Get Mystery Box with random crypto!

ፖሊስ እየወሰዳት ነው ! የመምህርቷን ፎቶ እዚህ ሰፈር እንዳየሁት የወሎ ወንድሜ Fisseha Me | Muktarovich Ousmanova

ፖሊስ እየወሰዳት ነው !

የመምህርቷን ፎቶ እዚህ ሰፈር እንዳየሁት የወሎ ወንድሜ Fisseha Melese ስልኳን አቀበለኝ እና ደወልኩላት። በወሎ ዩኒቨርሲቲ በመምህርነት እና በተመራማሪነት 12 አመት መስራቷን ነገረችኝ ።
እኔ ለምን ደሞዝሽ ተቋረጠ ?

እሷ በህመም ምክንያት ረዘም ላለ ጊዜ ስራ ስላቋረጥኩ ።

እኔ አሁን በምን ሁኔታ ላይ ነሽ ?

እሷ አሁን አንተ ስታናግረኝ ፖሊስ መለመን አትችይም ብሎ በመኪና ጭኖ እየወሰደኝ ነው ።መኪና ላይ ሁኘ ነው የማናግርህ።
እኔ የት አካባቢ ነበርሽ ?

እሷ አዲስ አበባ መገናኛ አካባቢ ነበርኩ ።
እኔ ወደ የት ነው የሚወስዱሽ ?

እሷ ወደ የት እንደሚወስዱኝ አላውቅም ።
ስልኩ ተቋረጠ ።

Via ተስፋዬ ወልደስላሴ