪۪۪۪۪۪۪۪۪۪۪۪۪۬ـــــــــــــاݩے𝕧, 18:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 17:43:01 ~የትም የሌለ ሰንሰለት~
▭▬▭▬▭▬▭▬▭▬▭
┏ሙስሊም የቡኻሪ ተማሪ
┃➘
┣ቡኻሪ የኢማሙ አህመድ ተማሪ
┃➘
┣ኢማሙ አህመድ የሻፊዒይ ተማሪ
┃➘
┣ኢማሙ አል ሻፊዒይ የማሊክ ተማሪ
┃➘
┣ኢማሙ ማሊክ የናፊዕ ተማሪ
┃➘
┣ናፊዕ የዐብደላህ ኢብኑ ዑመር  ተማሪ
┃➘
╚አብደላህ ኢብኑ ዑመር የረሱል ﷺ ተማሪ

የትኛውም ህዝብ(ኡማ) ላይ ሊገኝ
የማይችል ሰንሰለት

الحمد لله على نعمة الإسلام والسنة~
┊  ┊  ┊  ┊
┊  ┊  ┊  ✿
┊  ┊  ❀
┊  ✿
❀                
╠═════ •『 ﷽ 』• ═════╣
┣𝐆𝐫𝐨𝐮𝐩•
@Muslim_group2      
┣━━━━━━╗ ╔━━━━━━━⎙
┣𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥•
@Muslimchannel2
╠═══════•❁❀❁•══════╣
#SHARE_The_خير
1.7K views ︎رمـــــص۪۪۪۪۪۪۪۪۪۪۪۪۪۪۪۪۪۬ـــــــــــــاݩے𝕧, 14:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 06:19:04 ~ከነብዩ ﷺ ተዓምራት~
▭▬▭▬▭▬▭▬▭▬▭▬


ነብዩ ﷺ ታላቅ አውሎ ንፋስ እንደሚመጣ ማስጠንቀቃቸው~~~

:የአላህ ነቢይ ﷺ ተቡክ እያሉ ኃያል አውሎ ነፋስ እንደሚከሰትና በተቻላቸው መጠን ከፍ ያለ ሥፍራ ላይ እንዳይሆኑና በያሉበት ሥፍራም ከመቀመጥ(መተኛት)በቀር እንዳይቆሙ ባልደረቦቻቸውን አስጠነቀቁ። ኢማም ሙስሊም(የአላህ እዝነት አይለያቸውና) በሶሒሕ ኪታባቸው አቡ ሓሚድ (ረዲየሏሁ አንህ)እንደሚከተለው ማለታቸውን ዘግበዋል➘

▮"ተቡክ እስክንደርስ ድረስ ጉዟችንን ቀጠልን። እዚያ እንደደረስን "ዛሬ ምሽት ኃያል አውሎ ንፈስ ስለሚመጣ ከመካከላችሁ ማንም ሰው እንዳይቆም ፤ ግመላችሁንም በሚገባ እስሩ"በማለት የአላህ መልዕክተኛ ﷺ አስጠነቀቁ ። ልክ እንደተናገሩትም አውሎ ንፋሱ ሲመጣ አንድ ሰው ቆመ። በዚያ ጊዜም አውሎ ነፋሱ ሰውየውን ተሸክሞ ከወሰደው በኃላ 'ጢይ' በተሰኘ ተራራ አጠገብ ጣለው።▮

ሙክተሰር ሙስሊም ሐዲስ ቁ.1543~
┊  ┊  ┊  ┊
┊  ┊  ┊  ✿
┊  ┊  ❀
┊  ✿
❀                
╠═════ •『 ﷽ 』• ═════╣
┣𝐆𝐫𝐨𝐮𝐩•
@Muslim_group2      
┣━━━━━━╗ ╔━━━━━━━⎙
┣𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥•
@Muslimchannel2
╠═══════•❁❀❁•══════╣

#SHARE_The_خير
1.9K views ︎رمـــــص۪۪۪۪۪۪۪۪۪۪۪۪۪۪۪۪۪۬ـــــــــــــاݩے𝕧, 03:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ