Get Mystery Box with random crypto!

አል-ከሪሙ አላህ (ሱ.ወ) ከውሃና ከአፈር በመፍጠር እኛን የሰው ልጆችን ክብር ሰጥቶናል፡፡ ውሃና | ABX

አል-ከሪሙ
አላህ (ሱ.ወ) ከውሃና ከአፈር በመፍጠር እኛን የሰው ልጆችን ክብር ሰጥቶናል፡፡ ውሃና አፈር በፍጥረተ-ዓለሙ ውስጥ የሚገኙ እጅግ ንፁህ የሆኑ ነገሮች ናቸው፡፡ ይህም ፅዱና ንፁህ ፍጡር መሆናችንን ያመለክታል፡፡ ስለሆነም በሀጢአትና በመናፍቅነት ራሳችንን አንነጅስ፣ ራሳችንን አናዋርድ፡፡ እኛ የጠራን ፍጡር ነን፡፡ የቁርአን እናት ፈቲሓ እንደሆነችው ሁሉ እኛም የፍጥረተ-ዓለሙ ቁንጮ ነን፡፡ ….
እኛ በምድር ላይ የአላህ ምትኮች ነንና ከርካሽ ነገሮችና ከርካሽ ስሜቶች ከፍ ማለት ይኖርብናል፡፡ ያከበረንን አላህ ማክበር ይኖርብናል፡፡ ራሳችንን የማክበር ሰሜት ውስጣችንን የፈጠረውን አምላክ ልናከብር ይገባል፡፡
በስህተት ላይ በምንወድቅበት ጊዜ ራሳችንን እንንቃለን፡፡ ትላልቅ ወንጀሎች ትላልቅ የተባሉበት ምክንያት እነርሱ እኛን በማዋረዱ ረገድ ትልቅ ስለሆኑ ነው ይባላል፡፡
እኛ የቸሩ፣ የተከበረው ጌታ ባሮች ነንና ራሳችንን አናዋርድ፡፡ በሀጢአት፣ በንፍቅና በውሸት ራሳችንን አናዋርድ፡፡ አንድም ሰው ሀጢኣታችንን ባያውቅ እንኳ ራሳችን በራሳችን ላይ የምንመሰክረው ይብቃ፡፡ ራሳችን ራሳችንን የምንታዘበው ይብቃን፡፡ በሌሎች እይታ ውስጥ ገብተን ከመዋረድ እንጠንቀቅ፡፡ ሁሌ እየተሸማቀቁ ከመኖርና መጠቋቆሚያ ከመሆን እንራቅ፡፡ ሰላም አይኖረንምና፡፡ ኃጢኣተኛ እንደሌባ ነው፤ጩኸት ሁሉ ወደርሱ ይመስለዋል፡፡

"ቢስሚከ ነሕያ" ከተሠኘው መጽሐፍ የተወሰደ
ነጃሺ መፃሕፍት መደብር ያገኙታል፡፡

ዶ/ር ዐምር ኻሊድ እንዳዘጋጀው
ሙሐመድ ሰዒድ ABX እንደተረጎመው


https://t.me/NejashiPP