Get Mystery Box with random crypto!

የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የዚህችን ግለሰብ ጉዳይ 'ወደ ወሎ ዩኒቨርስቲ ደውዬ እውነታውን አጣርቻለው' በ | Muktarovich Ousmanova

የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የዚህችን ግለሰብ ጉዳይ "ወደ ወሎ ዩኒቨርስቲ ደውዬ እውነታውን አጣርቻለው" በማለት የሰራው ዘገባ እጅግ አሳዛኝና አሳፋሪ ነው
ይህች እህት "ወሎ ዩኒቨርስቲ 12 አመት ልምድ አለኝ" አለች እንጂ ዩኒቨርስቲው አባረረኝ ወይም ከስራ ገበታ አፈናቀለኝ አላለችም፣ በማንኛውም ሁኔታ በተቋሙ ላይ ክስና አሉባልታ አላነሳችም።

በመቀጠል ወደ ዩኒቨርስቲው አንድ ኋላፊ ተደውሎ የዚህችን ሴት ችግር ያስረዳበት ቋንቋና በሚስጥር ሊጠበቅላት የሚገባ የግል ጉዳይ "የዐዕምሮ ታማሚ ነች" በመቀጠልም "የማህፀን ህመም አለብኝ ምናምን ትል ነበር" እያለ ከአንድ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም የማይጠበቅ ቋንቋዎችን እየተጠቀመ ተቋሙን ባልከሰሰችበት ሁኔታ የግለሰቧን ሚስጥሮች ሲያዝረከርክ ነበር

12 አመት ያገለገለችንና ስራ ማጣቷን ብቻ ገልፃ ትብብር የጠየቀችን ሴት በብሄራዊ የቴሌቪዥን ጣቢያ "የአዕምሮ ታማሚ ነች" እና "የማህፀን ህመም አለብኝ ምናምን ትል ነበር" የሚሉ መልዕክቶችን ለአደባባይ ማስተላለፍ የተፈለገው የትኛውን ሃገራዊ መልካችንን ለመከላከል ነው?

ይህ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የወረደ ዘገባ እና የወሎ ዩኒቨርስቲ ሃላፊዎች መረን የቃላት አጠቃቀምና ባልተከሰሱበት ጉዳይ ራስን የመከላከል ጥድፊያ እጅግ የሚያሳዝን ነው

ይህች እህታችን የስራ ቦታቸውን ለመልቀቅ ያስገደዳቸውና እንደተባለውም የዐዕምሮ ህመም ገጥሟቸው ከሆነ ለህመማቸው መነሻና መባባስ የሆኑ ምክንያቶች ከዩኒቨርስቲው የስራ ከባቢ የተወለደ ቢሆንስ? የሸሹት ለጤናቸው ቢሆንስ?
ምንጭ: ሙሉቃል
Fact Check ማለት አንድን አካል ብቻ ሳይሆን ለምሳሌ ግለሰቧን፣ የህክምና ማስረጃ ካላት እሱን፣ የትምህርት ማስረጃዎቿን፣ ዩኒቨርስቲውን... በማናገር መረጃዎችን አመሳክሮ የሚሰራ እንጂ ግለሰቦችን ለማጥቃት የሚከናወን ስራ አይደለም
አሊያስ መሰረት