Get Mystery Box with random crypto!

ሰው ሁለት ጽዋ ታቅፎ ይኖራል፤ ባንዱ የመረረ ጭላጭ፡ በሌላው ጥዑም አርኪ ፈሳሽ በየትኛው ጊዜ፤ በ | ABX

ሰው ሁለት ጽዋ ታቅፎ ይኖራል፤ ባንዱ የመረረ ጭላጭ፡ በሌላው ጥዑም አርኪ ፈሳሽ
በየትኛው ጊዜ፤ በየቱ ፈረቃ፤ ከምኑ ዋንጫ ውሰጥ እንደሚጎነጭ፤ ሲዋትት፤ ሲረበሽ
ይነጉዳል፤ ይፈሳል፤ ቀን ውሎ፤ ቀን ሲመሽ፤
ሆኖም፤
ላታህዘን ነውና የጀሊሉ አማን(ና)
ኮሶ ስትጠጣ፤ አምርረህ፤ ተክዘህ፤ አትርሳ፤ ሌላውን
ከሃላሉ ወይን ከሆነልህ፤ ፍርቃው፤ ፈንድቀህ ያለልክ፤ አትጣ መላውን!
ይልቅ፤
በተራ ነውና፤ የዱኒያ፤ ፍጥራዋ
ሳትባክን፤በርትተህ፤ ትጋ ለኋላዋ!

http://t.me/MuhammedSeidABX