Get Mystery Box with random crypto!

የዛሬው ታሪክ ደግሞ እንዲህ ይላል፦ መካ የደረሱ የአላህ እንግዶች የተከበረ ቤቱን እየጦወፉ ነው፤ | ABX

የዛሬው ታሪክ ደግሞ እንዲህ ይላል፦

መካ የደረሱ የአላህ እንግዶች የተከበረ ቤቱን እየጦወፉ ነው፤ በዚሁ መሃል አንድ ሰው ተነሳና ልብሱ ከፍ አድርጎ የዘምዘም ዉሃ ዉስጥ መሽናት ጀመረ፤ የመስጂዱ ዘበኞች ወዲያዉኑ ተረባርበው ያዙት፡፡ ወደ መካው አሚር አመጡት፡፡
'ምንድነው እንዲህ ለማድረግ ያነሳሳህ?' አሉት፡፡ “የዘምዘም ዉስጥ የሸናው ሰዉዬ ይሄ እኮ ነው፡፡” ብለው ሰዎች እንዲያውቁኝ ነው፡፡” አለ፡፡

ይኸዉላችሁማ
አይደለም እዚህ በዚያ በተከበረው እና በተቀደሰው ምድር ጭምር ሁለት ዓይነት ሰዎች አሉ፡፡ አንደኛው አላህ ዘንድ ለመታወቅ ይለፋል፤ ሌላው ሰዎች ዘንድ ለመታወቅ ለጀብደኝነት ይሮጣል፤ ዓላማው መታወቅ ነው።
ትክክለኛ የሐጅ ያደረገ ሰው ልክ እናቱ እንደወለደችው ሆኖ ከወንጀሉ ሁሉ ጠርቶ ይመለሳል፡፡
ሁለተኛው - መታወቅን ነዉና ያሰበው ይኸው ቢያንስ ዛሬ እንኳ በምሳሌ አነሳነው፤

ሰዎች ግን ክብር የማይሆንላቸው ለምንድነው ?

..http://t.me/MuhammedSeidABX